የወር አበባ ህመም (ዲስሜኖሪያ)

pelvic-painዛሬ በወር አበባ ህመም ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለወር አበባ ህመምም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡

ከወር አበባ ጋር የተገናኘ ህመም ከእንብርት በታች ያለ የሆድ ቁርጠት ሲሆን ብዙዎች ሴቶች የወር አበባዉ ከመምጣቱ ከጢቂት ቀናት በፊት ወይም በወር አበባዉ ወቅት ህመሙ ይታይባቸዋል፡፡ ይህ በተወሰኑት ሴቶች ላይ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ የቀን ተቀን እንቅስቃሴያቸዉን በየወሩ ያዉካል፡፡

የህመሙ ምልክቶች
• የሆድ ቁርጠት
• ህመሙን መግለፅ የሚያስቸግር ቀጣይንት ያለዉ የሚመዘምዝ ህመም
• ወደ ጭንና ጀርባ የሚሄድ/የሚሰራጭ ህመም

የተወሰኑት ሴቶች ላይ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች በተጨማሪ ሊታዩ ይችላሉ
• ማቅለሽለሽ
• ልል ሰገራ
• የራስ ምታት
• የመደካከም ስሜት/ማጥወልወል

ሀኪም ዘንድ መሄድ ያለቦት መቼ ነዉ?

የወር አበባ ህመም በየወሩ እየተባባሰ የሚሄድ ከሆነና የእልት ተእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያዉክ ከሆነ ወይም እድሜዎ ከ25 ዓመት በላይ ከሆነና ከወር አበባ ጋር የተገናኘ ከመጠን ያለፈ የሆድ ቁርጠት ካለዎት የህክምና ባለሙያን ማማከር ይመከራል፡፡

የወር አበባ ህመም መንስኤዎች

በወር አበባ ዑደት ወቅት ማህፀንዎት የወር አበባዉ እንዲፈስ ይኮማተራል፡፡ በወር አበባ ወቅት ለማህፀን መኮማተር፣ ለህመምና የማህፀን መቆጣት ምክንያት ከሚሆኑ ነገሮች ዉስጥ እንደ ፕሮስታግላንዲን ያሉ ሆርሞኖች የሚመነጩ ሲሆን የዚህ ሆርሞን በብዛት መመረት ህመሙ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር/እንዲባባስ ያደርጋል፡፡ የማህፀን ከመጠን ያለፈ መኮማተር በሚከሰትበት ወቅት ወደ ማህፀን የሚሄደዉን የደም ስሮች በማኮማተር( constriction) ወደ ማህጸን የሚሄደዉን የደም መጠን ስለሚቀንሰዉ ህመሙን እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡
በወር አበባ ወቀት የሚመጣዉ ህመም በሚከተሉት ምክንያቶችም ሊመጣ ይችላል፡፡

• ኢንዶሜትርዮስስ፡- ይህ የሚከሰተዉ የማህፀንዎትን የዉስጠኛ ክፍል የሚሸፍነዉ ክፍል ከማህፀንዎ ዉጪ በሌላ ቦታ እንደ የዘር ማስተላለፊያ ቱቦ (ፋሎፒያን ትዩብ)፣ እንቁርጤዎች (በዘር ፍሬ) ላይ፣ በሆድ እቃ ከረጢት ውስጥ በሚገኙ አካላት ላይ በሚያድግበት ወቅት ነዉ፡፡

• የማህፀን እጢዎች፡- በማህፀን ግድግዳዎች ላይ የሚያድጉ የማህፀን ዕጢዎች ለህመሙ መምጣት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

• አዴኖማዮሲስ (Adenomyosis) ፡-ይህ የሚመጣዉ የማህፀን የዉስጠኛዉ ክፍል (tissue that lines your uterus) ወደ ማህፀን ጡንቻዎቸ ውስጥ በሚያድግበት ወቅት ነዉ፡፡

