ካፌይን እና መዘዞቹ

ካፌይን እና መዘዞቹ

🕔12:08, 18.Mar 2015

ካፌይን አዕምሮን ለማነቃቃት የሚረዳና በተለይ በቡና፣ በሻይና በተለያዩ የለስላሣ መጠጦች ውስጥ በስፋት የሚገኝ ኬሚካል ነው፡፡ ካፌይን ከእነዚህ መጠጦች በተጨማሪ በቸኮሌቶች፣ በብስኩቶችና በተለያዩ የህመም ማስታገሻና የራስ ምታት መድሃኒቶች ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ኬሚካል ሱስ የማስያዝ ባህርይው ከፍተኛ ነው፡፡ የተጠቀሱት መጠጦችና ምግቦች እንዲሁም

Read Full Article
የአልኮል መጠጥን አብዝቶ በመጠጣት ምክንያት የሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች

የአልኮል መጠጥን አብዝቶ በመጠጣት ምክንያት የሚጎዱ የሰውነት ክፍሎች

🕔13:33, 5.Mar 2015

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም) 1) ልብ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ ማዘውተር የልብ ጡንቻዎችን በማዳከም የደም ፍሰት መዛባትን ያሰከትላል፡፡ በአልኮል መጠጥ ብዛት የሚከሰት የልብ ሕመም የትንፋሽ ማጠር፤ የተዛባ የልብ ምት፤ድካም፤የማያቋርጥ ሳልን ያስከትላል በተጨማሪም ለደም ግፊት እና ለድንገተኛ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ይዳርጋል፡፡

Read Full Article
ሺሻ የማጨስ አደጋዎች –

ሺሻ የማጨስ አደጋዎች –

🕔13:03, 28.Jan 2015

መቀመጫውን በአሜሪካው ጆርጂያ ክፍለ ግዛት ፣ አትላንታ ከተማ ያደረገው በአለም ታዋቂው የጤና የምርምር ተቋም Centers for Disease Control and Prevention (CDC) ሺሻ የማጨስን አደገኛነት አስመልክቶ ያወጣው ሊነበብ የሚገባው መረጃ። በኢትዮትዩብ የዝግጅት ክፍል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እንደሚከተለው ቀርቧል፦ —  እንደ ሲጋራዎች ሁሉ፣

Read Full Article
የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ የጤና ችግሮች

የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ የጤና ችግሮች

🕔19:56, 15.Jan 2015

  በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ‹‹የወሲብ ፍላጎትን ያነሳሳሉ›› በሚል እምነት ተዘውትረው ጥቅም ላይ የሚውሉ አልኮል መጠጦችና ሌሎች ሱስ አስያዥ እፆች ሰዎች ከወሲብ ማግኘት የሚገባቸውን እርካታ እንዲያጡ የሚያደርጓቸው ከመሆኑም በላይ በአጠቃላይ የጤና ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያስከትሉ በቅርቡ ይፋ የሆኑ ጥናቶችና

Read Full Article
ሱስና መፍትሄዎቹ

ሱስና መፍትሄዎቹ

🕔21:59, 6.Nov 2014

አንድ ስኒ ቡና ለንቃት ሁለትና ሶስት ድብን ብሎ በመተኛት የካፌይን ተፅዕኖ ሲገለፅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ስራ፣ ጥናትንና በአጠቃላይ ለነቃ ውሎ ስንል ካፌይን ብለን የምንጠራውን ኬሚካል የያዙ መጠጦችንና ምግቦችን እንወስዳለን፡፡ በተለይም የዚህ ኬሚካል በብዛት መገኛ የሆኑትና በደከመንና በዛልን ወቅት ከድብርትና ከዱካክ ወጥተን

Read Full Article
ሲጋራ ለማቆም የሚረዳው ተክል

ሲጋራ ለማቆም የሚረዳው ተክል

🕔12:46, 29.Sep 2014

በ ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ) ይህ ተክል በአማርኛ በትንጀን (ደብርጃን) የሚባል ስም ሲኖረው በዎልፍ ሌስላው የተዘጋጀው የእንግሊኛ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ደግሞ ‹‹ማደርቻ፣ መደርቻ›› ብሎ ይገልፀዋል፡፡ ለጋራ መግባባት እንዲመቸን በእንግሊዝኛ መጠሪያው ‹‹ኤግፕላንት›› እያልን እንጥራው፡፡ ኤግ ፕላንት ከ10ሩ አወዛጋቢ ምግቦች (10 most controversial foods

Read Full Article
የአልኮል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦች

የአልኮል ተጠቂነትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ጠቃሚ ሃሳቦች

🕔05:31, 22.Aug 2014

ሀሰን አሰፋ (የኛ ፕሬስ) በፍቅረኝነት ጊዜና በትዳር ውስጥ ሴቶች ‹‹ባለቤቴን ከአልኮል ሱሰኝነት እንዴት ልታደገው እችል ይሆን?›› በማለት ይጨነቃሉ፡፡ ወንዶችም ፍቅረኛቸው የአልኮል ተጠቂ ከሆነች እንዲሁ ነው፡፡ የአልኮል ተጠቂዎችም እንዴት ከአልኮል ሱሰኝነት እንደሚወጡ በብርቱ ያስባሉ፡፡ ከአልኮል ሱሰኝነት መላቀቅ የቻለ አንድ ሰው አልኮል

