ቲቢ(የሳምባ ነቀርሳ) ምንድነው?

tuberculosis_symptoms“ቲቢ” የቱበርኪሎሲስ የተባለ በሽታ ምህፃረ ቃል ሆኖ በአየር ላይ መንሳፈፍ በሚችሉ ጥቃቅን ጀርሞች አማካኝነት ይተላለፋል። በቲቢ የተለከፈ ሰው በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት፣ ወይም በሚጮህበት ግዜ፣ እነዚህን ጀርሞች ወደ አየር ይበትናሉ። ሌላ ሰው እነዚህን  ጀርሞች ወደ ውስጥ ካስገባ/ከተነፈሰ፣ በቱበርኪሎሲስ(ቲቢ) ሊለከፉ ይችላሉ። ቲቢ ድካም እንዲሰማዎት ሊያደርግ ይችላል፣ ሳል ሊያስልዎት ይችላል፣ ትኩሳትና ማታ ማታ ሊያልብዎት ይችላል። አብዛኞቹ ሰዎች ቲቢ ሳምባን ብቻ ያጠቃል ብለው ያስባሉ። ምንም እንኳን  በቲቢ ከተለከፉ ሰዎች 70% በሳምባቸው ውስጥ ጀርሞቹ ቢገኙም፣ በተጨማሪ ቲቢ አጥንት፣ ጭንቅላት ወይም ልብን የመሳሰሉት  የሰውነት ክፍሎችን ሊያጠቃ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የቲቢ ጀርም በሰውነታቸው ውስጥ ሊኖራቸው ይችላል፣ ሆኖም ግን ህመም ላይሰማቸው ይችላል። ይህ የተዳፈነ(latent)ወይም “ድብቅ” የቲቢ ልክፍት ይባላል። ሌሎች ደግሞ ህመሙ ይሰማቸዋል፣ እንዲሁም ገቢር የቲቢ በሽታ አላቸው፡፡ የቲቢ በሽታ ገቢር በሚሆንበት/ማጥቃት በሚጀምርበት ወቅት በሰውነት ውስጥ ሊታዩ የሚችሉ ስሜቶች/ምልክቶች  የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ 12   በቲቢ በሽታ መለከፌን እንዴት አውቃለው? በክንድዎ ላይ የሚደረግ ቀላል ምርመራ የቲቢ ጀርም በሰውነትዎ ውስጥ መኖሩን አለመኖሩን ሊያረጋግጥልዎት ይችላል፡፡ ፖሲቲቭ የሆነ የቲቢ  የቆዳ ምርመራ ውጤት አብዛኛውን ግዜ የቲቢ ጀርም በሰውነትዎ ውስጥ መነሩን ያረጋግጥሎታል። እንደ የደረት የኤክስረይ ምርመራ ወይም የአክታ  ምርመራ የመሳሰሉ ተጨማሪ ምርመራዎች ሊስፈልግዎ ይችላል።.በክንድዎ ላይ የሚደረግ ቀላል ምርመራ የቲቢ ጀርም በሰውነትዎ ውስጥ መኖሩን አለመኖሩን ሊያረጋግጥልዎት ይችላል፡፡ በድብቅ ቲቢና በገቢር(“ንቁ”) ቲቢ መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?  የተዳፈነ የቱበርኪሎሲስ ልክፍት(LTBI) በተጨማሪ “ድብቅ” ቲቢ ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ጀርሞቹ ሰውነትዎ እስኪፋለማቸው ድረስ በድብቅ  ይኖራሉ። የቲቢ ፖሲቲቭ የምርመራ ውጤት ሊኖርዎት ይችላል ሆኖም ግን ድብቅ ቲቢ ካልዎት የደረት ኤክስረይ ውጤት የተለመደ/ጤናማ ሊሆን  ይችላል። ለሌሎች ሊያስተላልፉት አይችሉም፣ ሆኖም ግን የቲቢ መድሃኒቶች ከወሰዱ ጀርሞቹን የማነቃቃት ዕድል አነስተኛ ይሆናል። ገቢር(ንቁ) የቲቢ ጀርሞች በሰውነት ውስጥ ገቢር ናቸው እና አሁን ወደ ሳምባ ወይም ሌሎች የስውነት ክፍሎች ሊዛመቱ ይችላሉ እንዲሁም ከባድ  በሽታ ሊይስከትልብዎ ይችላል። በመሳል፣ ማስነጠስ ወይም በመጮህ እንዲሁም ጀርሞችን ወደ አየር በመርጨት/በመበተን ሌሎች ሰዎች ደግሞ  ጀርሞቹን ከአየር ጋር ስበው በማስገባት አመካኝነት የቲቢ በሽታው ሊያስተላልፉ ይችላሉ። የቲቢ በሽታ ቢኖረኝስ?. ጤነኛ ሆነው ለመቆየት መድሃኒት ሊወስዱ ይችላሉ። ቲቢ ሊፈወስ ይችላል! ሆኖም ግን፣ መድሃኒቱን ካልወሰዱ፣ ቲቢ ከባድ ህመም እንዲሰማዎት  ሊያደርግ ይችላል።መድሃኒቱምን መውሰድ ከጀመሩ ጤንነት ቢሰማዎትም እንኳ፣ ሃኪምዎ ወይም ረዳት ሃኪምዎ እስካልነገርዎት ድረስ መድሃኒቱን  መውሰድ እንዳያቆሙ። መድሃኒቱን መውሰድዎን ቶሎ ካቋረጡ፣ የቲቢ ጀርሙ ተመልሶ ይመጣና ለመፋለሙ/ለመመከቱ በጣም ከባድ ይሆናል። የቲቢ የቆዳ ምርመራ ምንድነው? የቲቢ የቆዳ ምርመራ ማለት በጣም ጥቂት የፈሳሽ መጠን ልክ በክንድዎ ቆዳ ስር በመርፌ መስጠት ማለት ነው። ትንሽ አረፋ  በ5 እስከ 10 ደቂቃቅች ውስጥ እንዲጠፋ ያደርጋል። መርፌ ከተወጉበት ግዜ በ 2 እስከ 3 ቀናቶች ውስጥ ወደ ሃኪምዎ  ወይም ረዳት ሃኪምዎ መመለስ ይኖርብዎታል፣ ክንድዎን  በማየት የቆዳ ምርመራ ውጤቱ ፖዚቲቭ ወይም ነጋቲቭ ነው  እንዲወስንልዎ። የቆዳ ምርመራ ካደረግኩ በኋላ ክንዴን እንዴት እንከባከበዋለው? መርፌ የተወጉበት ቦታ በፕላስተር ወይም በባንድ  ኤይድ አይሸፍኑት። ቦታውን አይሹት ወይም አይከኩት። የቲቢ የቆዳ ምርመራ ውጤቴ ነጌቲቭ ቢሆንስ? በአብዛኛው ሁኔታዎች፣ የምርመራ ፈሳሹ በመርፌ በተሰጠበት ቦታ እብጠት ከሌለ፣ ምናልባት በቲቢ አልተለከፉም ይሆናል። የቲቢ የቆዳ ምርመራ ውጤቴ ፖሲቲቭ ከሆነስ? ፖሲቲቭ የምርመራ ውጤት ምርምራው በተደረገበት ቦታ  ወጣ ባለ አንኳር/እብጠት ይገለጣል። ይህ ማለት ደግሞ  ምናልባት የቲቢ ጀርም በሰውነትዎ ውስጥ አለ ማለት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.