አላስፈላጊ የሰውነት ክብደት መቀነስ አዘውትሮ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፦ ቢያንስ በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ መንቀሳቀስ ጤናማ አመጋገብ፦ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ዝቅተኛ ቅባት ያለው የወተት ምርቶች በአመጋገብዎ ውስጥ ሶዲየምን (sodium ) ይቀንሱ፦ ጨው አለመጠቀም፣ የተዘጋጁ ምግቦችን አለማዘውተር ወይም የምግብ መለያዎችን ያንብቦ አነስተኛ ሶዲየም ያለውን መምረጥ የአልኮል መጠጥ፣ ካፌይን ምሳሌ ቡና፣ እና ጭንቀት ይቀንሱ ሲጋራ ማጨስ ማቆም
በተፈጥሮ ለልብ ህመም ተጋለጭ የሆኑ ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ የበሽታውን የመከስት እድል ከ50 በመቶ በታች ዝቅ ማድረግ እንደሚችሉ አንድ ጥናት አረጋገጠ።እድሜያቸው ከ40 እስከ 69 የሆኑ 482ሺህ 702 የብሪታኒያ ሰዎች ላይ ጥናቱ ተካሄዶ ውጤቱ እንደተገኘም ነው የተገለጸው። የልብና የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠነክሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በመስራት የልብ ህመምን፣ የደም ዝውውርና መርጋት እንከኖች መቀነስ እንደተቻለም በጥናቱ ተጠቅሷል። ከልብ ደም የሚመልሱ የደም ስሮች ላይ...
ያልተለመደ ወሲብ በተለይም በፊንጢጣ በኩል (anal sex) በመፈፀምና ከአንድ በላይ ወሲብ አጋር በመያዝ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ የሚፈረጀው የፊንጢጣ ካንሰር ነው፡፡ እንዶኒውስዊክ መፅሔት ሰፊ ዘገባ ከሆነ ይህን ካንሰር ለየት የሚያደርገው ችግሩ ከአንዳንድ ሴቶች ቅጥ ያጣ የወሲብ ባህሪ ጋር የሚያያዝ መሆኑና በዚህም ማህበረሰባዊነት በሌለው ባህሪ ሳቢያ የሚከሰተውን ካንሰር ለሌሎች ለመናገር አሳፋሪ (taboo) መሆኑ ነው፡፡ ለሰዎች በተለይም ለሐኪም የማይነግርበት አንዱ ምክንያት...
በተፈጥሮአዊ መንገድ ህክምና ድረስ መሄድ ሳያስፈልገን ቤታችን ውስጥ ጥርሳችን እንዴት ማንጣት እንችላለን? በተፈጥሮአዊ መንገድ ዘውትር በጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተአምር ትመለከታለህ እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን? መጠን 1 ለብ ያለ ውሃ ሁለት ብርጭቆ 2 የተፈጨ ቀረፋ አንድ ማንኪያ 3 የንብ ማር አንድ ማንኪያ 4 የሎሚ ጠብታዎች አዘገጃጀት ትንሽ ተለቅ ባለ ብርጭቆ ውሃውን እንጨምራለን ከዚያም ቀረፋውን እና ማሩን እናስከትላለን በመጨረሻም ከአምስት የማይበልጡ የሎሚ ጠብታዎችን እንጨምርበትና በደንብ አዋህደን ስናበቃ ዘውትር...
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ድረ ገፆች የሚሰራጩ የተሳሳቱ የአመጋገብ ስርዓትን መሞከር በጤና ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል። ለምሳሌ አወዛጋቢ በሆነ መልኩ ውሃን በምግብ ወቅት አለመጠጣት የሚመለከቱ መረጃዎች የሚሰራጩባቸው ድረ ገፆች አሉ። ይህ ያልተለመደ አመጋገብ ከየት እንደሚመጣ ወይም ለምን ያህል ጊዜ እንደሚሠራ ግልፅ ባልሆነ መልኩ ከዚህ ቀደም 17 ሺህ 600 ፅሁፎች በኢንስታግራም የማህበራዊ የትስስር ገፅ ላይ መጋራታቸውን ባለሙያዎች ያወሳሉ። ይሁን...