• የዳሌ ዉስጥ ህመም(ፔልቪክ ኢንፍላማቶሪ ዲዚዝ- Pelvic inflammatory disease (PID))፡-ይህ በሴቶች የላይኛዉ የመራቢያ አካላቶች ላይ በአባለዘር ህመም አምጪ ባክቴሪያዎች እንፌክሽን በሚከሰትበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡

• የማህፀን አንገት ጥበት( Cervical stenosis)፡-የተወሰኑ ሴቶች ላይ የማህፀን አንገት በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የወር አበባ እንደልብ እንዳይፈስ ስለሚያግድ በወር አበባ ወቅት ህመም እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡

በወር አበባ ወቅት ለሚከሰት ህመም የሚያግልጡ ነገሮች

የህመሙን መከሰት የሚጨምሩ ነገሮች፡-
• ከ30 አመት በታች መሆን
• ለጉርምስና (puberty) ቶሎ መድረስ፡- ከ11 አመታትና ከዚያ በታች
• በወር አበባ ወቅት የሚፈሰዉ ደም ብዙ መሆን ( menorrhagia)
• የሚዛባ የወር አበባ ዑደት ካለዎት(metrorrhagia)
• ልጅ ወልደዉ የማያዉቁ ከሆነ
• በቤተሰብዎ ዉስጥ መሰል ችግር ካለ
• ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ

በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው ህመም የሚያመጣዉ ጉዳት/ችግር (complications)

በወር አበባ ወቅት የሚከሰት ህመም በትምህርት፣ በስራና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎት ላይ ከሚያመጣዉ ጫናና ማወክ ዉጪ የሚያመጣው ምንም አይነት የህክምና ጉዳት ወይም ችግር የለም፡፡ ነገር ግን ይህን ህመም እንዲከሰት የሚያደርጉ እንደ ኢንዶሜትርዮስስና የዳሌ ዉስጥ ህመም ያሉ ተያያዥ ችግሮች ካሉ የልጅ ያለመዉለድንና ከማሕፀን ዉጪ እርግዝና እንዲከሰት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የሚደረጉ ምርመራዎች

የህክምና ባለሙያዎ የመራቢያ አካላትዎ ላይ ምርመራ በማድረግ ለህመሙ መንስዔ የሆኑ ሌሎች የጤና ችግሮች መኖራቸዉንና አለመኖራቸዉን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ምርመራዎች ሊያዙሎት ይችላሉ፡፡
• የአልትራሳዉንድ ምርመራ
• ሲቲ ስካን፣ኤም.አር.አይ (MRI)
• ላፓራስኮፒ( Laparoscopy)

የሚደረጉ ህክምናዎች

• የህመም ማስታገሻዎች፡- እንደ አይቡፕሮፌን(አድቪል) ያሉ ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ የሚችሉ የህመም ማስታገሻዎችን የወር አበባዎ መፍሰስ ከመጀመሩ ከአንድ ቀን በፊት አስቀድሞ መጀመርና የህመም ስቃዩ እስኪያልፍ ድረስ መቀጠል

• የወሊድ መከላከያ እንክብሎች፡-የወሊድ መከላከያ እንክብሎች የእንቁላልን ከአብራኳ መዉጣትን ስለሚከላከሉ የህመሙን ደረጃ ይቀንሳሉ፡፡

• ቀዶ ጥገና፡-ለህመሙ መከሰት መንስዔዉ የማህፀን ዕጢ ወይም እንዶሜትሪዮሲስ ከሆነ በቀዶ ህክምና ሊስተካከሉ ይችላሉ፡፡

የኑሮ ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና
• የአካል እንቅስቃሴ፡- ጥናቶች እንዳረጋገጡት የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በወር አበባ ወቅት የሚከሰተዉን ህመም ሊቀንስ ይችላል፡፡

