በህፃናት ላይ ለሚከሰቱ የተለመድ አደጋዎች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዴት እንሰጣለን?

(በዳንኤል አማረ)

✔ በስለት ነገሮች መቆረጥ(ቁስል)

venezuelan-baby-bottle-ban-3
በአነስተኛ ስለት መቆረጥና ቁስሎች የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዴት እንሰጣለን?
* በንጽህ ጨርቅ የሚፈሰውን ደም ማቆም
* ጨርቁ በደም ከተነከረ በባንዴጅ ከላይ በድጋሚ መጠቅለል
* ደሙ አሁንም ካልቆመ ቁስሉን ከልብ የተፈጥሮ አቀማመጥ ቦታ በላይ ከፍ ማድረግ ወይም ማንጠልጠል ።
* ደሙ ከቆመ በኃላ በንጽህ ውሃ እና ሳሙና ቁስሉን ማጠብ ወይም ማጽዳት።
* ፀረ ባክቴሪያ ጠብታ መድሃኒቶችን መጠቀም።
* ከዚያም ጨርቁን ሙሉ ለሙሉ በጨርቅ ወይም ባንዴጅ ጠቅልሎ ማሰር(የደም ዝውውር እንዳይስተጓጐል በጣም አጥብቀው አይሰሩት።

✔ የአፍንጫ መድማት
የአፍንጫ መድማት የተለመደና በአብዛኛው ህፃናቶች ፀሀይ ሲመታቸው ይከሰታል።
* ህፃኑ ቀጥ ብሎ እንዲቀመጥ ማድረግ ይህም የሚረዳው የህፃኑን አፍንጫ ቬይን ደም ግፊት በመቀነስ ደም መፍሰስ እንዳይኖር ያደርጋል።
* በአውራ ጣትና በጠቋሚ ጣት የህፃኑን አፍንጫ ቆንጥጦ በመያዝ በአፉ እንዲተነፍስ ማድረግ። አፍንጫውን ይዘው ከ 5-10 ደቂቃ መቆየት።
* በህፃኑ አፍንጫ አካባቢ በረዶ ለመያዝ መሞከር።
* በድጋሚ የአፍንጫ መድማት እንዳይኖር ህፃኑ አፍንጫውን እንዳይነካ ማድረግ።
★ የሚከተሉት ነገሮች የሚከሰቱ ከሆነ በአፋጣኝ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ያድርጉ፦
* ከ 2 ደቂቃ በላይ አፍንጫው የሚደማ ከሆነ
* ከደም መድማት በኃላ አደጋ፣ መውደቅ ወይም የራስ ቅል አካባቢ ጉዳት ካለ።

✔ ቃጠሎ(የእሳት አደጋ)
ለቀላል ቃጠሎ የሚከተለውን ያድርጉ
* የቃጠሎውን ቦታ በቀዝቃዛ የቧንቧ ውሃ ቢያንስ ለ 5 ደቂቃ ወይም ህመሙ እስቀሚቀንስ ያፍሱበት። ውሃ ውስጥ መንከርም ሌላ አማራጭ ነው።
* በቃጠሎ ቦታ በፍጽም በረዶ አያድርጉበት ምክንያቱም በረዶ በቁስሉ ላይ ማድረግ ሀይለኛ ቅዝቃዜ በቆዳችን ላይ ጉዳት ስለሚያስከትሉ ለበለጠ ጉዳት ይዳርገዋል።
* የቃጠሎው ቦታውን ስቴራይል(sterile) በሆነ ጐዝ ባንዴጅ ሳናጠብቅ በስሱ መሸፈን ይህም የሚጠቅመን የተቃጠለውን ቆዳችን አየር እንዲያገኝና ህመሙ እንዲቀንስ ያደርገዋል።
* ብናኝ ያለው ጥጥ በፍጽም አይጠቀሙ።
* ህመሙን ለመቀነስ አይቡፕሮፊን፣ አሲታሚኖፊን፣ አስፕሪን መጠቀም።
* ቀላል የቃጠሎ አደጋ ያለምንም ህክምና ይድናል። ነገር ግን ኢንፌክሽን እንዳይከሰት መከታተል ይኖርብናል። ለምሳሌ የህመም መጨመር፣ መቅላት፣ ትኩሳት፣ እብጠት ምልክቶችን መከታተል አለብን እነዚህ ምልክቶች ከታዮ ኢንፌክሽን ሊከሰት ስለሚችል የህክምና እርዳታ ማግኝት ያስፈልጋል።

