የተለያዩ የጽንስ መከላከያ ዘዴዎችን ያዉቃሉን? (በዳንኤል አማረ)

pregrenancy preventtionበአንድ ቤተሰብ ዉስጥ የልጆች ቁጥር መብዛት ለበርካታ ኢኮኖሚያና ማህበራዊ ችግሮች ያጋልጣል ይህ ደግም በሀገር እድገት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ያደርሳል::

በመሆኑም የህዝብ ቁጥር እድገት ከአገር ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማቶች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የቤተሰብ ምጣን ዘዴዎች መጠቀም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ::

1 ባህላዊ (ልማዳዊ ) የጽንስ መከላከያ ዘዴዎች
ሀ. ጡት ማጥባት
ለ. የወንድን የዘር ፍሬ ከሴት ብልት ዉጭ ማፍሰስ
ሐ. የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመፈጸም መቆጠብ
2. ተፈጥሮአዊ የጽንስ መከላከያ ዘድዎች
ሀ. የቀን አቆጣጠር
ለ. ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽን መመርመር
ሐ. የሰዉነትን ሙቀት መለካት
3. ሰዉ ሰራሽ የጽንስ መከላከያ ዘዴዎች
3.1 ከሆርሞኖች የሚዘጋጅ
ሀ. ከጥምር ሆርሞን የሚዘጋጁ ክኒኖች
ለ. ከባለ አንድ ሆርሞን የሚዘጋጁ ክኒኖች
በቆዳ ስር የሚቀበር መከላከያ
በመርፌ የሚሰጥ መከላከያ
ሐ. ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ
3.2 በማህጸን ዉስጥ የሚቀመጥ ሉፕ
3.3 ዘለቄታዊ የመከላከያ ዘዴ
ሀ. ሴቶችን የማምከን ዘዴ
ለ. ወንዶችን የማምከን ዘዴ
3.4 የወንድ የዘር ፍሬ ወደ ማህጸን እንዳይገባ የሚያደርጉ፣የሚያደክሙ ወይም የሚገድሉ
ሀ. ኮንዶም
ለ. አረፋማ ክኒን ናቸዉ

1. ባህላዊ (ልማዳዊ) ጽንስ መከላከያ ዘዴዎች
ሀ. ጡት ማጥባት
የእናቶች ጡት ወተት አቻ የማይገኝለት ተፈጥሮአዊ ምግብ ከመሆኑ በላይ እርግዝና እንዳይከሰት ይረዳል::
ጡት የምታጠባ እናት እርግዝናን መከላከል የምንትችለዉ ህጻኑ ከእናቱ ጡት ዉጭ ሌላ ተጨማሪ ምግብ የማያገኝ ለሆነና ሌሊትም ሆነ ቀን ቢቻል በቀን ለ9 ጊዜ ያህል መጥባት ከቻለ የወር አበባ እስካልመጣ ድረስ ህጻኑ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ6 ወር ድረስ መከላከያነቱ አስተማማኝ ሊሆን ይቻላል ::
ከ6 ወር በላይ ጡት የምታጠባ እና ሌላ የጽንስ መከላከያ ዘዴ የምትጠቀም
ጡቷን ለልጇ ያለማቋርጥ የማታጠባ እናት ከ6ወር በፈት ልታረግዝ ስለምትችል በእርግዝና መከላከያ ዘዴ ለመጠቀም ባለሙያዎችን ማማከር ይኖርባታል ::
ለ. የወንዱችን የዘር ፍሬ ከሴት ብልት ውጭ ማፍስስ
ይህ ዘዴ ጥንታዊ የጽንስ መከላከያ ዘዴ ነዉ::
የወንድን የዘር ፍሬና የሴት እንቁላል እንዳይገናኙ ያደርጋል::
በማንኛውም ጊዜና በተፈለገበት ቦታ ወጭ ሳይጠይቅ ሊከናወን ይችላል ::ሆኖም በዚህ ዘዴ የሚጠቀሙ ሁለቱ ጾታወች ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረጉ እርግዝና ሊፈጠር ስለሚችል ዘዴዉ አስተማማኝ አይደለም፡፡
ሐ. የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመፈጸም መቆጠብ
ይህ ዘዴ በጥንት ዘመን ሰዎች ስለጽንስ መከላከያ ዘዴዎች በቂ ግንዛቤ ባልነበራቸዉና ዘመናዊ የጽንስ መከላከያ ዘዴዎችን ለመጠቀም የሚያስችል ስልጣኔ ባልነበረበት ወቅት እንደ ጽንስ መከላከያ ዘዴነት በአማራጭነት ይጠቀሙበት ነበር፡፡
ዘዴዉ የሁለቱንም ጾታዎች መተሳሰብና ስምምነት የሚጠይቅ ነዉ፡፡
2. ተፈጥሮአዊ የጽንስ መከላከያ ዘዴዎች
ሀ. በቀን አቆጣጠር
በቀን አቆጣጠር ዘዴ እርግዝናን መከላከል የሚቻለዉ የወር አበባ መመለሻ ጊዜን መሰርት በማድረግ ነዉ፡፡
አንዲት ሴት በዚህ ጊዜ ከመጠቀሟ በፊት ትክክለኛዉን የእንቁላል መዉጫ ስሞን ለማወቅ ከ6 እስከ 8 ወራት ያህል የወር አበባዋ በስንት ቀን ልዩነት እንደሚመጣ መዝግቦ መያዝ ይኖርበታል፡፡