Read Full Article
ሲጋራ የውበትና የገፅታ፣ የስያሜና የአርማ እገዳ ተጣለበት

ሲጋራ የውበትና የገፅታ፣ የስያሜና የአርማ እገዳ ተጣለበት

🕔17:06, 15.Jun 2014

ጤናንና ህይወትን ለመታደግ ነው ተብሏል ሲጋራ ማጨስ ለከፍተኛ የጤና አደጋ፣ ባስ ሲልም ለህልፈት እንደሚዳርግ ማንም ሊክድ አይችልም። እንዲያም ሆኖ ከወደ አየርላንድ የተሰማው አዲስ እገዳ ክፉኛ ያስደነገጠው ከአጫሾች ይልቅ የትምባሆ ኩባንያዎችን ነው። ሰሞኑን አየርላንድ ማንኛውም ሲጋራ ስያሜ፣ የንግድ ምልክትና አርማ እንዳይኖረው

Read Full Article
ሱስን ለማቆም የሚጋጥሙ መሰናክሎች

ሱስን ለማቆም የሚጋጥሙ መሰናክሎች

🕔04:16, 11.Jun 2014

“አዲስ ለተወለደው ልጃችን ጤንነት ስል ማጨስ ለማቆም ወሰንኩ። በመሆኑም ‘ማጨስ ክልክል ነው’ የሚል ምልክት ቤታችን ውስጥ ለጠፍኩ። ልክ ከአንድ ሰዓት በኋላ የኒኮቲን ሱሴ ውስጤን እንደ ሱናሚ ሲያናውጠው ግን ሲጋራ ለኮስኩ።”—ዮሺሚትሱ፣ ጃፓን የዮሺሚትሱ ተሞክሮ እንደሚያሳየው ማጨስ የማቆም ሂደት የራሱ የሆኑ መሰናክሎች

Read Full Article
ስለ ጫት ጎጂነት ከብዙ በጥቂቱ

ስለ ጫት ጎጂነት ከብዙ በጥቂቱ

🕔13:44, 28.May 2014

በጫት ተክል ወይም ቅጠል ውሰጥ ብዙ የሆኑ ንጥረነግሮች (ኪሚካሎች) ሲኖሩ፤ በጤንነት ላይ ጉዳት ያሰከትላሉ ተብለው በይበልጥ የሚታመንባቸው ሶሰት ናቸው። እነሱም ካቲኖን፣ ካቲን እና ታኒንሰ ናቸው። ካቲኖንና ካቲን በአወቃቀርም ሆነ በአስራር አንፊታሚን ተብሎ ከሚታወቀው ኬሚካል / መድሃኒት ጋር ተቀራራቢ ናቸው። ሆኖም

Read Full Article
አደገኛ እፆችና የሚያስከትሉት የጤና ቀውስ

አደገኛ እፆችና የሚያስከትሉት የጤና ቀውስ

🕔19:15, 10.Feb 2014

የአደገኛ እጾች መዘዝ የልብ በሽታየአዕምሮ መዛባትየእንቅልፍ እጦትተስፋ የመቁረጥ ስሜትጭንቀትና መደበትራስን የማጥፋት ፍላጎት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሣይኮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የአራተኛ ዓመት ተማሪ እያለ ነው ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ እፅ መጠቀም የጀመረው፡፡ ለከፋ ጉዳትና ውስብስብ ችግር እንደሚዳርገው፣ የልጅነት ህልሙን እንደሚያጨናግፍበትም ፈጽሞ አላሰበም፡፡ በትምህርቱ ከሰቃዮቹ ተርታ ሚመደበው

Read Full Article
የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ

የአልኮል መጠጦችና እፆችና ወሲብ

🕔18:57, 19.Oct 2013

በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ‹‹የወሲብ ፍላጎትን ያነሳሳሉ›› በሚል እምነት ተዘውትረው ጥቅም ላይ የሚውሉ አልኮል መጠጦችና ሌሎች ሱስ አስያዥ እፆች ሰዎች ከወሲብ ማግኘት የሚገባቸውን እርካታ እንዲያጡ የሚያደርጓቸው ከመሆኑም በላይ በአጠቃላይ የጤና ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያስከትሉ በቅርቡ ይፋ የሆኑ ጥናቶችና ባለሙያዎች

Read Full Article
በትዳር መካከል ጸብ ሲነሳ እንዴት መፍታት ይቻላል?

በትዳር መካከል ጸብ ሲነሳ እንዴት መፍታት ይቻላል?

🕔17:24, 10.Aug 2013

ከሊሊ ሞገስ ትዳር በባህር ወይም ውቅያኖስ ውስጥ ያለችን ትልቅ መርከብ ይመስላል፡፡ መርከቧ ረጅም ርቀት እንደመጓዟ ለተለያዩ አየር ፀባይ ለውጦች መጋለጧ አይቀሬ ነው፡፡ ፀጥታና ሰላም የሰፈነበት ጉዞ እንደምታደርግ ሁሉ አንዳንዴ ማዕበልና ሞገድ ለበዛበት ነፋስ፣ ለተተናኳሽ ሻርኮች፣ ከበረዶ ክምር ጋር ለግጭት፣ ቀደም

Read Full Article
ጫት መቃም ከሚያስከትላቸው ጉዳቶት ውስጥ ( የወንድነት ስሜት ያጠፋል/ያሳጣል/ )

ጫት መቃም ከሚያስከትላቸው ጉዳቶት ውስጥ ( የወንድነት ስሜት ያጠፋል/ያሳጣል/ )

