የልቅ ፍትወት ፊልሞች የሚያደርሱት ተጽዕኖዎችልቅ የፍትወት ፊልሞች በሕሊናችን ውስጥ ማስቀመጥ የሚፈልጉት ምን ዓይነት ሃሳቦችን ነው? መጥፎ ነገር በሕሊናችን ውስጥ ልክ እንደቆሻሻ መጥቶ ከተዘረገፈ፣ ሕሊናችን አስተሳሰቡ ሁሉ ይበከልና የጤናማ ሃሳብ ችግር እጦት ስቃይ ውስጥ እንገባለን። ሕሊና ደህንነቱ በሚገባ እንዲጠበቅ አስፈላጊ ነው የሚባለው ዋና ነገር ጤናማ በሆነ የወሲብ ሃሳብ ውስጥ መገኘት ነው። ይህ ጤናማ ሃሳብ ከውጭ ወደ ውስጥ በዘለቀ መርዛማ ሃሳብ ከተበከለ አስተሳሰባችን በአንድም ሆነ በተለያየ አቅጣጫ መጣመሙ አይቀሬ ነው። የአስተሳሰባችን አካሄድ የሚቃኘውም ከዛ አንጻር ይሆንና እንቸገራለን።

ልቅ የፍትወት ፊልምን ያየ ሁሉ ወዲያውኑ በሱሱ ይጠመዳል ማለት አይደለም። አንዳንዶች ቀድሞውኑ ሴትንና ወሲብን እንዲሁም ትዳርንና ልጆችን በተመለከተ የተመረዘ አስተሳሰብ በሕሊናቸው ውስጥ ተሞልተው ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች ሁሉንም እንዳለ መቀበል የሚወዱ በቀላሉ ስሜታቸው ወደፈለገው የሚመራቸው ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ የልቅ ፍትወት ፊልም አዘጋጅ ካምፓኒዎች እናንተ ማን ሁኑ ማን እነርሱ ግድ የላቸውም። እነርሱ የሚፈልጉት በዚህ ሱስ ወጥመድ ውስጥ ገብታችሁየምርቶቻቸው ጥገኛ እንድትሆኑ ብቻ ነው። ለነርሱ ትልቁ ጉዳያቸው ገበያቸውና ትርፋቸው ብቻ ነው።

ዶ/ር ቮክቶር ክላይን የተባሉ ምሁር ሱስ በውስጣችን ሊያድግ የሚችልባቸውን ደረጃዎች አስቀምጠዋል። ከነርሱም መካከል አራቱ የሚከተሉት ናቸው። በሱሱ መጠመድ፣ የሱሱ ፍላጎት ማደግ፣ ሱሱን በጣም የመላመድ ስሜትና በመጨረሻም በተግባር ውስጥ መውደቅ ናቸው። በተጨማሪ ደግሞ ከነዚህ ውጭ በልቅ የፍትወት ፊልም ሱስ ለመጠመድ ቀዳማይ ምክንያት የሚሆን ደረጃ አለ ፤ በልጅነት ጊዜ ለዚህ ፊልም መጋለጥ የሚለውን መጨመር ይቻላል። እስቲ እነዚህን ደረጃዎች በዝርዝር እንቃኛቸው።

በልጅነት ዕድሜ ለልቅ የወሱብ ፊልሞች የመጋለጥ ደረጃ
ብዙዎች በዚህ የልቅ ፍትወት ፊልም ሱስ የተጠመዱ ሰዎች ታሪካቸው ሲጠና ገና ከልጅነታቸው ጊዜ ጀምሮ ለዚህ ፊልም እይታ ስለተጋለጡ እንደሆነ ተደርሶበታል። ይህንን ልቅ የሆነ የወሲብ ፊልም ማየት የጀመሩት ገና በህጻንነታቸው ነው። የቤታቸውን ደፍ የረገጠው በሕይወታቸው ማለዳ ላይ ነው። ይህ በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው።

በልቅ ፍትወት ሱስ የመጠመድ ደረጃ

በተደጋጋሚ የልቅ ፍትወት ፊልምን ማየት ስናዘወትር፣ ፍላጎቱ የሕይወታችን አንዱ ክፍል መሆን ይጀምራል፤ ስለዚህ በዚህ ወቅት ወጥመድ ውስጥ ገብታችኋልና በቀላሉ ከወጥመዱ መላቀቅ አትችሉም።

የሱሱ እያደገ መምጣት

አንዳንድ የልቅ ፍትወት ምሥሎችን በማየት ትጀምራላችሁ፤ ቀድሞ ያ የምታዩት እንዳላስጠየፋችሁና እንዳልጠላቸሁት ሁሉ አሁን ማድነቅና ራሳችሁንም በስሜት ውስጥ መሆን ትጀምራላችሁ።

ከሱሱ ጋር በጣም የመላመድ ደረጃ

በዚህ የሱስ ደረጃ ላይ ስታዩት የሚያስደንቃችሁ ምስል ስሜት አልሰጥ እያላችሁ ትቸገራላችሁ፤ በጊዜው ስታዩት ስሜት ውስጥ ሲከታችሁ የነበረው ምስል አሁን ምንም ስሜት አልሰጣችሁ ይላል። በዚህ የተነሳ መበሳጨት መነጫነጭ ትጀምራላችሁ። የበለጠ የሚያስደንቅ ፊልም እንዲመጣላችሁ ትፈልጋላችሁ፤ በቀላሉ አታገኙም፤ ይህም በባህርያችሁ ላይ ከባድ ለውጥ ማምጣት ይጀምራል።

የደረጃው ማደግ

ይህ በወንዶች ላይ የሚታየው እጅግ በጣም የሚያስደነግጠው ደረጃ ነው። በዚህ ደረጃ በሱሱ የተጠመደው ሰው በቀጥታ ያየውን በተግባር ለመግለጽ የሚፈልግበት ደረጃ ነው። አንዳንዶች በቀጥታ ተንቀሳቃሽ ፊልሙን ሳይመለከቱ ከሥዕልና ከፕላስቲክ ምሥሎች እይታ በኋላ በቀጥታ ወደተጨባጩ ዓለም ዘው ብለው ይገባሉ። ይህም ራሳቸውን ለጥፋት ከመዳረግ ባለፈ የሌሎችንም ሕይወት ወደ ጥፋት ይልካሉ።

ምን ማድረግ ይበጃል

ባለሙዎቹ እንዲህ ይመክራሉ፡- የመጀመሪያው እርምጃ ፖርኖግራፊ ሱስ ጋር እያታገላችሁ እንደሆነ አምናችሁ ተቀበሉ። ብዙዎች የሚያልፉበት፣ ያለፉበትና እያለፉም ያሉበት ነገር ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንዶች በሱሱ ተለክፈው በተለያየ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በእርግጥም የሚያስደንቅ ክስተት አይደለም። የልቅ ወሲብ አምራች ኩባንያዎች እናንተን የመሳሰሉትን ለማጥመድ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ማጥፋታቸውን አትርሱ። ምናልባትም አንዳንዶቻችሁ ከዚህ በፊት በሕይወታችሁ ባለፈ የወሲብ ትንኮሳ ምክንያት ወደዚህ ሱስ ተገፋፍታችሁ ይሆናል። ሆኖም ከዚህ በኋላ ራሳችሁን ከዚህ ቀንበር ነጻ ለማወጣት ብቻችሁን ለመታገል እንደማትችሉ ማወቅ አለባችሁ። እርዳታ ያስፈልጋችኋልና ባለሙያን ለማማከር ችላ አትበሉ።

THE END

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.