ከፍተኛ የደም ግፊት ሀይፐርቴንሽን (አለሳልሶ ገዳይ)

የደም-ግፊትየደም ግፊትን ሳይታከሙ ወተው የልብ ምት ማቆም፣ የልብ በፍጥነት መምታት፣ የኩላሊት መጎዳት፣ ሞት፣ Eይታን
ማጣት ወይም የAEምሮ መጎዳት የመሳሰሉ የተወሳሰቡ የጤና ችግሮች Eንዲከሰቱ ያደርጋል፡፡
‹‹ሀይፐርቴንሽን›› የህክምና ሳይንስ ቃል ሲሆን ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመግለጽ ያገለግላል፡፡ የደም ግፊት ደምን ወደ
ሌላው የሠውነት ክፍል ለመርጨት (ለማድረስ) የሚረዳ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ጤናማ የማይሆን ሲሆን
ከፍተኛ የሆኑ የጤና ችግሮችንም ሊያስከትል ይችላል፡፡
(ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ) Aዋቂ ሰው ከፍተኛ የደም ግፊት የ140 ሚ.ሜ ኤችጂ ሲስቶሊክ የደም ግፊት (‹‹የላይኛው
ቁጥር››) ወይም ከዚያ በላይ Eና የ90 ሚ.ሜ. ኤች ጂ ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ዲያስቶሊክ (‹‹የታችኛው ቁጥር››) የደም
ግፊት Eንደሆነ ተደርጎ ይገለጻል፡፡ ሲስቶሊክ የደም ግፊት የሚባለው ልብ ሲመታ በደምቅዳ የደም ቧንቧ ግድግዳዎች ላይ
የሚለካው ኃይል ነው፡፡ ዲያስቶሊክ የደም ግፊት በሁለት የልብ ምቶች መሀከል ወይም ልብ ሪላክስ ሲያደርግ በደም ቅዳ
የደም ቧንቧዎች ላይ የሚለካው ኃይልነው፡፡ የደም ግፊት በሜርኩሪ (ሚሜ ኤችጂ በሚሊ ሜትር ይለካል፡፡
ከፍተኛ የደም ግፊት በማናቸውም የEድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን በAብዛኛው ግን Eድሜያቸው
ከ35 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡ ከ50 ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ Aሜሪካዊያን ላይ (ከAራት ሰዎች Aንዱ ላይ)
የደም ግፊት ይታያል፡፡ በተለይም በAፍሮ Aሜሪካዊያን (ከሶስት ሰዎች Aንዱ ላይ) ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ ይታያል፡፡
በርካታ ነገሮች በደም ግፊት ላይ ተፅEኖ የሚያሳድሩ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በሰውነት ውስጥ ያለው የውሃ መጠን፣
የጨው መጠን፣ ሆርሞኖች፣ የEንቅስቃሴ ደረጃ፣ የሰውነት ሙቀት፣ ስሜታዊነት Eና የኩላሊቶች፣ የነርቭ ስርዓት Eና
የደም ቧንቧዎች ሁኔታ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የደም ግፊት ከፍተኛ ከሆነና ባለበት ከተተወ፣ ልብ Eና ደም ቅዳ የሚባሉት
የደም ቧንቧዎች መስራት የሚገባቸውን ያህል Aይሰሩም፡፡ መሠረታዊው (ቀዳሚው) ከፍተኛ የደም ግፊት ተለይቶ የታወቀ
ምክንያት የለውም፡፡ ይህ Aይነቱ ከፍተኛ የደም ግፊት ከፍተኛ የደም ግፊት ካለባቸው ህመምተኞች ሁሉ 95 በመቶውን
ይይዛል፡፡ ምንም Eንኳ ምክንያቱ ግልጽ ባይሆንም የAመጋገብ ሥርዓት Eና Aካላዊ Eንቅስቃሴ የመሳሰሉት የጀነቲክና
Aካባቢያዊ ሁኔታዎች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ሁለተኛው ከፍተኛ የደም ግፊት ከፍተኛ በሆነ ችግር ምክንያት የሚከሰት ከፍተኛ የደም ግፊት ነው፡፡ ምሳሌዎቹ
የሚከተሉትን ያካትታሉ፡፡
♥ የተወሰኑ ደም ቅዳዎች መቅጠን
♥ በAድሬናል Eጢ ላይ የሚከሰቱ ችግሮች
♥ የኩላሊት ችግር