• ሙቀት፡- ሙቅ ሻወር መውሰድ፣ የሞቀ ዉሃ የተሞላ ጠርሙስ በእንብርት በታች ባለዉ ሆድ አካባቢ መያዝ ህመሙን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

• ተጨማሪ ምግቦች፡- ቫይታሚን ኢ፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ፣ ቫይታቢን ቢ1(ታያሚን)፣ ቫይታሚን ቢ6 እና ማግኒዝየም በተጨማሪ መዉሰድ የህመም ስቃዩን በሚገባ ይቀንስልዎታል፡፡

• መጠጥንና ሲጋራን ማስወገድ፡- መጠጥ መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በወር አበባ ወቅት የሚከሰተዉን ህመም ስለሚያባብሱ በተቻለ መጠን እነዚህን ነገሮች ከመውሰድ መቆጠብ፡፡

• ጭንቀትን ማስወገድ፡- ጭንቀት ህመሙ እንዲባባስና ከፍ ያለ ደረጃ እንዲደርስ ያደርዋል፡፡

======ዛሬ ጤናማ ቆዳ እንዲኖሮት የሚመከሩ 5 ነገሮች ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ስለቆዳ እንክብካቤም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡

የቆዳ እንክብካቤ

1. የፀሃይ ብርሃንን መከላከል

• ሰን ሰክሪን መጠቀም
• ጥላ ዉስጥ መሆን
• ፀሃይን ሊቀንሱ የሚችሉ አልባሳትን መጠቀም
2. ሲጋራ ያለማጨስ

3. ቆዳዎትን በጥንቃቄ መያዝ

• ረጅም ሰዓት ሻወር ዉስጥ ያለመቆየት፡-ሙቅ ዉሃና ለረጅም ሰዓት ሻወር መዉሰድ የቆዳን ወዝ ስለሚያሳጣ የሻወርን ሰዓት ማሳጠር እንዲሁም ከሙቅ ዉሃ ይልቅ ለብ ያለ ዉሃ መጠከም ይመከራል
• ለገላ መታጠቢያነት የሚያገለግሉ ሳሙናዎችን ብቻ መጠቀም፡- ጠንከር ያሉ ሳሙናዎችና ዲተርጀንቶችን መጠቀም የቆዳን ወዝ ስለሚያሳጣ እነዚህን ከመጠቀም መቆጠብ
• በጥንቃቄ መላጨት፡- ቆዳዎትን ለማለስለስና ለመከላከል የመላጪያ ክሬሞችን፣ሎሽኖችን ወይም ጄል መጠቀም፡፡ሲላጩ ስለቱ የዶለዶመ ምላጭ ያለመጠቀም፣ ፀጉር መደሚተኛበት አቅጣጫ እንጂ ወደተቃራኒዉ ያለመላጨት
• ቆዳዎትን ማደራረቅ፡- ከታጠቡ ወይም ሻወር ከወሰዱ በኃላ ቆዳዎት ላይ የተወሰነ እርጥበት እንዲኖረዉ ከላይ ከላይ በፎጣ ማደራረቅ(ያለመፈተግ)
• ቆዳዎትን ማለስለስ፡-ቆዳዎት እየደረቀ የሚቸገሩ ከሆነ ቆዳዎትን ሊያለሰልሱ የሚችሉና ለቆዳዎት ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን መጠቀም

4. ጤናማ አመጋገብን መከተል/ጤናማ አመጋገብ እንዲኖሮት ማድረግ፡-ጤናማ አመጋገብ ጥሩ ስሜት እንዲኖሮት ያደርጋል፡፡ስለዚህ በዛ ያለ አትክልትና ፍራፍሬ፣ጥራጥሬ እና ቀይ ስጋ መመገብ፡፡በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦች፣ጤናን የማይጎዱ ስቦች፣በፋብሪካ የተቀነባበሩ ካርቦሀይድሬቶችን መጠቀምም ቆዳዎት ጤናማ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርገዋል

5. ጭንቀትን ማስወገድ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.