የሸንቃጣ ሰዎች 20 ሚስጥር

ከጤና ይስጥልኝ የጤና መፅሔት የተወሰደ

 1. የሚጠጣ ውሃ ከእጃችሁ አትጡ

slim_fatበማንኛውም ጊዜ ውሃችሁን ከቦርሳችሁ አውጥታችሁ መጎንጨት፤ ከጠማችሁም ጥማችሁን እስክትቆርጡ መጠጣት ጥሩ ነው፡፡ ውሃ ብዙ አማራጭ ያለው መጠጥ ነው፡፡ ባዶውን ከጉሮሮአችሁ አልወርድ ብሎ አስቸግሯችሁ እንደሆነ ሎሚ ወይም የሎሚ ጁስ ደባልቃችሁ ልትጠጡ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቅርበት የምታገኙ ከሆነ ቫይታሚን ውሃ መጠጣትም ሌላናው አማራጭ ነው፡፡ ንፁህና ኩልል ያለን ውሃ የመሰለ የለም፡፡

 1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደ አንድ አስደሳች ድርጊት አንጅ እንደ አንድ መወጣት ያለባችሁ እለታዊ ግዴታ አትመልከቱት፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰውነታችሁ እና ሕይወታችሁ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ለውጥ አስቡ፡፡ በመቀጠል ምን መብላት እንዳለባችሁ ሳይሆን ምን አይነት እንቅስቃሴ ልታደርጉ እንደምትችሉ አስቡ፡፡

 1. የተመጣጠነ ምግብ

አንዳንድ ምግቦች ምንም እንኳ ከስብ ነፃ ሆነው በአንፃሩ የፕሮቲን ይዘታቸው ከፍ ያለ ቢሆንም ዋና የካሎሪ ምንጭ ስለሚሆኑ ክብደት እንድትጨምሩ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ የምትመገቡት ምንም ያህል የተመጣጠነ ቢሆንም ዞሮ ዞሮ ተጨማሪ ካሎሪ ማለት ተጨማሪ ክብደት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

 1. የካፌይን አጠቃቀምን ገደብ ማበጀት

ከሲጃራ በተዘዋዋሪ የሚመጣ ጭስ እንኳን ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

 1. አጭር ጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ዋናው ትኩረት መሆን ያለበት የዕለት ተዕለት ተግባርን ከግቡ ማረስ ነው፡፡

 1.  በቀን ምን ያህል እንደምንመገብ መለየት

በቀን ውስጥ በትክክል ምን ያህል እንደምንመገብ ለመለየት የሚያስችል ዝርዝር መረጃ በአነስተኛ ማስታወሻ ላይ ማስፈር፡፡ በየካፌው የምትመገቡትን ችፕስ፤ ልጆች መክሰስ ሲበሉ አብራችሁ የምትጎራርሱትን ነገር ሁሉ አካቶ መመገቡ አስፈላጊ ነው፡፡

 1. በሳምንት አንድ ቀን እንዳሻ መሆን

ሺ ዓመት አይኖር፡፡ በእርግጥ መዝናናቱ  ሳምንቱን ሙሉ እንዳይሆን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡

 1. ለሌሎች ጤንነት ጥንቃቄ አድርጉ

በዙሪያችሁ የሚገኙ ሌሎች ሰዎችም ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ አብሯችሁ ስፖርት የሚሰራ ጓደኛ ቢኖራችሁ መልካም ነው፡፡ ሌሎችን በቅርበት የምታውቋቸውን ሰዎች ስፖርት እንዲሰሩ አበረታቷቸው፡፡ ጧት ተነስቶ የእግር ጉዞ ማድረግ ወይም ዱብ ዱብ ማለት የሚወድ ጎረቤት ካላችሁ እናንተም መቀላቀል ትችሉ እንደሆነ ጠይቁ፡፡

 1. መሰልቸትን ታገሉ

መሰልቸት እንዳይገጥማችሁ በየጊዜው የምትሰሩትን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አይነት ቀያይሩ፡፡ ኤሮቢክስ፤ ብስክሌት መንዳት፤ ዋና፤ ዳንስ፤ የእግር ጉዞ ማድረግ፤ ወዘተ እንደሁኔታው እየለዋወጣችሁ ልትሰሯቸው የምትችሉት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ናቸው፡፡

 1. የጤና ነክ ህትመቶችን መከታል

የጤናና አካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ መፅሔትና ጋዜጦችን መከታተል ጠቃሚ ነው፡፡

 1. አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ወጪ አለመሰሰት

አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ ንብረቶች ላይ ገንዘባችሁን አውጡ፡፡ ለስፖር ምቹ የሆነ ጫማ፤ ቱታ፤ ሙዚቃ ወዘተ

 1. ጠኋትና ማታ ለመስራት ማቀድ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘውትሮ ጠኋትና ማታ መስራት

 1. ለራስ ምርጥ እንደሆኑ ማሰብ

ራስን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር

 1. አመጋብ

አመጋገባችሁ ያልተመጣጠነ ከሆነ የተመጣጠነ አድርጉ፡፡ ቫይታሚንና ሜኔራል በየቀኑ መውሰድን ማረጋገጥ፡፡

 1. ክብደት

ክብደትን በየጊዜው መለካት

 1. ዕቅድ

በየጊዜው በማግስቱ የሚሰሩትን ማቀድ

 1. ክብደት መቀነስ

ክብደት መቀነስ ከሚለው ክልል ወጥቶ ሁለገብ አካላዊ ብቃት ወደሚለው መሸጋገር

 1. የአመጋገብ ልምድ

ያለማቋረጥ ልትመገቡት የሚገባ የአመጋገብ ልምድ ይኑራችሁ

 1. ዕንቅልፍ

በቂ እንቅልፍ ተኙ፡፡ ስፖርት የሚሰሩ ሰዎች በጊዜ የመተኛትና በቂ እንቅልፍ የማግኘት ልምድ አላቸው፡፡

 1. መጠጥ

የአልኮል መጠጥ አወሳሰዳድን የመወሰን ልምድ ማዳበር ሸንቃጣ የሚያደርጉ ምስጢሮች ናቸው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

6 COMMENTS

  • በአሁኑ ሰዓት 36 ዓመተ ሆኖኛል ቁመቴ 1.80 ነዉ ነገር ግን ክበደቴ ከ54 ኪ.ግ በልጦ አያዉቅም ፡፡ይህ ሁኔታ ደግሞ በተደጋጋሚ ያሳስበኝ ስለነበር ክደቴን ለመጨመር ካለኝ ፍላጎት አንጣር ድረገፆችን ስመለከት ዉፍረት ወይም ክብደት ለመጨመር MACAROOT PILLS ወደር የማይገኝለት ፍቱን እንደሆነ ተገንዝቢያለሁ ፡፡ነገርግን ይህ መዳኒት ባፈላልግ ላገኘዉ ስላልቻልሁ የሚገኝበትን ብትነግሩኝ ዉለታ ከፋይ ነኝ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.