እርግዝና (ጽንስ)

inside-5c1dbed6f9የወንድ የዘር ፈሳሽ በሴቷ ብልት ውስጥ በተፈጥሮአዊ የግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በሰውሰራሽ መንገድ ከፈሰሰ በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዘር ህዋሶች ከታችኛው የሴቷ የብልት ክፍል ወደላይ በመዋኘት በሴቷ የዘር ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ የተዘጋጀ እንቁላል ካገኙ በእንቁላሉ ዙሪያ ያለውን ቅርፊት ለመስበር ይሞክራሉ።

ከመሃከላችው አንድ የተሳካለት የዘር ህዋስ ከእንቁላሉ ተዳቅሎ ጽንስ ይፈጥራል። ይህም ማለት የሴቷ እንቁላልና የወንዱ የዘር ህዋስ አንድ የሰው ህዋስ ይሆናሉ ማለት ነው።

ይህ ህዋስ 2፣ 4፣ 8፣16 እያለ በተደጋጋሚ በመከፋፈል ከዘር ማስተላለፊያ ቱቦ ወደ ታች በመውረድ በመጨረሻ በሴቷ የማህጸን ግርግዳ ውስጥ ይቀበራል። የህዋሶቹ መከፋፈል በቁጥር እንዲሁም በአይነት የተለያዩ ብዙ ህዋሶች በመፍጠር ወደፊት የእንግዴ ልጅ የሚሆነውን ከረጢት እንዲሁም ልጅ የሚሆነውን ሽል ይፈጥራሉ።

የሴቷ እንቁላል ከመዘጋጀቱና ከመለቀቁ እስከ 120 ሰዓት በፊት ድረስ የተደረገ ግንኙነት ጽንስ የማስከተል እድል አለው። እንቁላሉ ከተለቀቀ በኋላ ወይም እንቁላሉ በሚለቀቅበት ወቅት የተደረገ ግንኙነት ግን ጽንስ ለማስከተል አይችልም።

Fotolia_37682524_XS-43ee64957f

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.