በአሁኑ ጊዜ ብዙ የሰነ-ልቦና ጠበብት እንደሚያምኑት በህጻናት አስተዳደግ እና ባህሪ መካከል ቀጥተኛ ቁርኝት አለ። ከባህሪም ባሻገር የሚያስፈልጋቸውን በጊዜው ማድረግ ለአካላዊ ጤንነታቸውም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

ልጆች ሽንትና ሰገራቸውን መቆጣጠር የሚጀምሩት ከ12-18 ባሉት ወራት ውስጥ ነው። ብዙ ህፃናት ፖፖ የሚጀምሩት ከአንድ እስከ ሶስት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ ነው።

ልጄን መግረፍ ይጠቅመዋል?

scoldingህፃናት ቁጡ ባህሪ፤ ማለትም መናከስ፣ መማታት፣ ወይም መቧጨር በሚታይባቸው ጊዜ ክትትል እና በሚያሣዩት ባህሪ ላይ እርምት ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። በሀገራችን ውስጥ እንደሚዘወተረው፣ ህፃናትን ላጠፉት ጥፋት በሙሉ መግረፍ በወላጆች ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩ ያደርጋቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የሚያደርጉትን ነገር በሙሉ በፍራቻ እንጂ በማገናዘብ እንዳይሠሩ ያግዳቸዋል። በዚህም ምክንያት፣ ወላጆች በአካባቢው በማይኖሩ ጊዜ ተመሳሳይ ስህተት ሲፈጽሙ ይታያሉ። በተጨማሪም ህፃናት ላይ መበሳጨት እና መጮህ እነሱም በዛው መልኩ ተመሳሳይ የመቆጣት ባህሪ እንዲያበጁ ያደርጋቸዋል።

የልጅዎ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት በቤትዎ ውስጥ ላለው ነዋሪ ሁሉ ሰላም ይሰጣል። የልጅ እንቅልፍ ማግኘት ያለውን ጠቀሜታ አዲስ ቤት የመሰረቱ ወላጆች ከምንም በላይ ይረዱታል። ህፃናት እድገታቸው በጨመረ ቁጥር የእንቅልፍ ሰዓታቸውን እያስተካከሉ ይሄዳሉ። ቅሬታ ሲኖራችውም ከማልቀስ በተጨማሪ ላለመተኛት ጥረት ያደርጋሉ። ከእንቅልፋቸው በመነሳትም ውሀ ሊጠይቁ ይችላሉ።

ልጆች በተወለዱ በቀናት እድሜ ውስጥ ፀሃይ መሞቅ መጀመር አለባቸው። ይህም ለአካላዊ ጤንነታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው።

ምንጭ — አዲስ ጤና

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.