🕔20:11, 14.May 2013

ጨጓራ ተልጦ ጥርስ እየረገፈ የለጋነት እድሜ በከንቱ አለፈ፡፡ በጤና በአካል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ጫት ለጤና ጠንቅነቱ ለሥነ-ምግባር ብልሹነቱ መንስኤነቱ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ላይ ጎጂነቱ ማንም ሠው የሚያውቀውና የሚመሠክረው እውነታ ለመሆኑ አይደለም ጤነኞችን፣ እብዶችን፣ አዋቂዎችን ሳይሆን መሀይሞችን የማይቅሙትን ሳይሆን ቃሚዎችን መጠየቅና ማረጋገጥ

Read Full Article
ስለ ጫት ምን ያውቃሉ  –  ከዘለቀ ወ.አ

ስለ ጫት ምን ያውቃሉ – ከዘለቀ ወ.አ

🕔20:02, 14.Jan 2012

  በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውሰጥ በየከተማው አሰተዉሎ ለሚመለከትው ሁሉ ብዙ ሰዎች ጫት አንደሚቅሙ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። በየቦታው የጫት ምርት ጨምራል፤ የመሸጫና የመቃሚያ ሱቆች በብዛት ተከፍተዋል፡ የመጋበዣ ማሰታወቂያዎችም እንደዚሁ በየቦታው ተለጥፈው ይታያሉ። ዘር፤ ሀይማኖት፤ ጾታ፤ የሰራ አይነት ወዘት ሳይገድበው ሁሉም የህብረተስብ

Read Full Article
የወሲብ ሱስ (Sex Addiction)

የወሲብ ሱስ (Sex Addiction)

