ቂጥኝ በግብረ-ስጋ ግንኙነት አማካኝነት ከሚመጡ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ የቂጥኝ ኢንፌክሽን ትሬፖኔማ ፓሊደም (Treponema Pallidum) ከተባለው የባክቴሪያ ዝርያ የሚመጣ ነው፡፡ ማንኛውም በወሲብ እንቅስቃሴ የተሰማራ ግለሰብ ቂጥኝ ሊይዘው እና ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ብዙ የወሲብ አጋር በኖረ ቁጥር በሽታውን የማግኘት እድል እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ቂጥኝ በተጨማሪም ለHIV ኢንፌክሽን የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋል፡፡
በየአመቱ 12 ሚሊዮን የሚሆኑ አዲስ የቂጥኝ ተጠቂዎች ይከሰታሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ከ90% በላይ የሚሆኑት በማደግ ላይ ባሉት አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡ በነዚህ አገራት ይህ በሽታ ለፅንስ ሞትና ከውልደት በኋላም ለሚፈጠር ሞት ዋነኛ መንስኤ በመሆን ቀጥሏል፡፡ በሰሜን አሜሪካ እና በምዕራብ አውሮፓ እምብዛም ተሰራጭቶ ይታያል፡፡ በነዚህ አገራት ደግሞ በግብረ-ሰዶማውያን ወንዶች ላይ እና በሀሺሽ (Cocaine) ተጠቃሚዎች ላይ እየተበራከተ መጥቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.