የታወቁ ዋና ዋና የካንሠር ህመም ምልክቶች የትኞቹ ናቸው፣

የካንሠርን ህመም የተለያዩ ዓይነት ብዛት ያላቸው ምልክቶችን የሚያስከትል ቢሆንም ቀጥሎ የተመለከቱት ይገኙበታል ፡፡
symptoms-of-pancreatic-cancer-hpthvqfv1. በጡት ወይም በተለያዩ የሰውነታች አካል ላይ ጠጣር ወይም ልል የሆነ ምልክት (Thickening) መታየት፣
2. በሰውነታችን ላይ አዲስ አልፎ  አልፎ የቀለሙን ዓይነት የሚለየውን ነጠብጣብ መታየት፣
3. በቀላሉ የማይድን የጉሮሮ ህመም፣
4. ሳል አልፎ  አልፎ ደረቅ ሳል በተከታታይ መከሰት፣
5. በአንጀትና ኩላሊት ላይ የህመም ስሜት መከሰት፣
6. የምግብ መፈጨት ችግር በተደጋጋሚ መከሰትና ምግብ አኝኮ ለመዋጥ መቸገር፣
7. በቀላሉ ለመግለፅ አስቸጋሪ የሆነ የክብደት መቀነስ፣
8. በተለያዩ የአካላችን ክፍሎች ያልተለመደ ደም መፍሰስ መከሰት፣
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትም ሆነ ሌሎች አንዳቸውም ሆነ ከአንድ በላይ ምልክቶች ሲያጋጥም የካንሠር ህመም ተከስቷል ብሎ መደምደም አይቻልም ፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ህመሞች የእነዚህን ዓይነት ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉና ፡፡ እነዚህን ዓይነት ምልክት እንደታዩ ፈጥኖ አግባብነት ካለው ሐኪም መቅረብ ያስፈልጋል ፡፡ ሐኪሙ የህመሙን ዓይነት በውል ለይቶ ለማወቅ የተለያዩ ዓይነት የምርመራ ዓይነቶችን ያካሂዳል ፡፡ ከተለያዩ ዓይነት ምርመራዎች መካከል ባዮኘሲ (Biopsy) ህመሙ ካንሠር መሆንና አለመሆኑን መለያ ዘዴ ነው ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.