ሁለገቡ የዱባ ፍሬ

በተደጋጋሚ ጥናት ከሚደረግባቸው ለምግብነት ከሚውሉ ነገሮች አንዱ የዱባ ፍሬ ነው፡፡ በኦሜጋ 3 ፋቲ አሲዶች የበለፀገ መሆኑም ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል፡፡

                ለአጥንት ጥንካሬ ይሰጣል

የዚንክ እጥረት የሚታይባቸው ሰዎች የዱባ ፍሬ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ፍሬው በቂ ዚንክ ይሰጣል፡፡ ሩብ ኩባያ የዱባ ፍሬ ከእለታዊ ፍላጎት 17 ከመቶ ያህሉን ይሰጠናል፡፡

               ጎጂ ኮሌስትሮልን ይቀንሳል

pumpkin- eeds  በ509 ሰዎች ላይ የተካሄዱ 16 ቀደምት ጥናቶች ላይ ምርምር ያደረገ የቅርብ ጊዜ ጥናት የዱባ ፍሬ ውስጥ ያለው phytosterols የተሰኘ ንጥረ ነገር ጎጂ ኮሌስትሮል የሚቀንስና ጠቃሚው እንዲጨምር የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡ phytosterols በአንጀት ውስጥ የኮሌስትሮል ክምችት እንዳይኖር በማድረግ በደም ውስጥ ሊገኝ የሚችለውን ጎጂ ኮሌስትሮል ይቀንሳል፡፡ በ2011 ለንባብ የበቃ አንድ ጥናት እንደ ዱባ ፍሬ ያለ በ phytosterols የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ተፈጥሯዊ ኮሌስትሮል ማስወገጃ ዘዴ ከመሆኑም በላይ በልብ በሽታዎች የመጠቃት እድልንም ይቀንሳል ብሏል፡፡

             የአንጀት ጥገኛ ተውሳኮችን ያስወግዳል

በሃገራችን የዱባ ፍሬ ሲባል ትዝ የሚለን ጥገኛ ተውሳኮችን በማስወገዱ ነው፡፡ የበርካታ መቶ ዓመታት እድሜ የቻይና ባህላዊ ህክምና እንደሚገልፀው የአንጀት ጥገኛ ትላትሎችን የዱባ ፍሬ፣ ሽንኩርትና የአኩሪ አተር ወተት በመጠቀም ማስወገድ ይቻላል፡፡ ሦስት ሾርባ ማንኪያ የዱባ ፍሬ፣ አንድ አነስ ያለ ሽንኩርት ግማሹን፣ ግማሽ ኩባያ የአከሪ አተር ወተትና አንድ ማንኪያ ማር ቀላቅሎ በመቀላቀያ (blender) መፍጨት ያስፈልጋል፡፡ ይህን ውህድ በቀን ሦስት ጊዜ ለተከታታይ ሦስት ቀናት መውሰድ ይገባል፡፡  አስተማማኝ በመሆኑም ህፃናትና ነፍሰጡሮች ሳይቀሩ ሊጠቀሙት ይችላሉ፡፡

             የኩላሊት ጠጠርን ያስወግዳል

    በቅርቡ በየተደረጉ ሁለት ጥናቶች በስፋት የሚከሰተውን calcium oxalate የተሰኘ የኩላሊት ጠጠር እንዳከሰት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ በቀን ከ5-10 ግራም ብቻ በመመገብ የኩላሊት ጠጠሮችን መከላከል ይቻላል፡፡

              ስንፈተ ወሲብን በዱባ ፍሬ

የዱባ ፍሬ ወሲባዊ መነቃቃትን የሚፈጥሩ ሆርሞኖች እንዲመረቱ የሚያበረታቱ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ ፍሬው ከፍተኛ ሊባል በሚችል መጠን ዚንክ፣ ማግኒዝየም፣አይረን፣ ፎስፈረስ፣ካልሲም፣ ቫይታሚን ኤና ቢን ይዟል፡፡ በየእለቱ የዱባ ፍሬን በመመገብ ስንፈተ ወሲብን መከላከል እንደሚቻል የሚገልፁ ማስረጃዎች አሉ፡፡ በቡልጋርያ፣ሃንጋሪ፣ ቱርክና ዩክሬን የሚገኙ ማህበረሰቦች በየእለቱ የዱባ ፍሬን የሚመገቡ ሲሆን ፍሬው የተለያዩ የፕሮስቴት ችግሮችን ከመፍታቱም  በላይ ስንፈተ ወሲብን አስወግዶላቸዋል፡፡

