አዲስ   አበባ ፤ ነሐሴ 16/2005 (ዋኢማ) ¬- በአሜሪካ የተካሄደ  አንድ  ጥናት እንዳመላከተው    ሰዎች    የልባቸውን    ጤንነት ለመጠበቅ   ቁርስን  መመገብ  ማዘውተር  እንደሚያስፈልግ     ጠቁሟል ።

በ27 ሺ  ሰዎች  ላይ   የተካሄደው   ጥናት እንደሚያሳየው    ቁርስ  የማይመገቡ  ሰዎች   ለልብ  ችግር  የመጋለጥ   ዕድላቸው  እንደሚጨምር   አትቷል ።

በሃርቫርድ   ዩኒቨርስቲ   የህብረተሰብ  ጤና ትምህርት  ክፍል   ቡድን  እንዳስታወቀው   ቁርስን    አለመብላት  በሰውነት  ላይ    ተጨማሪ   ውጥረት  ይጨምራል።

የእንግሊዝ   የልብ  ፋውንዴሽን   በበኩሉ   ጥናቱ  ከ45  እስከ 82  ዕድሜ  ባላቸው  ወንዶች   ላይ  ለ16  ዓመታት መካሄዱን ገልጿል።
በተደረገው ጥናት መሰረትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ  ከ1ሺ 5 መቶ  በላይ  ሰዎችን  ለሞት  የሚዳርግ  የልብ ህመም   ተመዝግቧል ።

የጥናቱ  ውጤት  እንደሚያሳየው   ቁርስን  አዘውትረው   የማይመገቡ   ሰዎች በልብ  ችግር  የመጋለጥ   ዕድል     27 በመቶ  ነው።

ዶክተር  ሊህ  ካሊል  ለቢቢሲ  እንደገለጹት  ማንኛውም  ሰው   በጥዋት በተነሳ    በአንድ  ሰዓት   ውስጥ   ቁርስ  መመገብ ይኖርበታል።
በጥናቱ   መሠረት  በጥዋት   መመገብ    በጣም ወሳኝ  መሆኑንና ከምሳ   በፊት   ያለመመገብ    በጊዜ  ሂደት  ለሰውነት  ጉዳት   ከማስከተሉም   በተጨማሪ  ለከፍተኛ   የደም ግፊት፣  ከመጠን  ላለፈ  ክብደትና  ለስኳር    በሽታ  የሚያጋልጥ   መሆኑም ታውቋል።

በጥናቱ   የተካተቱት    ከ  45  ዓመት   በላይ  የሆኑ  ወንዶች   ብቻ  በመሆናቸው   ይበልጥ   ቁርስን  መመገብ    በልብ  ጤና   ላይ   ምን  ያህል  ተመሳሳይ     ጉዳት  እንደሚያስከትል  ለማረጋገጥ  በሌሎች  የዕድሜ   ክልል   ላይ    ጥናት  ማድረግ  እንደሚያስፈልግም ፋውንዴሽኑ ገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.