የአኗኗር ዘይቤዎ ላይ ለዉጥ ማድረግ የስኳር ህመምን ለመከላከል ትልቁን እርምጃ/ጉዞ እንደጀመሩ ይታሰባል፡፡ እናም እስከ አሁን ድረስ የአኗኗር ዘይቤዎ ላይ ለዉጥ አልጀመሩ ከሆነ ብዙም ስላልረፈደ ዛሬዉኑ መጀመር ይችላሉ፡፡

በጣም የተለመደዉና በብዛት ያለዉ የስኳር ህመም አይነት 2ኛ አይነቱ (type 2 diabetes) ሲሆን ህመሙ እንዳይይዝዎ መከላከሉ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መንገዶች ይተግብሩዋቸዉ፡፡
1. ተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን እነርሱም
• ክብደትዎን ለመቀነስ
• የደም የስኳር መጠን ለመቀነስና
• የስኳር ህምተኛ ከሆኑና ኢንሱሊን እየወሰዱ ከሆነ የሰዉነትዎ ሴሎች ላይ እንሱሊኑ በደንብ እንዲሰራ ያነቃቃቸዋል፡፡

2. የፈይበር/ቃጫነት/ ይዘታቸዉ ከፍ ያሉ ምግቦችን አዘዉትሮ/በብዛት መመገብ፡- ይህም
• የሰዉነትዎን የስኳር ቁጥጥር በማሻሻል ለስኳር ህመም ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ ይረዳል
• ለልብ ህመም ተጋላጭነትዎን ይቀንሳል
• የጥጋብ ስሜት እንዲሰማዎ በማድረግ የሰዉነት ክብደትዎን ለመቀነስ የሚያግዝዎት ሲሆን ጥሩ የፋይበር ምንጭ ከሆኑ ምግቦች ዉስጥ አትክልትና ፍራፍሬ፣ጥራጥሬ፣አተርና ኦቾሎኒና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡

3. ጥራጥሬን በብዛት መመገብ
4. ክብደትዎ ከመጠን በላይ ከሆነ ትርፍ የሆነዉን መቀነስ
5. አላስፈላጊ የሆኑ ምግቦችን በመተዉ ጤናማ የአመጋገብ ምርጫ ማድረግ፡- የካርቦሃይድሬት/ሀይል ሰጪ ይዘታቸዉ መጠነኛ የሆኑ ምግቦችን ማዘዉተር የሰዉነት ክብደትዎን ለመቀነስ የሚረዳ ቢሆንም ለወደፊቱ የስኳር ህመምን የመከላከል ብቃታቸዉ ወይም ማምጣት መቻላቸዉ አልተረጋገጠም፡፡ ስለሆነም የተወሰነ የምግብ አይነትን መተዉ/መገደብ ከምግቡ ማግኘት የሚገባዉን አላስፈላጊ ንጥረነገር ሊያሳጣዎ ስለሚችል በአጠቃላይ ምግብን አፈራርቆና አመጣጥኖ መመገብ ተገቢ መሆኑ ይመከራል፡፡

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚያስፈልግዎ መቼ ነዉ?
እንደ አሜሪካን የስኳር ህመምተኞች ማህበር አንድ ሰዉ የስኳር ምርመራ ማድረግ ያለበት
• እድሜዉ ከ45 አመታትና ከዚያን በላይ ከሆነና ክብደቱ ከመጠን በላይ ከሆነ
• እደሜዉ ከ45 አመታት ሆኖ ክብደቱ ከመጠን በላይ ሆኖ በተጨማሪ ለሁለተኛዉ የስኳር አይነት ተጋላጭነትን ሊጨምሩ የሚችሉ እንደ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤና በቤተሰብ የስኳር ችግር ያለበት ከሆነ

11099980_500100960154129_4049286794316438973_n

8896 Hello Doctor Ethiopia

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.