ዋናው ጤና

(Low Back Pain Overview)

Low-Back-Pain1ጀርባ ከአጥንቶች፣ ጅማቶች፣ ጡንቻዎችና የተለያዩ ህዋሳት የተዋቀረ በኋለኛው የሰውነታችን ክፍል በአንገት እና ፐልቪስ (pelvis) መካከል የሚገኝ የሰውነታችን አካል ነው፡፡ በጀርባችን መሐል የሚገኘው የጀረባችን አጥንት የሰውነታችንን ክብደት ከመሸከም ባሻገር ህብለ-ሰረሰራችንን (spinal cord) አቅፎና ደግፎ ይይዛል፡፡ የጀርባ አትንታችንም እርስ በርሳቸው በተደራረቡ እና በመካከላቸው ክብ ቀዳዳ ባላቸው ሰላሳ አጥንቶች (vertebrae) የተገነባ ነው፡፡ በእነዚህ አጥንቶች መካከል የሚገኝ ለስለስ ያለ ዲስክ (Intervertebral disk) ለእንቅስቃሴ፣ ግፊትን ለመቋቋምና የሰበቃ ሃይልን (friction) ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡ ሊጋመንት (ligament) እና ቴንደን (tendon) ተብለው የሚጠሩ ህዋሳትም የጀርባ አጥንቶቻችንን እርስበርስ እንዲሁም ከጡንቻዎቻችን ጋር አጥብቀው በማያያዝ ቦታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ይረዳሉ፡፡

የጀርባችን አጥንት አራት ክፍሎች አሉት፡፡ ከላይ ወደታችም በሚከተለው ቅደም ተከተል ቀርበዋል፡፡

  • ሰባት የአንገት አጥንቶች (Cervical vertebrae labeled C1-C7)

  • አስራ ሁለት የላይኛው ጀርባ አጥንቶች (Thoracic vertebrae labeled T1-T12)

  • አምስት የታችኛው ጀርባ (ወገብ) አጥንቶች (Lumbar vertebrae labeled L1-L5)

  • የታችኛው ጀርባ የተዋሀዱ አጥንቶች (Sacrum and coccyx fused together)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here