በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስገባት የማስታዎስ አቅምን ይጨምራል – ጥናት

1290

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስገባት የማስታዎስ አቅምን እንደሚጨምር አንድ ጥናት አመላክቷል።

በዚህም ማዕዛዎችን የመለየት እና የመረዳቱ ተግባር ነገሮችን ከመልመድ እና ከማስታዎስ ጋር እንደሚያያይዝም ነው በጥናቱ የተገለጸው።

ለዚህም የማስታዎስ አቅምን ለማሻሻል አየርን በአፍ ከመሳብ እና ከማስወጣት ይልቅ በአፍንጫ መለማመዱ ጠቃሚ ነው ተብሏል።

የቤተ ሙከራ አይጦች አየር የሚስቡት በአፋቸው ሳይሆን፥ በአፍንጫቸው መሆኑ ነው በዘገባው የተመላከተው።

ይህንን ሀሳብ መነሻ በማድረግም በስዊድን የካሮሊንስካ ኢኒስቲቲዩት ተመራማሪዎች ተጠኝዎች 12 ንጥረ ነገሮችን በሁለት መንገዶች እንዲለዩ በማድረግ በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስወጣት የማስታዎስ አቅምን እንደሚጨምር አረጋግጠዋል።

በዚህም ተጠኝዎቹ ነገሮችን እንዲሁ በማየት እና አየር በአፋቸው በመሳብ እና በማስወጣት ንጥረ ነገሮቸን እንዲያጠኑ ሲያደርጉ በሌላ በኩል ደግሞ አየር በአፍንጫቸው በማሳብ እና በማስወጣት ንጥረ ቅመሞቹን እንዲያጠኑ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም አየር በአፍንጫቸው በመሳብና በማስገባት ንጥረ ነገሮችን ያጠኑት ተጠኝዎች በአንጻሩ አየር በአፋቸው እየሳቡና እያስወጡ እንዲያጠኑ ከተደረጉት ተጠኝዎች በተሻለ ደረጃ ንጥረ ነገሮችን ለመለየት እና ለመረዳት መቻላቸው ነው የተገለጸው።

ተጠኝዎቹ አየር በሰርንአቸው ሲያስወጡና ሲያስገቡ ከሚረዱት ማዕዛ በተጨማሪ በዚሁ በኩል የሚያልፈው አየር ለአዕምሮ ስሜት እንደሚሰጥ ነው በጥናቱ የተጠቆመው።

ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እና ጥልቅ ምርምሮች መደረግ እንዳለባቸው ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ምንጭ፦ sciencedaily.com

Loading...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.