🕔16:39, 30.Dec 2010

  ብዛቻችን ሱስ ሱባ የምናያይዛ ከሲጋራ ከመጠጥና ከመሣሰሉት ጋር ብቻ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ የተለያዩ የአደነዛዥ ዕፆችን ተጠቃሚነት ሱስ በዋናነትየሚጠቀስ ሱስ ነው፡፡ ከዚያ በተለየ ወሲብንስ ብናይ ለመሆኑ የወሲብ ሱስ አለው? ብለን ብንጠይቅ መልሳችን አንድና አንድ ነው እሱም “አዎ!የወሲብ ሱስ አለው፡፡” ነው፡፡ ልክ እንደ ሲጋራ፣ እንደ አልክሆል፣ ጫት አሊያም ቁማር መጫወት ከመጠን ሲያልፍ እና ግለሰቡ ራሱን መቆጣጠርሲያቅተው ሱስ ሆነበት እንደምንለው ሁሉ ወሲባዊነት ከገደቡ በላ አልፎ አዕምሮንና ድርጊትን የሚቆጣጠርበት ደረጃ ላይ ሲደርስ የወሲብ ሱሰኝነትደረጃ ላይ ሲደርስ የወሲብ ሱሰኝነት ብለን እንጠራዋን፡፡   ይሄም ሱስ በማህበረሰቡ ላይ በሰፊው የተንሰራፋና ሁሉም ሰው በልቡ እያወቀው ከሌሎቹ የሱስ ዓይነቶች ባነሰ እውቅና የሚሠጠው እና እንደቀልድ ተደርጎ የሚወራ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የሴሰኝነት ባህሪ በተለያየ መንገድ ሊገደጋጋሚ የፖርኖግራፊ ምስል እና ቪዲዮዎችን በመመልከት፣ ከተለያዩሰዎች ጋር ግንኙነት በመፈጸም ፣ ወደ ሴተኛ አዳሪዎች አብዝቶ በመሄድ፣ ስለ ወሲብ በብዛት  በማሰብ እንዲሁም በማውራት እና በተደጋጋሚ ወሲብንበመፈጸም ሊሆን ይችላል፡፡   ለመሆኑ የወሲብ ሱስ ምንድነው ?   ወሲብ ማለት ከሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜቶች መካከል ዋነኛው ሲሆን፣ በአግባቡሲጠቀሙበት ደግሞ ትውልድን ከመተካት ባሻገር ታላቅ የሆነ ደስታን የሚሰጥ ስሜትነው፡፡ ይኸውም ማንኛውም ነገር ከመጠን በላ ሲበዛም ሆነ ከሚገባው መጠን ሲያንስችግር እንደሚያስከትለው ሁሉ ወሲባዊ ባህሪይም ከመጠን ሲያንስም ሆነ ከመጠን በላይሲያልፍ የግለሰቡን ጤንነት እና ማህበራዊ ኑሮ ያቃውሳል፡፡ ሴሰኝነት ከሃሳ ወደ ድርጊትየሚሸጋገር ባሪ ነው፡፡ ይህም ባህሪይ በአንድ ስው አዕምሮ ውስጥ ገዥ ሲሆን፣ መላውየህይወት ኃይሉ ልቅ በሆኑ የወሲብ ሃሳቦች ተሞልቶ ወደ ድርጊት ሲወጣ ሰዎችገንዘባቸውን ፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውን ፣ እውቀታቸውን፣ ኃላፊነታቸውንናተፈጥሮሯቸውን ሳይቀር ልቅ ለሆነ የወሲብ ስሜታቸው ማርኪያ ይጠቀሙበታል፡፡በአብዛኛው ከተቃራኒጾታዎች ጋር ያላቸው ግንኙነትና ሃሳብም ወደ ወሲብ ስሜት ዝቅይላል፡፡   የወሲብ ሱሰኝነት በግለሰቡ ላይ በሚያደርሰው አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት፣ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ማበራዊ ግንኙነት በመላሸት እንዲሁምበሚፈጠረው ገለልተኝነት ከሌሎች ሱሶች ጋ ተመሳሳይ ሲያደርገው የሚለይበት ደግሞ ሳይጫወትም ሆነ አልክሆል ሳይጠጣ መኖር የሚቻል ሲሆንወሲብ መፈጸምን ግን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ አንዱ አካል በመሆኑ የተነሣ እስከነአካቴው ይቅር የሚሉት አይደለም፡፡   በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች በሁኔታዎች ተገደውም ሆነ በራሳቸው ምርጫ ከወሲባዊ ባህሪይ ርቀው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ጤናማ የሆነ ሰው ግን ወሲባዊፍላጎት ይኖረዋል፡፡ እንዳውም የወሲብ ፍላጎት አለመኖር ወይም መቀነስ በራሱ ችግር ነው፡፡   ወሲባዊ ሱስ ማለት እየጨመረ የሚሄድ ተደጋጋሚ በሆነ የወሲብ ሃሳብ እና ድርጊት የሚገለጥ ስነ-ልቦናዊ ጥገኝነት ነው፡፡ ለአንዳንድ የወሲብ ሱሰኞችይሄ ችግር በተደጋጋሚ ፖርኖግራፊ ከመመልከት፣ ወሲብ ከመፈፀም ወይም በተደጋጋሚ ወሲብ መፈፀም ከመፈለግ ላያልፍ ይችላል፡፡ ይሄ ጥገኝነትደግሞ ከሌሎች ምክንያቶች ጋር ተደማምሮ ከፍተኛ የአዕምሮ ቀውስ ሲያስከትልና ወደ አደገኛ የሆነ ከራስም አልፎ ሌሎችን ሰዎች ወደ ሚጎዳእንደአስገድዶ መድፈር በህፃናት ላይ ወሲባዊ ጥቃትን መፈፀምና ወደ መሳሰሉት ድርጊት ሊሸጋገር ይችላል፡፡   ሁሉንም ባህሪያት አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም የሚፈፁሙት በድብቅ ስለሚሆን በቅርበት ባሉ ሰዎች ሁሉ የመታወቅ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው፡፡   በዚህ ሱስ ውስጥ የሚገኝ ሰው አዕምሮው ልቅ የሆነ ወሲብን መፈፀም ምግብን እንደመመገብ አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚቀበለው አብዛኛውን ጊዜውንከወሲብ ጋር በተያያዙ ሀሳቦች እና ድርጊቶች ይወጠራል፡፡ እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ወሲብ መፈፀም ትልቁ የእርካታ ምንጫቸው እንደሆነ ቢያስቡምየተቃራኒ ጾታ ግንኙነታቸው ፍቅር የጎደለው እና እንደ መጠቀሚያ ቁስነት የመቁጠር ያህል ነው፡፡ ወሲባዊ ስሜታቸውም በሚነሳሳበትም ጊዜራሳቸውን አደጋ ውስጥ በሚከት ሁኔታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ በዚህም የተነሣ ከግብረ-ሥጋ ግንኙነት በሚመጡ በሽዎች የመያዛቸው ዕድል ሰፊነው፡፡   እንዲሁም በወሲብ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ወሲብን እርካታን ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ከመጥፎ ስት ለመሸሽ፣ ፍርሃትንና ጭንቀትን ለማስወገድ እንደመደበቂያነት ሲገለገሉበት ይታያሉ፡፡ ድርጊቱን ከፈፀሙ በኋላ ግን በአብዛኞቹ የማዘን እና የመፀፀት ስሜት ስለሚከተልባቸው ዳግመኛ ላለመፈፀምቃል ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ጊዜ በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን መልሰው ያገኙታል፡፡   በትዳር ሕይወት አሊያም ደግሞ በፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ ያሉ ሴሰኞች ከፍቅረኞቻቸው ውጭ ከተለያ ሰዎች ጋር ወሲብ ስለሚፈፅሙ የተቃራኒ ጾታግንኙነታቸው ሊበላሽ ይችላል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በሚኖራቸው የወሲብ ግንኙነት አለመጣጣም ሊኖር ስለሚችልከሚወዱት ሰው ጋር ለመያየት ሊፈጠር ይችላል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ባሕሪይ ጋር በተያያዘ በሥራ ገበታ ኃላፊነትን አለመወጣት እና ያልተገባባሕሪይን ስለሚያሳዩ በሥራ ሕይወታቸው ውጤታማ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡   የወሲብ ሱስ መገለጫዎችከተለያዩ ሰዎች ጋር ወሲብ መፈፀም ወይንም መፈለግ ከሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ረጅም ጊዜን የወሲብፍጎትን ለሟሟላት በሚደረጉ ጥረቶች ማሳለፍ ለወሲብ ቅድሚያ በመስጠት ሌሎች በማህበረሰቡ የተሰጡ የሥራ፣ የቤተሰብ እና የትዳር ኃላፊነቶችንችላ ማለት ተመሳሳይ የሆነ ወሲባዊ እርካታን ለማግኘት ይበልጥ ለመጨመር መገደድ በተደጋጋሚ ሁኔታ ወሲብን መፈጸም ከሰዎች ጋር የሚመሠረቱግንኙነቶች በቀዳነት በወሲብ ላይ ያተኮሩ መሆን ወሲባዊ ባህሪን ሳያስታግሱ ሲቀሩ የባህሪ መለዋወጥ (መቆጣት፣ መነጫነጭ..)       መንስኤው መንድነው?   የወሲብ ሱሰኝነት የተለያዩ መንስኤዎች በአንድ ላይ ተዳምረው የሚያመጡት ችግር ነው፡፡ከዚህም ውስጥ በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው በልጅነት አስተዳደግ ወቅት የሚፈጠሩ እናከወሲብ ጋር የተያያዙ ክስተቶች መፈጠር ነው፡፡ በተለይ በልጅነት መደፈር ወይም ደግሞከትክክለኛው ዕድሜ ቀደም ብሎ የሚከሰቱ ወሲባዊ ልምምዶች ያንን ግለሰብ በቀሪ ህይወቱከወሲብ ጋር የተያያዘ ጥብቅ ቁርኝት እንዲኖረው ያደርጋሉ፡፡   በዘርፋ በተደረገ ጥናት ሊታወቅ የቻውም በወሲብ ሱሰኝነት ተጠቂ ከሚሆኑት ሰዎችመካከል ከግማሽ በላይ በልጅነታቸው ወቅት ወሲብን መፈጸም የጀመሩ አሊያም ወሲባዊጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን ነው፡፡   ከዚህም ጋር በተያያዘ በመጀመሪያው የወሲብ ግንኙነታቸው ወቅት የአስገድዶ መደፈር ሰለባየሆኑ ሴቶች በቀሪው ወሲባዊ ህይወታቸው ሁለት ዓይነት አማራጮችን ሊከተሉ ይችላሉ፡፡አንደኛው ለወሲብ ከፍተኛ የሆነ ጥላቻን ማዳበር እና ምንም ዓይነት ደስታ እንደማይገኝበት አምነው መቀበል ሲሆን ፣ ሌላኛው ደግሞ ከፍተኛ የሆነየወሲብ ፍላጎት ማዳበር ውስጣዊ ጠባሳን የበለጠ ወሲብ በመፈጸም ለመሸፋፈን መሞከር ነው፡፡ እነዚህም ሴቶች ወሲባዊ ስሜታቸውን ለማርካታበሚል ብቻ ምንም አይነት ውስጣዊ መተዋወቅ እና መግባባት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ወሲብን መፈፀም ቀላል ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዚህምባሕሪያቸው የተነሣ እውነተኛ የሆነ ፍቅር ከፊታቸው ሆኖ በሚገኝበት ሁኔታ ውስጥ ለመሰብሰብ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም እንኳ በአካላዊ ስሜት ብቻበመገፋፋት በሚኖራቸው ወሲባዊ ህይወት የፍቅር ሕይወታቸው የተበላሸ መሆኑ አይቀርም፡፡   በተጨማሪም በአንዳንድ ሁኔታዎች ከልክ በላይ የሆነ ወሲባዊ እንቅስቃሴ ለራሳችን የሚኖረንን አመለካከት እና የበታችነት ስሜት ሊያንፀባርቅይችላል፡፡ የወሲብ ስሜት ከስጦታዎች አንዱ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊት ከሚገኘው የደስታ እና የእርካታ ስሜት ባሻገር ተፈጥሮን ለመቀጠል እና በጊዜየተገደበውን የሰው ልጅ ሕይወት መቀጠያ ታላቅ ጥበብ ነው፡፡ በዚህም የተነሣ ይሄንን  የተሠጠንን ታላቅ ሥጦታ በአግባቡ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ይሄም ማለት በውስጣችን ያለውን ተፈጥሪአዊ ስሜት በቁጥጥራችን ሥር በማድረግ በተገቢው ቦታ፣ በተገቢው ጊዜ፣ ከተገቢው ሰው ጋር ሆኖመጠቀም የተፈጥሮ ህግ ሥር የሚገኝ በመሆኑ ይህንን ተገንዝበን ትክክለኛ የሆነ የወሲብ ባሕሪይን በዕድሜያችንና ከምንኖርበት ማበረሰብ እና ከጊዜውጋር በማጣጣም ማስኬድ ጤናማነትን ይገልፃል፡፡   ምክንያቱም አርስቶትል እንደተናገረው የሰው ልጅ የመጨረሻ ፍላጎቱ ደስታን መጎናፀፍ እንደመሆኑ ይህንን ደስታ ቋሚ ለማድረግ ደግሞ ስሜታችንን፣ድርጊታችንና ፍላጎታችንን ከልክ ሳያልፍና ጉድለት ሳይኖርበት የተጠበቀ ማለትም መካከለኛ ወይንም ሚዛናዊ ማድረግ አለብን፡፡ በጣም የበዛም ሆነበጣም ያነሰ ነገር ጎጂ በመሆኑ ነገሮችን ሁሉ በሁለቱ መካከል ሚዛናችንን መጠበቅና ማመጣጠን መቻል አለብን፡፡  

