ስለ አዕምሮ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች!!

 

Brainአዕምሮአችን የጠቅላላው ሰውነታችን የአስተዳደር ስፍራ ነው፡፡ ስለሆነም ሰውነታችን ለሚያከናውናቸው ማንኛውም ተግባራት አዕምሮአችን ይህ ቀረሽ የማይባል አስተዋፅኦ ማድረጉ አይቀሬ ነው፡፡ ታዲያ ይህ የሰውነታችን ማእከላዊ ክፍል እክል ያጋጠመው እንደሆነ በጤናችን ላይ ሊከሰት የሚችለው መታወክ መዘዙ እጅግ የከፋ ሊሆን እንደሚችል እሙን ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሳይንቲስቶች ስለ አዕምሮአችን እጅግ ብዙ የሆኑ ምርምሮችን ቢያደርጉም ሁሉንም የአዕምሮአችን አፈጣጠር እና ተግባር አውቀውታል ብሎ ለመደምደም ግን አይቻልም፡፡ እኛም አእምሮአችንን በተመለከተ የወጡ ሚስጥራት እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

  1. ሁለቱ የአዕምሮአችን ክፍሎች

በአዕምሮአችን ውስጥ ሁለት አይነት ክፍሎች ሲኖሩ አንደኛው ኋይት ማተር (white matter) በመባል የሚታወቅና 60 ከመቶ የሚሆነውን የአዕምሮአችን ክፍል የሚሸፍን ነው፡፡ ሁለተኛው ግሬይ ማተር (gray matter) በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

  1. ጭንቅላታችንና የደም ቧንቧ

በጭንቅላታችን ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ የደም ቧንቧዎች ተቀጣጥለው 150 ሺ ማይል የሚደርስ ርቀትን መሸፈን የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን ሁሉም የደም ቧንቧዎች በተቀላጠፈና በተስተካከለ መንገድ ስራቸውን በአግባቡ ይከውናሉ፡፡

  1. አዕምሮአችን ክብደት

የትልቅ ሰው አዕምሮ 1.5 ኪሎ ግራም ወይም 3 ፓውንድ የሚመዝን ሲሆን ከአጠቃላይ የሰውነት ክብደታችንም 2 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ነው፡፡ በተጨማሪም ከ20-30 በመቶ የሚሆነውን የሰውነታችን ጉልበት ይጠቀማል፡፡

  1. አዕምሮአችንና ውፍረት

የሰው ልጅ አእምሮ ከተቀረው የሰውነት አካላችን የበለጠ ወፍራሙ ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘው ሁለት ሦስተኛ የስብ መጠንም በአዕምሮአችን ውስጥ ይገኛል፡፡

  1. ቀኝና ግራ የአዕምሮአችን ክፍል

ጭንቅላታችን በሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈለ ሲሆን ይሄውም የቀኙ የጭንቅላታችን ክፍል እና የግራው የጭንቅላታችን ክፍል በመባል የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ተቀናጅተው በአንድነት ይሰራሉ፡፡

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.