ቁርስና ምሳ ብቻ መመገብ ለስኳር ህመም ቁጥጥር ‘ውጤታማ’ ነው

diabetics_5በቀን ውስጥ በጥቂት በጥቂቱ ብዙ ጊዜ ወይም አሁንም አሁንም ከመመገብ ይልቅ ምግቡን በርከት አድርጎ ቁርስና ምሳ ብቻ መብላት ሁለተኛውን አይነት የስኳር ህመም (type 2 diabetes) ለመቆጣጠር ይበልጥ ውጤታማ መሆኑን ነው ተመራማሪወች ያመለከቱት::

የፕራግ ተመራማሪዎች በሁለት ቡድን የተከፈሉ 27 ሰወችን ተመሳሳይና እኩል የንጥረ ነገር መጠን ያለው  ምግብ እያዘጋጁ አንዱ ቡድን በቀን ሁለት ጊዜ :ሌላው  ደግሞ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ እንዲመገቡ አደረጉ::

በዚህም መሰረት በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ የተመገቡት 6 ጊዜ ከተመገቡት ጋር ሲነጻጸሩ ክብደታቸውን በመቀነስና የስኳር መጠናቸውን በማውረድ ውጤታማ ሆኑ ይላሉ ተመራማሪወቹ::

ስለዚህ በቀን በጥቂት በጥቂቱ ብዙ ጊዜ ከመመገብ ይልቅ ምግቡን በርከት አድርጎ በየእለቱ ሁለት ጊዜ ወይም ቁርስና ምሳ ብቻ መብላት ለሁለተኛው አይነት ስኳር ህመም ቁጥጥር የበለጠ ውጤት አለው::

ምንጭ :-ቢቢሲ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.