ቀይ ሽንኩርት ከምግብ በተጨማሪ ጤናንም ያጣፍጣልCleaned-fresh-red-onionsበየእለቱ የምግባችን ማጣፈጫ ዋነኛ ግብአት አድርገን የምንጠቀመው ቀይ ሽንኩርትን ነው። ታዲያ አብዝተን የምንጠቀመውን ቀይ ሽንኩርት አብስለን ከመመገብ ይልቅ በጥሬው መጠቀም ለጤና እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ያስነብበናል ከጎግል ድረገፅ ያገኘነው መረጃ፡፡ በቀይ ሽንኩርት ውስጥ የምናገኛቸው ክዩርስቲን፣ አላሲን፣ ክሩሚየም የተባሉት ንጥረ ነገሮች ካንሰርን በመዋጋት ወደር የላቸውም። ይህ አትክልት ፈንገስንና ባክቴሪያንም ይከላከላል፡፡ ኢንሱሊንን በመቆጣጠር ከስኳር በሽታ እንደሚታደግ ፣ የደም ግፊትን እንደሚቆጣጠርና ክብደትን ለመቀነስም ጥሩ አማራጭ እንደሆነ ነው መረጃው ያስቀመጠው፡፡

ቀይ ሽንኩርት የሆድ ውስጥ ካንሰርን እንደሚከላከል የደረሱበት አጥኚዎቹ በቀን ግማሽ ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው መመገብ በሆድ ውስጥ ካንሰር የመጠቃት እድልን ሃምሳ በመቶ ይቀንሳል ይላሉ።

በቀይ ሽንኩርት ውስጥ የምናገኘው አላሲን የተባለው ንጥረነገር የመተንፈሻ አካል ጤንነትን በመጠበቅ፤ካንሰርን የመከላከልና ህመሙንም የመቆጣጠር፤ከፍተኛ የደም ግፊትን መቆጣጠር ዋንኛ ተግባሩ ሲሆን፤ በተጨማሪም ፈንገስን በመከላከል ከፎረፎርና ቆዳ ላይ ከሚወጡ ጭርት መሰል ነገሮች ይጠብቃል።

ከቀይ ሽንኩርት የምናገኛቸው ስምንት የጤና ገፀ በረከቶች ብሎ ድረገፁ ያስቀመጣቸውን ስንመለከት በጭማቂ መልክ፣ከሰላጣና ከሌሎች በጥሬያቸው ከሚበሉ ምግቦች ጋር በመቀላቀል መመገብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

1. ቀይ ሽንኩርት በውስጡ በያዘው የቫይታሚን ሲ ይዘት የሰውነትን ከበሽታ የመከላከል አቅም ያሳድጋል።
2. በውስጡ ክሩሚየም የተባለ ንጥረነገር አለው። ይህ ንጥረነገር የደም ግፊትንና ስኳርን ይቆጣጠራል።
3. ቀይ ሽንኩርት ገላን የማሳከክና የማቃጠል አይነት ባህሪ ያላቸውን አለርጂዎች ይቆጣጠራል
4. ቀይ ሽንኩርት ጥሬውን መመገብ ኮሊስትሮንን ከመቆጣጠሩ ባሻገር የጤናማ ልብ ባለቤት ያደርጋል።
5. ክዩርስቲን የተባለው በቀይ ሽንኩርት ውስጥ የምናገኘው ንጥረነገር ካንሰርን የመከላከል ሚና አለው።
6. በንብ በምንነደፍበት ጊዜ ትንሽ የቀይ ሽንኩርት ውሃ ብንቀባ ከስቃዩ እፎይታን እናገኛለን
7. ቀይ ሽንኩርት በየእለቱ መጠቀም ከጨጓራ አልሰር ይጠብቃል።
8. አረንጓዴ ጫፍ ያለው ለጋ ቀይ ሽንኩርት የቫይታሚን ኤ ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.