Read Full Article
ማጨስ ክልክል ነው!!!

ማጨስ ክልክል ነው!!!

🕔17:27, 20.Feb 2010

ውድ አንባቢያን በመቀጠል ሌላውንና በጤናችንና በማህበራዊ ሕይወታችንከፍተኛ የሆነ ጉዳት ስለሚያመጣው፣የሲጋራ ሱስ በሰፊው እንመለከታለን፡፡ እ.ኤ.አ እስከ 1940 ዎቹ ድረስ ሲጋራን ማጨስ ምንም ጉዳት እንደሌለውናእንዲያውም የቅንጦት እና ክብር መገለጫ ተደርጎ ይታስ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግንበተደረጉ የላብራቶሪ ፍተሸዎች እንደተረጋገጠው ከአንድ ሲጋራ የሚወጣው ጭስወደ 4ሺህ ዓይነት ኬሚካል ንጥረ-ነገሮችን የያዘ፣ ከእንዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹመርዛማነት ያላቸውና 43 ያህል ደግሞ ካንሰርን ሊያመጡ የሚችሉ መሆኑን ነው፡፡

Read Full Article
ማጨስ ለአዕምሮ ህመም ያጋልጣል

ማጨስ ለአዕምሮ ህመም ያጋልጣል

🕔02:30, 20.Nov 2008

ሲጋራ ማጨስ ለሳምባ ካንሰርና ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያጋልጥ በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ የጥናት ውጤቶች አሳይተዋል፡፡ ሰሞኑን በዩናይትድ ስቴትስ ይፋ የተደረገው አንድ የጥናት ውጤት በበኩሉ በየዕለቱ በከፍተኛ ሁኔታ ማጨስ ለተለያዩ የአእምሮ ህመሞች የመጋለጥ እድልን ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል አስረድቷል፡፡ ዜናውን ከሥፍራው ያሰራጨው ቢ.ቢ.ሲ.

