ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች

belly-fatቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

በጥያቄያችሁ መሠረት ቦርጭን ለማጥፋት የሚጠቅሙ ምክሮች እነሆ፡-

በሰውነታችን ላይ የስብ መከማቸት ለተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚዳርግ የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ፡

✔ ለልብ ሕመም
✔ ለስኳር ሕመም
✔ ለደም ግፊት መጨመር
✔ ለከፍተኛ ኮሌስትሮል

በአብዛኛው ስብ የሚከማችበት ቦታ ሆድ አካባቢ ሲሆን ይህም በአማርኛው ቦርጭ ብለን የምንጠራው ነው፡፡ ቦርጭን ሊያመጡ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

✔ ሊተኙ ሲሉ መመገብ
✔ ሰዓትን ጠብቆ አለመመገብ
✔ በሰውነታችን የሚገኙ ሆርሞኖች ለውጥ
✔ ጭንቀት
✔ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ
✔ በተፈጥሮ የሚመጣ

► ቦርጭን ለማጥፋት

✔ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ ብርጭቆ ሎሚ ያለው ውኃን ጠዋት መጠጣት

✔ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት፡- በውስጡ በያዘው ንጥረ ነገር ምክንያት አላስፈላጊ ስብን የማስወገድ አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

✔ ስብ የማቃጠል ችሎታ ያላቸው ምግቦችን መመገብ፡- እነዚህም እንደ ብሮክሊ፤ካሮት፤ጎመን ያሉ አትክልቶቸ፤ እንዲሁም እንደ ፖም፤ ሃብሃብ፤ ፓፓዬ ያሉ ፍራፍሬዎችን ማዘውተር

✔ ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖረን ማድረግ ፡- የተመጣጠነ እና አትክልት የበዛበት የምግብ ባሕልን ማዳበር

✔ በቀን ውስጥ የምንጠጣውን የውኃ መጠን መጨመር

✔ ቁርስን በሚገባ መመገብ፡- ይህን ማድረግ የረሃብ ስሜት እንዳይሰማንና ማስታገሻ የሚሆኑ ተጨማሪ ስኳር እና ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች እንዳንመገብ ያደርጋል፡፡

✔ የአካል ብቀት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ዋና መዋኘትን ማዘውተር በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የእግር መንገድ መሄድ

✔ እንቅልፍ አለማብዛት
✔ ጭንቀት ማስወገድ
✔ ለስላሳ መጠጦችን አለማዘውተር ናቸው፡፡

#ዶክተር_ሆነሊያት

25 COMMENTS

 1. What do you mean “Enkilf alemabzat”? getting enough sleep which is at least 6-7 hours sleep help not to gain belly fat comparing to people who are sleeping less than 5 or more than 8 hours. Sleep deprivation also cause to gain weight. Right?

  Thanks

 2. Number 2 is wrong. Scheduled diet can actually sabotage your weight. It’s recommended that you nibble on healthy food whenever hunger calls.
  Number 5. Inconclusive. Dietician actually recommend moderate fat intake. Fat is not the enemy; the culprit is carbohydrate.

 3. በቀላሉ የምናገኘውን ምግብ እኔ የፈተንኩት እና በጣም በርካታ ጊዚዎች ሙከራ ያደረግሁበት ነው ፡፡በጥናታቹ ያለተካተተበትም ምክንያት ያ ምግብ ፈረንጅ ስለማያውቀው ይሆናል፡፡የገብስ ቆሎ በእራት ለተከታታይ 7 ቀናት መመገብ ቦርጭ ያልነበረን እስኪመስል እንደሚያጠፋ በተግባር ተመልክቻሎህ፡፡ቁርጥ እየበሉ ስፖርት ቢሰሩ 30 ደቂቃ ይቅርና 24 ሳዓት ቢሮጡ ጥንካሬ ይጨምር እንደሆነ ነው እንጂ የሰውነት ክብደታችንንና ቦርጫችንን አይቀንስም፡፡
  ባንድ ወቅት ሩጫ እሞክር ነበረ ፡፡አብረውኝ ከሚሮቱ ሰወች መካከል አንዱ አመጋገቡም በጣም ጨመረ ስለሚደክመው ወተት ማር ሎውዝ እና ስጋ ነክ ምግቦች ይመገባል እናም በክብደቱላይ 7 ኪሎ ጨምሮ ተገኘ ፡፡ አብሮውን ከሚሮጡ የተወሰኑት ግን በምግብ መርሐግብር የጨመሩት ነገር ባለመኖሩ ክብደት እና ቦርጭ ቅነሳው ተሳክቶላቸዋል፡፡
  በተረፈ ግን ስለምትሰጡን ትምህርት በጣም አመሰግናሎህ፡፡

Leave a Reply to papino Cancel reply

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.