(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)

Brain1. ቁርስ አለመመገብ

ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።

2. በህመም ወቅት በቂ እረፍት አለማድረግ

ሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖር ይረዳል።

3. ሲጋራ ማጤስ

ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባ ካንሰር እና ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

4. ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።

5. የአየር ብክለት

አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።

6. የእንቅልፍ እጦት

እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።

ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡

7. የአልኮል መጠጥ ማብዛት

በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

8. የምግብ አይነቶችን መምረጥ

ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።

ጤና ይስጥልኝ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.