Read Full Article
ወጣቶች ለካንሰር ከሚዳርጉ ሱሶች ራሳቸውን በማራቅ የበሽታውን መስፋፋት እንዲገቱ አሶሴሽኑ ጠየቀ

ወጣቶች ለካንሰር ከሚዳርጉ ሱሶች ራሳቸውን በማራቅ የበሽታውን መስፋፋት እንዲገቱ አሶሴሽኑ ጠየቀ

🕔01:41, 15.Oct 2008

ወጣቶች ለካንሰር ከሚዳርጉ ሱሶች ራሳቸውን በማራቅ የበሽታውን መስፋፋት መግታት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን አሳሰበ፡፡ በአዲስ አበባ የካንሰር በሽታን የመመዝገብ ሥራም ተጀምሯል፡፡የአሶሰሴሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ቦጋለ ሰለሞን የአሶሴሽኑ ዘጠነኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ሲካሄድ እንዳሳሰቡት የአገር ተረካቢ የሆኑት ወጣቶች ለካንሰር ከሚያጋልጡ እንደ

Read Full Article
“በመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ… መጠን አትለፋ…”

“በመጠጥ ደስታ ይገኛል ብላችሁ… መጠን አትለፋ…”

🕔17:29, 10.Sep 2008

አልኮል መጠጥ ሱስ ራሱን የቻለ በሽታ ሲሆን ፣ ዋነኛመገለጫውም ከፍተኛ የሆነ የአልኮል መጠጥ ፍላጎት ነው፡፡በዚህም ሱስ ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የመጠጥ ፍላጎታቸው ምንምያህል በቤተሰባቸው፣ በሥራቸውና በጤናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳትየሚያመጣ ቢሆንም እንኳን ለማቆም ሲቸገሩ ይታያሉ፡፡ የአልኾልጥገኝነት በእያንዳዱ ግለሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ይገለጣል፡፡ ነገርግን ሁሉንም የአልኾል ሱሶች አንድ የሚያደርጓቸውን ተመሳሳይምልክቶችንም ማውጣት ይቻላል፡፡ እነዚህም፡- ለመጠጣት የሚያሳሳ ከፍተኛ ፍላጎት ፣ ምንምያህል ጉዳት ቢያደርስባቸውም መጠጥን በተመለከተ ራስንየመግታትም ሆነ የመቆጣጠር ችግር፣ አንዴ ከጀመሩ በኋላ ደግለማቆም ያለመቻል፣ እንዲሁም ደግሞ አልክኾል ከሰውነታቸው ጋር ከመለማመዱ የተነሣ በአንድ ጊዜ ለማቆም በሚምክሩበት ወይም በሚገደዱበትወቅት የሰውነት እንቅስቃሴ መስተጓጎል ሊከሰት ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሆድ መረበሽ፣ የሰውነት ላብ መጨመር የሰውነት መንቀጥቀጥ እናየፍርሃት ስት መረጠር ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የአልክሆል ጥገኝነት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣ እና በብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ላይ የተንሰራፋ በሽታ ነው፡፡ ብዙ ጥናቶችእንደሚያሳዩትም ከከፍተኛ ባለስልጣናት እስከ ቀን ሠራተኛ ባሉ ግለሰቦች ላይ ችግሩ ይከሰታል፡፡ የአልክሆል መጠጥ አጠቃቀም በየግለሰቡ ባህሪ፣የኑሮ ሁኔታ፣ የማህበረሰብ ባህልና የሐይማኖር ሁኔታዎች ይወሰናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች መጠጥን በጭራሽ አይጠጡም፡፡ ሌሎች ሰዎች ደግሞ እንደቋሚየመዝናኛ አማራጭ በመውሰድ አዘውትረው ይጠጣሉ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ በተለየ በአልክሆል ሱሰኝነት ሥር   የወደቁት ግን ውስጣቸውን ለማሳረፍ እናሳይጠጡ የሚከሰቱትን ችግሮች ለመሸሽ ዘወትር ይጠጣሉ፡፡ የአለም የጤና ድርጅት (WHO) እንዳስታወቀው ከሆነ በዓለም ላይ 76 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከአልክሆል ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎችይሰቃያሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል አሜሪካ ከጠቅላላው ህዝቧ 15% የሚሆነው ከአልክሆል ተጠቃሚነት በሚከሰት ጠንቅ ተጎጂ ነው፡፡   ሩሲያ ብንመለከት ደግሞ በሀገሪቱ ከሚከሰቱ ሞት መካከል 1/3 በቀጥታም ሆነ በተዘወዋሪ ከአልክሆል አወሳሰድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የዚህንምጉዳይ አሳሳቢነት የሀገሪቱ መንግስት በመረዳት የመጠጥ አምራች ፋብሪካዎችን፣ መሸጫ ቤቶችንና መሳሰሉትን በመዝጋት ያደረገው ሙከራ ፋይዳ ቢስከመሆኑም ባሻገር በተቃራኒው ህገወጥ የመጠጥ ዝውውር እንዲኖርና ሰዎችም የአልክሆል ጥገኝነታቸውን በድብቅ እንዲያጣቱፋ በር ከፋች ሆኗል፡፡  እንደጃፓን የመሳሰሉ የእስያ ሀገራትን ብንመለከት ደግሞ የመጠጥ ሱሰኝነት ችግር ከግለሰብ ደረጃ አልፎ ማህበረሰቡንም ከፍተኛ ሁኔታአቃውሶታል፡፡ በእነዚህ ሀገራት አልክሆል መጠጣት ከመዝናኛነት አልፎ ከሥራ ሂደትም ውስጥ እንደ አንዱ አካል ለመወሰድ በቅቷል፡፡ እንዲያውምበቢሮ ውስጥ ከሚደረጉት በላይ ትላልቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጣቸው በመጠጥመሸጫ ቤቶች ውስጥ ነው፡፡ የመጠጥ ግብዣ ሲቀርብለት ይለፈኝ ያለሠራተኛ ደግሞ የሥራ ዕድገትም አብሮ እንደሚያልፈው ነው መረጃዎች የሚያሳዩን፡፡   በሁሉም ዓይነት አልክሆል መጠጦች ውስጥ (Ethanol) የተሰኘው ኬሚካል (ንጥረ-ነገርየሚገኝ ሲሆን አልክሆልን በምንወስድበትም ጊዜ ይህ ንጥረ-ነገር አብሮ ወደ ሰውነታችንበመግባት ሆዳችንና አንጀታችን ላይ ያርፋል፡፡ በዚህም ስፍራ አልክሆል ከደማችን ጋርበመቀላቀል ወደመላው ሰውነታችንመ ይሰራጫል፡፡ ይህም አልክሆል የአንጎል አሠራር ላይ ተፅእኖ ያመጣል፡፡ በዚህ በሰውነታችን ውስጥየሚገባው የአልክሆል መጠጥ በጨመረ ቁጥር ተፅእኖውም ይበልጥ ይጨምራል፡፡ አልክሆልየተቀላቀለበት ደም በጨጓራ በኩል በሚያልፍበት ወቅት በጨጓራ ውስጥ ያሉ ኢንዛይሞችአልክሆሉን በመስበር ጉዳት እንዳያደርስ አድርጎ ወደ ቆሻሻት በመለወጥ ከሰውነታችንእንዲወገድ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን የአልክሆል ወደ ሰውነት ውስጥ መግባት በጨጓራችንኢንዛይም ተሰባብሮ ከሰውነታችን ከሚወገድበት ፍጥነት በላይ ከሆነ ለስካር ምክንያትይሆናል፡፡ አነስተኛ የሆነ አልክሆል ድካምንና ጭንቀትን ለማሰወገድ ፣ የምግብ ፍላጊት ለመጨመርናየህመም ስትን ለማስታገስ ጠቃሚ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የአልክሆል መጠን