በዚህም መሰረት
• አንዲት ሴት በአማካኝ በየ28 ቀናት ልዩነት የወር አበባዋ የሚመላለስ ከሆነ የወር አበባዋ ከመጣበት ቀን ጀምሮ ያሉት ከ11 እስከ 18 ቀኖች እርግዝና ሊከሰት የሚችልባቸዉነ ቀናት ተብለዉ ይገመታሉ፡፡
• አንዲት ሴት የወር አበባዋ አንዴ ቀድሞ ሌላ ጊዜ ዘግይቶ የሚመላለስ ከሆነ ከአጭሩ የወር አበባ 18 እና ከረጂሙ የወር አበባ ዑደት 11 በመቀነስ ከግብረ ሰጋ ግንኙነት የምትቆጠብበትን ቀን ማወቅ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ:- የአንዲት ሴት የወር አበባ የተዘበራረቀ መምጫ ኖሮት ረዥሙ 32ቀን አጭሩ 24 ቀን ቢሆን
ከ24-18=6
32-11=22 ይህ ማለት የወር አበባ የመጣበትን ቀን 1 ብሎ በመቁጠር ከ6 እስከ 22ኛዉ ቀን ድረስ የግብረ ስጋ ግንኙነት ቢፈጸም እርግዝና ሊኖር ይችላል፡፡

ለ. ከማህጸን የሚወጣ ፈሳሽን መመርመር፦ በዚህ ዘዴ ጽንስን ለመከላከል አንዲት ሴት በብልት አካባቢ እርጥበት ወይም ድርቀት መኖሩን ከሽንት በፊት ወይም በሗላ እንዳመችነቱ መመርመር አለባት ፡፡
በዚህ መሰረት:-
• የእንቁላል ነጩን አሰኳል የሚመስል የሚያሙለጨልጭ ብሩህ መልክ ያለዉ ና እንደክር የሚሳብ ፈሳሽ ከታየ ፈሳሹ በእንቁላል መዉ ጫ ጊዜ የሚፈጠር ስለሆነ እነዚህ ቀናት የሚረገዝባቸዉ መሆናቸዉ በመገንዘብ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት መታቀብ ወይም ልላ ጊዚያዊ ዘዴ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
• ከብልት የሚወጣዉ ፈሳሽ ወፍራም፣ ደመናማ፣ የሚያጣብቅ ሽሮ መልክ ቀለም በሚኖረዉ ወቅት የግብረ ስጋ ግነኙነት ቢፈጸም ለእርግዝና አያጋልጥም፡፡
ሐ. የሰዉነትን ሙቀት በመለካት
• የሰዉነትን ሙቀት በመለካት ፅንስን ለመከላከል አንዲት ሴት 3እና 4 ወራት በተከታታይ የሰዉነቷን የሙቀት መጠን በየቀኑ መመዝገብ አለባት፡፡
• የሙቀት አለካኩ ሁኔታ ሁልጊዜ ጠዋት ከአልጋ ከመነሳትዋ በፊትና ምግብና መጠጥ ከመዉሰዷ በፊት በፊንጢጣ ወይንም በአፍ ቴርሞ ሜትሩን በማስቀመጥ ለ5 ደቂቃ ያህል አቆይቶ አዉጥቶ በማየት ምዝገባው ይከናወናል
• በዚህም መሰረት የሰውነንት ሙቀት ዝቅ ካለበት ቀን ጀምሮ ሙቀት ከፍ ብሎ እሰከሚቆይበት ጊዜ ድረስ ግብረ ስጋ ግንኙነት ቢፈጸም እርግዝና ላይከሰት ይችላል ፡፡

https://www.facebook.com/Danieltechnologist

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.