የአመት በዓል ጤናና ደህንነት ጥንቃቄ ምክሮች

new-yearየአመት በዓል ሲመጣ ከሚወዷቸዉ ጋር ለማሳለፍ፣ለመደሰትና ምስጋናን ለማቅረብ ጥሩ አጋጣሚ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ በተጨማሪም አመት በዓል የጤና ስጦታን የምናስብበት ስለሆነ ለእርስዎም ይሁን ለሌሎች በበዓል ወቅት ለጤናና ደህንነት ጥንቃቄ ለመደገፍና ለማድረግ የሚከተሉትን ምክሮች እነሆ:-

እጅዎን ሁሌ መታጠብ
ከህመም ለመጠበቅና የጀርሞችን ስርጭት ወደሌሎች እንዳይዛመት ለመከላከል ከሚወሰዱ እርምጃዎች አንዱና ዋነኛዉ የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ መቻል ነዉ፡፡እጅዎን በንፁህ ዉሃና ሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

ምግብን ሲያሰጋጁም ይሁን ሲያቀርቡ በጥንቃቄ ያድርጉ
ለዓመት በዓል ምግብ ሲያዘጋጁ እርስዎንም ይሁን ቤተሰብዎን ምግብ ወለድ ከሆኑ ህመሞች መጠበቅ ይገባዎታል፡፡
• ከአንድ ምግብ ወደሌላ ምግብ ብክለትን ለመከላከል የተዘጋጁና ለመመገብ ዝግጁ የሆኑትን ምግቦች ካልተዘጋጁት ምግቦች( ከጥሬ ስጋ፣እነቁላልና ከመሳሰሉት) እንዲሁም የመመገቢያ ቦታ መለየት የስፈልጋል፡፡
• ምግቦችን ሲያዘጋጁ በአግባቡ መብሰላቸዉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
• የበሰሉትንም ይሁን ሌሎችንም ቢሆን አግባብ ባለዉ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት ማስቀመጥ፤በተጨማሪም በቀላሉ ሊበላሹ የሚችሉ ምግቦችን ከሁለት ሰዓታት በላይ ከፍሪጅ ዉጪ ያለማስቀመጥ፡፡

ጤናማ አመጋገብ እንዲኖሮትና ንቁ እንዲሆኑ ለማድረግ
የተመጣጠነና ጤንነቱን የጠበቀ ምግብ በመመገብ አመት በዓሉን በደስታና በጤናማ መንገድ ያሳልፉ፡፡
• ስብነት ያላቸዉን/የበዛባቸዉን፣ጣፋጭና ጨዉ የበዛባቸዉን ምግቦች መወሰን/መቀነስ
• አትክልትና ፍራፍሬ፡- ጣፋጭ ምግቦችን ትኩስ በሆኑ አትክልትና ፍራፍሬ መተካት
• ንቁና ደስተኛ ሊያደርጎት የሚችሉትን ነገሮች መተግበር፡- ለምሳሌ በሚወዱት የአመት በዓል ሙዚቃ መደነስ/መጨፈር
• የአልኮሆል መጠጦችን ከመጠን በላይ ያለመዉሰድ
• ሲጋራ ያለማጨስ/ሌሎች ሲያጨሱም ቢሆን ጭሱን ያለመማግ፡፡የሚያጨሱም ቢሆን ዛሬዉኑ ማጨስ ለማቆም መወሰን፡፡

አደጋን መከላከል( Prevent injuries)
አደጋዎች በየትኛዉም ቦታና ሰዓት የሚከሰቱ ቢሆንም አንዳንዶቹ ብዙዉን ጊዜ በአመት በዓል ወቅት ይበዛሉ፡፡በተቻለዎት መጠን
• የተጠቀሙበትን የኤልክትሪክም ይሁን ሌሎች የማብሰያ ምድጃዎች መዘጋታቸዉን ማረጋገጥ
• ለበዓል ተብለዉ የሚበሩ ሻማዎችን ከልጆች፣ከቤት ውስጥ እንስሳት( pets)ና ከመሳሰሉት ማራቅ ይገባል
• ከሰልን ከተጠቀሙ በኃላ ጭስ የሌለዉ ወይም የጠፋ መሆኑን ማረጋገጥ
• መጠጥ ጠጥተሁ ያለማሽከርከር ወይም ሌላ ሰዉ ጠጥቶ እንዲያሽከረክር ያለመፍቀድ

መልካም በዓል ይሁንልዎ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.