የመድሃኒት ኩባኒያዎች እና የመድሃኒት አቅርቦቱ

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

በተለይ በአዳጊ ሀገራት መድሀኒት የሚያስፈልጋቸው ብዙ ህሙማን ይገኛሉ። ለብዙ በሽተኞች አስፈላጊውን መድሃኒት ከማግኘት ጎን ለጎን ያላቸው ችግር መድሃኒቶች ውድ መሆናቸው ነው።

እንደ ሳኖፊ ያሉ የፈረንሳይ የመዳህኒት አምራች ኩባኒያዎች ለአዳጊ ሀገራት መድሀኒት በቅናሽ ዋጋ እንደሚያቀርቡ ይናገራሉ። ለአደጉት ሀገራት በአንፃሩ ተመሳሳዩን መድሀኒት በውድ ዋጋ እንደሚሸጡ የሳኖፊ መድሀኒት አምራች ኩባንያ ባልደረባ ፍራንኮስ ቦምፓር ያብራራሉ። « ክትባትን ብንወስድ ይህ በደንብ ስኬታማ ሲሆን ይስተዋላል። ተመሳሳይ ክትባት እንበል በዮናይትድ ስቴትስ እና በአውሮፓ 50 ዮሮ ድረስ ይሸጣል። ይህው መድሀኒት ደግሞ በአፍሪቃ 3 እና 4 ዮሮ ያወጣል። በአጠቃላይ ይህ አሰራር ስኬታማ የሆነው በመካከል እንደ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪቃ እና ታይላንድ ያሉ ሀገሮች ስላሉ ነው። እነሱ ደግሞ ከ10 እስከ 20 ዮሮ ይከፍላሉ። »

Titel: Medikament<br />
Bildbeschreibung: Rekordzahlen beim Medikamentenverbrauch im Iran. Vor 15 Jahren verbrauchte jede Iraner durchschnittlich 265 Einheiten. Bis ende 2012 steigt Medikamentverbrauch auf 452 Einheiten.<br />
Stichwörter: Iran, Medikament, Medizin, Gesundheit<br />
Quelle: ISNA<br />
Lizenz: Frei

ኢትዮጵያ ደሀ ከሚባሉት እና መድሃኒት በቅናሽ ዋጋ ከሚሸጥባት ሀገራት አንዷ ናት። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የመድሃኒት ዋጋ አቅርቦት፣ የማከፋፈል ሂደት እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜ በባለሙያዎች፤ በተጠቃሚ ( በሽተኛው) እና አከፋፋዮች መካከል ልዩነት አንዳንዴም ውዝግብ ሲፈጠር ይስተዋላል። መድሃኒት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው እንዴት ነው?መድሃኒቶች በሰዓቱ ለተጠቃሚዎች የማይደርሱበት ምክንያትስ? በኢትዮጵያ በአንድ የመድሃኒት አከፋፋይ የሚያገለግሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ባለሙያ ፤መድሃኒት ወደ ሀገሪቱ ለማስገባት መሟላት ያለበትን ዋና መስፈርት ገልፀውልናል።

እንዲሁም ወ/ሮ ናዲያ አብዱር ከፉር በአዲስ አበባ የሚገኝ «የአባድር ፋርማሲ» ባለቤት ናቸው። ለተጠቃሚ የሚያቀርቡትን መድሀኒት በቀጥታ ከውጭ ከአምራች ኩባንያዎች ሳይሆን ከአገር ውስጥ ነው የሚገዙት። ዋጋው ላይ ያለውን ትልቅ ልዩነት በምሳሌ አነፃፅረውልናል።

የሁሉንም አስተያየት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.