♥ ህክምናዎችን፣ Aደንዛዥ Eጾችንና ሌሎች ኬሚካሎችን መጠቀም
♥ Eርግዝና
♥ በAፍ የሚወሰዱ የEርግዝና መከላከያዎችን፣ ስቴሮይዶችን፣ Aንቲሂስታሚኖችን፣ መነቃቂያዎችን ወይም ነን-
ስቴሮይዳል Aንቲ-Iንፍላማቶሪ መድኃኒቶችን መጠቀም፡፡
♥ ሌሎች ተያያዥ ችግሮችና ምልክቶች
ክፍል ሲስቶሊክ የደ.ግ. (ሚ.ሜ ኤች ጂ) Eና/ወይም ዲያስቶሊክ የደ.ግ. (ሚ.ሜ ኤች ጂ)
ከፍተኛው <120 Eና <80
ኖርማል 120-129 Eና 80-84
ከፍተኛ ኖርማል 130-139 ወይም 85-89
ከፍተኛ የደም ግፊት >140 ወይም >90
erte si –
— ri ( e 1)ለከፍተኛ የደም ግፊት መንስኤ የሚሆኑ ምክንያቶች
♥ ከፍተኛ ውፍረት
♥ በምግብ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ጨው ወይም ሶድየም መጠቀም
♥ ብዙ ጊዜ መቀመጥ ማብዛት
♥ ሲጋራ ጤስ
♥ ከፍተኛ ውጥረት/ጭንቀት ያለበት Aካባቢ
♥ ጤናማ ያልሆነ Aመጋገብ
♥ በቤተሰብ ውስጥ በከፍተኛ የደም ግፊት የሚታመሙ ሰዎች መኖር
የከፍተኛ የደም ግፊት መከላከያ
♥ ሲጋራ ማጤስን ማቆም
♥ ክብደትዋ ከፍተኛ ከሆነ፣ መቀነስ
♥ የልብን ጤናማነት ለማሻሻል Aካላዊ Eንቅስቃሴን መጨመር
♥ ሶድየም ወደ ‹ 2.4 ግ መቀነስ ወይም በቀን ‹ 6ግ ጨው (1 1/4 የሻይ ማንኪያ ጨው)
♥ ብዙ ቅባትንና ኮሌስቴሮልን ከምግብ ውስጥ መቀነስ
♥ መጠነኛ Aልኮል መውሰድ (በቀን ከAንድ Eስከ ሁለት)
♥ በቂ የሆነ ካልሺየም፣ ፖታሺየም፣ ማግኒዝየም Eና ፕሮቲን መውሰድ
♥ ጭንቀትን ማስወገድ
የከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች
♥ ራስ ምታት
♥ ድካማም
♥ የAይን የማየት Aቅም መለወጥ
♥ ማስታወክ ማቅለሽለሽ
♥ ስጋት
♥ ግራ መጋባት
♥ የቆዳ መወየብ ወይም መቅላት
ማሳሰቢያ፡ Aብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ምንም ምልክት Aይታይባቸውም፡፡
የደም ግፊትዎን ስለለመካት ምን ያስባሉ ?
የደም ግፊት ልኬት ውጤቶች በሀኪም ጽ/ቤት ውስጥ ሊከናወን የሚችል ሲሆን በተለያዩ የህክምና ባለሙያዎች ሊከናወን
ይችላል፡፡ በማህበራዊ ማEከላት ወይም በጤና Aሰራሮች ውስጥ የጤና ምርመራዎች የደም ግፊት ለመለካት Eድሉን ሊሰጡ
ይችላሉ፡፡ የደም ግፊትዎን በተወሰኑ መደበኛ በሆኑ የጊዜ ርቀት ውስጥ (በየዓመቱና በየሁለት ዓመቱ) መለካት Aስፈላጊ
ነው፡፡ የደም ግፊትዎን ከመለካትዎ በፊት ቡና Aይጠጡ ወይም ሲጋራ Aያጪሱ፡፡ የደም ግፊትዎ ከፍተኛ ከሆነ ሀኪም
ዘንድ Eየተመላለሱ በመታየት ወደፊት ሊከሰት ስለሚችል የጤና ችግር ማወቅ Aስፈላጊ ነው፡፡ Aንድ ጊዜ በመለካት የታየ
ከፍ ያለ የደም ግፊት ለደም ግፊት ምርመራ በቂ Aይደለም (ሁለት Eና ከዚያ በላይ የሆኑ ጊዜያት ተለክቶ ማየት
ያስፈልጋል፡፡)
የደም ግፊት ህክምና
♥ Aመጋገብን መቆጣጠር ጨው፣ ብዙስብ Eና ኮሎስትሮልን መቀነስ
♥ ጭንቀትን ማስወገድ፣ ጭንቀትን መቀነስ ወይም ጭንቀትን የሚከላከሉበትን መንገድ መፈለግ
♥ Aካላዊ Eንቅስቃሴ፡ በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል ጥሩ Aካላዊ Eንቅስቃሴ ማድረግ ይመከራል፡፡
♥ ክብደትን መቀነስ፣ Aስፈላጊ ከሆነ
♥ ሀኪምዎ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚረዳ መድሃኒት ሊያዝ ይችላል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.