ግን የአስተሳሰብ ችሎታን ያዛባል፣ የራስ መተማመንን ከልክ ባለይበማድረግ፣ ፍርሃትንና የጥፋተኝነት ስሜትን ያስወግዳል፡፡ አንድ ሰው በመጠጥ ስካር ደረጃ በሚደርስበት ወቅት እስጨናቂና አሳፋሪ ስሜቶች በሙሉእየቀነሱ ይመጣሉ፡፡ ይበልጥ በጨመረ ቁጥር ደግሞ ንግግሩ በጣም ጮክ ያለ እና የተሳሰረ እየሆነ ይመጣል፣ የውሳኔ አቅም እና ሰውነትመገጣጠሚያዎች እንቅስቃሴ ይስተጓጎላል፡፡ በዚህም ከቀጠለ የሰውነት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የማቆም እና ራስን የመሳት ደረጃ ላይ ሊደርስይችላል፡፡ ጫን ካለ ደግሞ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡ አልክሆል ሱስነት ጉዳትን የሚያስከትለው ግለስቦች ብቻ ሳይሆን በዙሪው ያሉትን ግለሰቦችከዚያም ባለፈ ማህበረሰቡን ነው፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ የአልክሆል ጉዳት በተዘዋዋሪ መልኩ ሌሎች ማህበራዊ እና የጤና እክሎች መሰረት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ በኢኮኖሚውም ላይየራሱ የሆነ ተፅእኖ ያለው ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ በየዓመቱ 185 ሚሊዮን ዶላር ያህል ክስረትን እንዲሁም ያለዕድሜ ሞትን ያስከትላል፡፡ የጤና ባለሙያዎች የአልክሆል ሱሰኝነት ሂደትን በሦስት ክፍለው ይመለከቱታል እነዚህም፡- 1.      ማህበራዊ ጠጪነት፡- በዚህ ምድብ ውስጥ ብዙ ሰዎችን የምናገኝ ሲሆን፣ እነዚህም ሰዎች አልክሆል መጠጥን የሚወስዱት በተለያዩ አጋጣሚዎችሲሆን ማህበራዊ ስብስቦችን ፣ በዓላትንና ልዩ ዝግጅቶችን የተመረኮዘ ልምድ ነው ያላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ወስጥ የጠጨው ግለሰብ ዋና ዓላማ መጠጡላይ ሳይን ማህበራዊ ግንኙነቱ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ 2.      መደበኛ ጠጪነት፡- ከመጀመሪያ ቀጣዩ ደረጃ በማለፍ አልክሆል በተደጋጋሚ የመውሰድ ባህሪን ያዳብሩ ናቸው፡፡ እነዚህመ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜመዝናኛዎቻቸው መጠጥን ከመጠቀም ጋር የተያያዙ ይሆናሉ፡፡ በዚህም ወቅት አዘወትረው አልክሆል መጠጥ መውሰዳቸው የትኛውንም ያህልማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ተፅእኖ ቢያመጣባቸውም ከመጠጣት አይቆጠቡም፡፡ አዘውትረውም “መጠጥን ማቆም ከፈለግኩ እችላለሁ” ሲሉይደመጣሉ፣ ለማቆም ግን ፍላጎቱ የላቸውም፡፡ 3.      የመጠጥ ጥገኝነት፡- ከሁለተኛው ምድብ ከተመለከትናቸው ሰዎ መካከል ደግሞ የተወሰኑት በዚህ ልማዳቸው ሲቀጥሉ ወደ መጨረሻና በበሽታነትሊታይ በሚችለው የመጠጥ ጥገኝነት ሱስ ላይ ይወድቃሉ፡፡ እነዚህም ግለሰቦች የመጠጣት ባሪያቸው ከእነርሱ ቁጥጥር በላይ የሆነባቸውናየሚጠጡትም ለመዝናናት አሊያም  ፈልገውት ሳይሆን እንደ ግዴታ ነው፡፡ የአልክሆል ሱስ መነሻው ምንድነው? አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአልክሆል ሱሰኝነት በአንዳንድ በቤተሰብ አካለት ላይ በተደጋጋሚ ይታያል፡፡ ነገር ግን ይሄ መነሻው በዘርይሁን ተመሳሳይ በሆነ የመኖሪያ አካባቢ መኖር አልተረጋገጠም፡፡ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ወደ መጠጥ ሱስ ለመግባት ትልቅ ሚና አላቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በልጅነት ዕድሜ የጓደኛ ግፊት፣ የቤተሰብ አስረዳደግ፣ አልክሆልን በተመለከተ ማህበራዊና ባህላዊ አስተሳሰቦች ፣የኑሮ ጭንቀት እናአልካሆልን በአቅራቢያ አልክሆል ሱሰኝነት ጉዳት የሚያስከትለው ግለሰቡን ብቻ ሳይሆን በዙሪያው ያሉትን ግለሰቦች ከዚያም ባለፈ ማህበረሰቡንነው፡፡ ከእነዚህም በተጨማሪ የአልክሆል ጉዳት በተዘዋዋሪ መልኩ ሌሎች ማህራዊ እና የጤና እክሎች መሠረት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ በኢኮኖሚውምላይ የራሱ የሆነ ተፅእኖ ያለው  ሲሆን፣ በአሜሪካ ብቻ በየዓመቱ 185 ሚሊዮን ዶላር ያህል ክስረትን ያስከትላል የማግኘት አጋጣሚ ተጠቃሾ ናቸው፡፡ እንዲሁም ቀደም ባለ ዕድሜ አልክሆል መጠጣት ዘግይቶ ከመጀመሩ ይልቅ ለሱሰኝነት ያጋልጣል፡፡ ሌላውደግሞ የመጠጥ ሱስ ያለባቸው ግለሰቦች ከዚህ ባህሪያቸው የተነሣ በሰዎች ዘንድ የሚያገኙት ተቀባይነት ጥሩ ስለማይን ሱሰኝነታቸውን ሲክዱይታያሉ፡፡ በእርግጥ የተወሰነ መጠን ያለው የአልክሆል አጠቃቀም ለጤንነት ተስማሚ እና እንደ ለልብ ህመም የመሳሰሉትን ችግሮች  ለመከለካልቢጠቅምም ተከታታይ እና ከፍተኛ የሆነ የአልክሆል አወሣሰድ የሰውነታችንን የኬሚካል ስርዓት በእጅጉ ያዛባዋል፡፡ ከፍተኛ አልክሆል ተጠቃሚዎችየምግብ ፍላጎታቸው አነስተኛ ሲሆን ለሰውነታቸውም የሚያስፈልገውንም ካሎሪ ከአልክሆል መጠጥ ብቻ ያገኛሉ፡፡ አልካሆል ምንም ያህል ከፍተኛየሆነ ካሎሪ ይዘት ያለው ቢሆንም ሌሎች ከምግ ማገኘት ያለብንን የቫይታሚንና ሚኒራ የመሳሰሉትን ንጥረ ነገሮች ስለሚያካትት ለጉዳትእንደረጋለን፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የጨጓራ በሽታ ፣ የልብ አጥንት በአግባቡ አለመሥራት. ከፍተኛ የደም ግፊት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የአልክሆል ሱሰኛመሆን በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳተ መጠጥ ሲወስዱ ብቻ ሣይሆን ለማቆም በሚሞክሩበትም ጊዜ የተለያዩ ዓይነት ችግሮች (Withdrawal symptoms) አሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የድብርት ስሜት፣ ግራ የመጋባት፣ የእንቅልፍ ማጣት፣ አስፈሪ እሳቤአዊ ምስሎች እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በእርግዝና ውስጥ ያሉሴቶችን ስንመለከት ደግሞ ጉዳቱ ከእርሷ ባለፈ ህፃኑ ላይም ይታያል፡፡ በውልደት ወቅት ልጁ ላይ ግድፈት ከማስከተሉም በላይ ልጁ ላይ ግድፈትከማስከተሉም በላይ ልጁ ከተወለደ በኋላ ከባህሪ ችግር እስከ አዕምሮ ዘገምተኝነት ድረስ ከፍተኛ የጤና እክል ሊያጋጥመው ይችላል፡፡

Read Full Article

Archives