ካንሰርን ይዋጋል

በቅርቡ Current pharmaceutical design ላይ ለንባብ የበቃ ጥናት cucurbitaceous የተሰኘ በዱባ ፍሬ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኝ ንጥረ ነገር ካሰርን በመዋጋት ረገድ ጠቀሜታ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁሟል፡፡ እነዚህን መሳይ ንጥረ ነገሮች የተለያዩ አይነት የካንሰር ሴሎችን ከማጥፋታቸው በላይ ከፍተኛ የህመም ስሜት የማስወገድ አቅም እንዳላቸው በቫለንሲያ ዩንቨርስቲ ጥናት ያደርጉ ሳይንቲስቶች ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ጥናታቸውን ይፋ ያደረጉ የጀርመን ሳይንቲስቶች የዱባ ፍሬ ያረጡ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን በ23 በመቶ እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡

ጥናቱ ካንሰር ያለባቸውን 2884 ሴቶችና 5509 ጤናማ ሴቶችን ያካተተ ሲሆን በውጤቱም የዱባ ፍሬ ብቻ ሳይሆን ሱፍና አኩሪ አተርም በካንሰር የመያዝ እድልን እንደሚቀንሱ አስረድቷል፡፡

             የፕሮስቴት ጤንነት ያሳድጋል

የዱባ ፍሬ ለወንዶች የሚሰጠው ጥቅምም አለ፡፡ ከፍሬው የሚገኘው ዘይት የፕሮስቴትን ጤንነት ይጠብቃል፡፡ international journal of oncology ላይ የወጣ አንድ ጥናት የዱባ ፍሬ መመገብ የፕሮስቴት ካንሰር እንዳያድግና እንዳይሰራጭ ይረዳል ብሏል፡፡

         በስኳር በሽታ የመጠቃት እድልን ይቀንሳል

ምርጥ ምግቦች ከሚባሉት የሚመደበውን የዱባ ፍሬ በአይረን እና የልብ ወዳጅ በሆነው unsaturated fats የበለፀገ ስለሆነ የስኳር ህሙማን እንዲያዘወትሩት በዘርፉ ምርምር ያካሄዱ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

በእንስሳት ላይ የተደረጉ ጥናቶች በፍሬው ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ኢንሱሊንን በመቆጣጠር እንዲሁም በስኳር ህመም የመያዝ እድልን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ መሆኑ የታየ ሲሆን የስኳር ህመም ያለባቸው የላብራቶሪ አይጦችም ጤናቸው መሻሻልን አሳይቷል፡፡      

ጥናቱን ያካሄዱት ቻይና ሳይንቲስቶች በዱባ ፍሬ ውስጥየሚገኙት ንጥረ ነገረቶች በአዲስ አይነት ፀረ- ስኳር ህክምና ለማስጀመር ያስችላሉ ብለዋል፡፡

           ጭንቀትና ድብርትን ያቃልላል

ፍሬው ለሰውነትብ ብቻ ሣይሆን ለአእምሮ ጠየንንት ሰላም ይሰጣል፡፡በጉዳዩላይ የተካሄደ አንድ ጥናት የዱባ ፍሬ ከግልኮስ ጋር የተወሰደ ጭንቀትንና ድብርትን ያስወግዳል ያለ ሲሆን ሌላ የቅርብ ጊዜ ጥናት ደግሞ በወሲብ ፍላጎትም ይጨምራል ብለዋ፡፡ Canadian journal of physiology and pharmacology የተሰኘ አሚኖ አሲድ ፍሬው ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚገኝ ሲሆን ጭንቀትን ያባርራል ብለዋል፡፡

           

             በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል

ፈሬውን አዘውትሮ መመገብ በርካታ ጥቅሞችን ያላቸው ቫይታሚን ኢ በቀላሉ ለማኘት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ቫይታሚን ኢ ሴቶች በፍራዲካልሶች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ከማድረጉም በላይ የበሽታ መከላከል አቅምን ያሳድጋል፡፡እንዲሁም የሰውነታችንን ተላላፊ በሽታወችን የመቋቋም አቅምን ይጨምራል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.