የሆድ ህመም/ ቁርጠት

ለሆድ ህመም/ ቁርጠት አብዛኛውን ጊዜ መነሻ የሚሆኑ ነገሮች የወር አበባ መምጣት፣ ቫይረሶችና የምግብ መመረዝ ናቸው፡፡ የተበላሹ ወይም የሚሸቱ ምግቦችን በማስወገድ፣ መፀዳጃ ቤት ገብተን ስንወጣ እጃችንን በውሃና ሳሙና በመታጠብ፣ እንዲሁም እንደ ሥጋ አና አሳ ያሉ የምግብ ዓይነቶችን በደንብ እንዲጠበሱ በማድረግ የሆድ ህመምን ብሎም ተቅማጥን መከላከል እንችላለን፡፡

???????????????????????????????????????????????????????????????????????????????????የሆድ ህመም/ ቁርጠር በሚይዝዎት ጊዜ የሚከተሉትን በማድረግ እራስዎን ማከም ይችላሉ፡፡

 • ሙቅ ውሃ መያዣ ላስቲክ ውስጥ ሙቅ ውሃ አድርገው ሆድዎ ላይ ይያዙ
 • ፓናዶልና የመሳሰሉትን ፓራሲታሞል መድኃኒቶች በአቅራቢያዎ ካለ የመድኃኒት መደብር (ፋርማሲ) ገዝተው ይውሰዱ፡፡

በቫይረስ ምክንያት የሆድ ህመሙ ከተከሰተ ትውከት፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የጡንቻ ህመም፣ እና የመገጣጠሚያ ቦታዎች ህመም ሊከሰትብዎት ይችላል፡፡ እነዚህ ህመሞች አብዛኛውን ጊዜ 24 ሰዓት ያህል ሊቆዩ ይችላሉ፡፡

 • ከሆድ ህመም ጋር ተያይዞ ተቅማጥ ካለብዎት ተቅማጡ በጀመረዎት ከ 2 እስከ 3 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት መድኃኒት አይውሰዱ፡፡ ተቅማጡ ቫይረሱን እያስወገደ ሊሆን ይችላል፡፡
 • በደንብ ይረፉ
 • እንደ ፍራፍሬ ጭማቂ፣ ሙዝ፣ ሾርባ እና የመሳሰሉትን ቀለል ያሉ ምግቦች ይመገቡ፡፡
 • ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን፣ ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን፣ ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን፣ እንደቡና እና ለስላሳ ያሉ ካፌን የበዛባቸው መጠጦችን፣ አልኮልና የትምባሆ ውጤቶችን ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡

የምግብ መመረዝ

ማጥወልወል፣ ማስታወክ፣ ማስቀመጥ፣ ትኩሳት እና የሰውነት መድረቅ (ውሃ ማጠር) በምግብ መመረዝ ወቅት ሊያጋጥም ይችላል፡፡

 • ከሆድ ህመም ጋር ተያይዞ ተቅማጥ ካለብዎት፤ ተቅማጡ በጀመረዎት ከ2 እስከ 3 ሰዓት ድረስ ምንም አይነት መድኃኒት ተቅማጡን ለማስቆም ብለው አይውሰዱ፡፡ ተቅማጡ ቫይረሱን እያስወገደው ሊሆን ይችላል፡፡
 • ከተወሰነ ሰዓት በኋላም በአካባቢዎ ከሚገኝ የመድኃኒት መደብር (ፋርማሲ) የተቅማጥ ማስቆሚያ መድሃኒት ገዝተው ይጠቀሙ፡፡
 • በተቅማጥ ምክንያት ያጡትን የሰውነት ፈሳሽ ብዙ ውሃ ወይም ጭማቂ በመጠጣት መተካትዎን አይርሱ፡፡
 • ምግብ መብላት ካሰኝዎትም እንደ ዳቦ፣ ሙዝ እና ሩዝ ያሉትን ምግቦች ይመገቡ፤ ተቅማጥን ለማስቆም ያግዛሉና፡፡ ብዙ ቅባትነት ያላቸው ወይም ከባድ ምግቦችን አይመገቡ፡፡ የወተት ተዋፅኦዎችን እና ጥሬ አትክልት/ ፍራፍሬንም ቁርጠቱና ተቅማጡ ባለበት ሰዓት አይውሰዱ፡፡
 • በደንብ እረፍት ያድርጉ፡፡

የሚከተሉት ነገሮች ከተከሰቱ ግን ወደ ሀኪም ቤት በመሄድ የሕክምና እርዳታ ያግኙ፡፡

 • በጣም አጣዳፊ የሆነ ተቅማጥ ከቁርጠት ጋር ተጣምሮ ከተከሰተ ወይም የሰውነትዎ የሙቀት መጠን ከ38.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ከደረሰ
 • ሆድዎ ላይ ያለው ህመም ከእምብርትዎ በታች በቀኝ ክፍል ከሆነ
 • ያዝ ለቀቅ ከሚያደርግ የሆድ ቁርጠት ጋር አብሮ መንቀጥቀጥ፣ ደካማ ወይም ፈጣን የልብ ምት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ የደረት ህመም፣ የአፍ መድረቅ፣ ማስታወክ፣ የሆድ ማበጥ፣ የጋዝ ችግር (ከባድ ፈስና ግሳት)፣ መድከም፣ ጥቁር ወይም ደም ያለው ሰገራ፣ ትኩሳት ወይም መጥፎ የአፍ ጠረን ከተከሰተ
 • የሆድ ቁርጠትዎ ከ2-3 ቀን በላይ እራስዎን ቢያክሙም ካልጠፋ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.