ከሜዲካል ጋዜጣ goodhealth

ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ተብለው ከሚጠቀሱ ህመሞች መካከል ካንሰር፣ ስትሮክ እና የልብ ህመም ተጠቃሽ ሲሆኑ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ከሆነም በአሁኑ ሰአት 60 የአለማችን ህዝቦች ህይወታቸው የሚያልፈው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች /ካንሰር፣ ስትሮክ፣ የልብ ህመም/ መሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ቀላል የሆኑ የአኗኗር ዘይቤዎች በመከተል አሰቀድሞ መከላከል የሚቻል ሲሆን አንዴ ከያዙ ግድ ከህሙማኑ ጋር ረዥም ጊዜ መቆየት ከመቻላቸው በላይ የበሽታዎቹ ምልክቶች ደግሞ ቀስ በቀስ የሚታይ ህሙማን ሀኪም ዘንድ እስከሚደርሱ ድረስ የከፋ የጤና ቀውስ ያስከትላል፡፡ የኛም እርስዎን ከነዚህ አደገኛ በሽታወች ይጠበቁ ዘንድ በባለሙያወች የሚሰጡ ምክሮችን እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል፡፡

  1. ጤናማ የአመጋገብ ሰርአት ይኑርዎ

ጤናማ አመጋገብ የሚባለው ለሰውነታችን ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የሚሰጡ የምግብ አይነቶችን መመገብ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የምግብ ምርጫዎን እንደ ፍራፍሬዎች፣ ከፍተኛ የስብ መጠን የሌላቸውን ምግቦች፤ እንዲሁም አሳዎችን በዛ በማድረግና በተቃራኒው ጥሬ ስጋን፣ ጣፋጭ ምግቦች እንዲሁም ጨውን መቀነስ፤

  1. የአካል ብቃት አንቅስቃሴ

ጤናችንን በአግባቡ ከምነጠብቅባቸው ተጠቃሽ ዘዴወች መካከል በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ እንቅስቃሴ የማድረግ አማራጮች ያሉት ሲሆን ለአብነትም የእግር ጉዞ፣ ውሃ ዋና ብሎም እግር ኳስ ተጠቃሽ ነው፡፡

  1. ክብደትዎን መቆጣጠር

ጥናቶች አንደሚያመላክቱት ከሆነ በአሁኑ ሰዓት አለማችንን እያሰጉ ብሎም እየተፈታተኑ ከሚገኙት የሰው ልጅ የጤና ቀውሶች በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ የሆነው ከመጠን በላይ የሚከሰት የውፍረት መጠን ነው፡፡ ለአብነት ያህል እንደ ስኳር፣ ደም ገፊት እና የልብ በሽታ የመሳሰሉት ተላላፊ ያልሆኑት በሽታወች የሚነሱባችው ምክንያቶች አንደ ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት የመጋለጥን እድል ይቀንሱ፡፡

  1. ሲጋራ አለማጨስ

ተላላፊ ላልሆኑ ህመሞች መከሰት ምክንያት ከሆኑ ነገሮች አንዱ ትንባሆ ነው፡፡ትንባሆ አብዛኛውን ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች መከሰትና መባባስ ከፍተኛ የሆነ አሰተዋፅፆ ያለው ሲሆን ለአብነትም  ትንባሆ ለልብ በሽታ፣ ለኩላሊት ብሎም ለካንሰር ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡ ስለሆነም ጤናማ አና ደስተኛ ሆነው ይኖሩ ዘንድ ትንባሆ ጢስ ካለበት ቦታ መራቅ ይኖርበታል፡፡

  1. አልኮል ይቀንሱ

እንደ ህክምና ባለሙያዎች ገለፃ ከሆነ መጠነኛ የሆነ የአልኮል መጠን  ለሰውነታችን አስፈላጊ ቢሆንም መጠኑ ካለፈ ግን የተለያዩ የጤና ቀውሶች ማስከተሉ አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ጤንነቶን በአግባቡ ይጠብቁ ዘንድ የሚዎስዱትን የአልኮል መጠን መቀነስ ግድ ይሎታል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.