ከመጠን ያለፈ ላብ (hyperhidrosis)

ከመጠን በላይ የሆነ ላብ ማላብ ሀይፐርሀይድሮስስ ይባላል፡፡

hqdefault (1)ሀይፐርሀይድሮስስ ብዙዉን ጊዜ የሚከሰተዉ በእጅ መዳፍ፤በእግር መዳፍ(የዉስጥ እግር)ና ብብት ዉስጥ ሲሆን እንደ ጤና ችግር የሚቆጠረዉ የእረስዎን የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን የሚያስተጓጉል ከሆነ ነዉ፡፡ ሀይፐርሀይድሮስስ የእለት ከዕለት እንቅስቃሴዎትን ከማስተጓጎሉም በተጨማሪ ማህበራዊ ጭንቀትንና እፍረትን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ሃኪሞትን ማማከር የሚገባዎት መቼ ነዉ?

• ላቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴዎትን ካስተስጓጎሎት
• ያልተለመደ ከበፊቱ የተለየ ብዙ የሚያልቦት ከሆነ
• ምክንያቱን ያላወቁት ማታ ማታ ላብ ካለዎት

ይኸንን ችግር ለማሻሻል ከሚረዱ ዘዴዎች ዋነኛዉ የላብን መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶችን መጠቀም ሲሆን ችግሩ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰ ከሆነ ደግሞ ላብን ከመጠን በላይ የሚያመርቱትን የላብ ዕጢዎች ወይም ወደ ላብ ዕጢዎች የሚሄዱትን ነርቮች በቀዶጥገና እንዲስተካከል ማድረግ ይቻላል፡፡

አጠቃላይ ምክሮች

• በየቀኑ መታጠብ፡ ይህን ማድረግዎ በሰዉነትዎ ላይ ያሉትን የባክቴሪያ መጠን ይቀንሳል
• ሻወር ከወሰዱ በኃላ እግሮትን በደንብ ማድረቅ፡ በጣትዎት መካከል በደንብ ማድረቅ፤ፓዉደር መጠቀም
• የሚጠቀሙትን ጫማና ካልሲ መምረጥ፡ ጫማዎትንና የጫማዎትን ሶል ከቆዳ የተሰራ ቢሆን ይመረጣል
• ጫማዎትን መቀያየር፡ አንድን ጫማ ከሁለት ቀን በላይ ያለማድረግ
• የሚጠቀሙት ካልሲ ጥጥነት ወይም ሱፍነት ያለዉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ከጥጥ ወይም ከሱፍ የተሰሩ ካልሲዎች እርጥበትን የመምጠጥ ባህሪይ ያላቸዉ ሲሆን እንቅስቃሴ በጣም በሚያበዙበት ወቅት ደግሞ እርጥበትን በደንብ ሊመጡ የሚችሉ የአትሌት ካልሲ የሚባሉትን መጠቀም ይመረጣል
• እግሮት አየር እንዲያገኝ ማድረግ፡ በሚመቾት ሰዓት እግሮትን ከጫማ ማዉጣትና ማናፈስ፤እቤት ዉስጥ ደግሞ ባዶ እግር ወይም ነጠላ ጫማ ማድረግ
• ከጥጥ፤ ሱፍ ወይም ናይለን የተሰሩ ልብሶችን ማዘዉተር፡ እነዚህ አየር በደንብ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ

====መጥፎ የአፍ ጠረንን ወይም ሃሊቶስስን የሚያመጣዉ ምንድነዉ?

መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት፡፡ ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚዉን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በስራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ፡፡

• የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ
• የድድ ህመም መኖር
• ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ዉስጥ መራባት
• እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት
• የሳይነስ እንፎክሽን
• መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች)
• ሲጋራ ማጨስ
• የተወሱ የምግብ አይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ሽንኩርት፤ሰርዲን፤ከፍተኛ የገንቢ ምግብ(ፕሮትን) ያላቸዉ ምግቦች)
• የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር
• የሆድ ድርቀት

መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያዉቁ ይችላሉ?

• መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት
• በጣም የሚመከረዉ ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰዉ መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እዉነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸዉ፡፡

መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ምክሮች

• ምግብ ከተመገቡ በኃላ ጥርስዎትን መታጠብ(መቦረሽ)
• ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት
• ምላስዎትን መቦረሽ
• አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት
• የአፍ ድርቀትን መከላከል፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ዉሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.