✔ ስብራት
የአጥንት መሰበር ሲከሰት የህክምና እርዳታ ማግኝት ግድ ነው ነገር ግን የህክምና እርዳታ እስከምናገኝ የሚከተለውን እናድርግ
* የደም መፍሰስ ካለ በንጽህ ጨርቅ ወይም ስቴራይል ባንዴጅ በመጠቀም ማቆም።
* ህክምና እስከምናገኝ ህመሙን ለመቀነስ እና እብጠት እንዳይኖር በረዶ መጠቀም። በረዶውን ቀጥታ ቆዳችን ላይ ከማድረግ ይልቅ በጨርቅ ወይም ፎጣ ጠቅልሎ መጠቀም።
* ህፃኑ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግና ስብራትን በእንጨት ወይም በሌላ ነገር መጠገን ስልጠና እስካልወሰድ ድረስ ምንም እንዳይነኩት።
* ህፃኑ እራሱን ስቶ ከወደቀ፣ የትንፋሽ እጥረት ካለበትና ቶሎ ቶሎ የሚተነፍስ ከሆነ ህፃኑን በጥንቃቄ በጀርባው በማስተኛት ጭንቅላቱን ከሆዳችን በታች ዝቅ በማድረግ እና እግርን ወደላይ ከፍ በማድረግ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጠት ተገቢ ነው።

✔ መርዛማ ነገሮች መውሰድ
በተለያዮ ነገሮች ስንመረዝ ምልክቶቹን ማወቅ ተገቢ ነው።
* አፍና ከንፈር አካባቢ የማቃጠልና መቅላት ይታያል ይህም መርዛማ ፈሳሽ መጠጣታቸውን ጠቋሚ ነው።
* ከአፋቸው የሚወጣው የኬሚካል ሽታ በማሽተት በቀላሉ ይለያል ለማሳሌ ጋዝ ወይም የቀለም ማቅጠኛ(Thinner)
* ማስታወክ፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ግርታ ይጋጥማል።
★ የህክምና እርዳታ እስከምናገኝ ድረስ የሚከተሉትን እናድርግ
* የወሰድት መርዝ የቤት ማጽጃ ወይም ሌሎች ኬሚካሎች ከሆኑ እቃው ላይ የተፃፈውን ማንበብ
* መርዙ በልጅዎ ልብስ፣ ቆዳ ወይም አይን ላይ ከፈሰሰ ልብሳቸውን በፍጥነት ማውለቅና በቆዳ እና አይን ላይ ቀዝቃዛ ንጹህ ውሃ ማፍሰስ ወይም ለ20 ደቂቃ ሻወር እንዲወስድ ማድረግ
* ወደ ሆስፒታል ስንወስደው መርዙ የተቀመጠነትን እቃ ይዞ መሄድ

✔ ትንታ/መታፈን
ህፃናት ጎጂ ነገር መሆኑን ሳያውቁት ትናንሽ ነገሮችን ይውጣሉ፡፡ ትንታ የሚፈጠረው የዋጡት ቁስ አካል በጉሮሮ ወይም በመተንፈሻ ቧንቧ ውስጥ በሚገባበት ጊዜ ሲሆን በዚህ ጊዜ አየር እንዳይገባና ወደ አእምሮ የሚሄደውን ኦክስጂን ያግደዋል/ያቋርጠዋል፡፡
የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዴት ይሰጣል?
* ከህፃኑ ጀርባ በመቆም እጅዎን በልጁ ወገብ በማሳለፍ ልጁን በትንሹ ዘንበል ማድረግ
* ከልጁ እንብርት በላይ በአንድ እጅዎ ሆድን በስሱ መምታት
* ሁለት እጅዎን አጣምረው ይዘው ሆድን በደንብ ጫን ጫን ማድረግ
* የተቀረቀረው አካል እስከሚወጣ ድረስ ይደጋግሙት፡፡

መልካም ጤንነት!!
Like my Facebook page for more news.https://www.facebook.com/Danieltechnologist

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.