የቀለሞች ሳይኮሎጂ/Color Psychology)

(በዳንኤል አማረ ©ኢትዮጤና)

1. ቀይ(Red)
11693858_495368177284474_1315493328730807015_nየምግብ ፍላጎትን ይቀሰቅሳል ወይም ይጨምራል፣ አእምሮአችን ለነገሮች በጥልቅት ትኩረት እንዲያደርግ ያነሳሳል ለዚህም ነው እንደ ማክዶናልድ አይነት ትላልቅ ድርጅቶች የምርታቸው ቀለም ምርጫ ያደረጉት፡፡ በቅርብ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀይ የለበሱ አስተናጋጆች ጠቀም ያለ ጉርሻ(ቲፕ) እንደሚያገኙ ተደርሶበታል የዚህ ምክንያት አእምሮአችን በቀይ ቀለም በቀላሉ ስለሚሳብ ነው፡፡ ቀይ ቀለም ፈተና እና ስራ የመስራት አቅምን ይቀንሳል የዚህ ምክንያት ቀይ ቀለም ከአደገኛ ነገሮች ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው፡፡

2. ሰማያዊ(Blue)
በአይናችን ከምናየው ነገር ውጪ አእምሮአችን ሰፋ አድርጎ እንዲያስብ ያበረታታል በተጨማሪም አምራች/ውጤታማ እንድንሆን እና ስኬትን ይጨምራል፡፡ የምግብ ፍላጎታችን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

3. አረንጓዴ(Green)
ውስጣዊ ሰላም እና መረጋጋትን ይጨምራል ነገሮች እንደሚሆኑ እምነታችን እንዲጨምርና ጥሩ ውጤት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ በ2012 እ.ኤ.አ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በአረንጓዴ ጽሁፍ የተጻፈባቸው የታሸጉ ምግቦች የጤናማነት ስሜት እንዲሰማን የማድረግ ተጽእኖ ስላላቸው በሚገርም ሁኔታ በብዛት እነዚህ ምርቶች ይሸጣሉ፡፡

4. ቢጫ(Yellow)
በቀለሞች ዝርዝር ከሚገኙ ቀለሞች ውስጥ የደስታን ስሜት የሚፈጥር የቀለም ዓይነት ነው፡፡ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን እና ሰውነታችን እንዲጠቀምበት የማድረግ ሁኔታን ይጨምራል፡፡ የሰውነታችንን ጉልበት/ብርታት ይጨምራል፡፡ ህፃናት ለቢጫ ቀለም በሚጋለጡበት ጊዜ የበለጠ እንዲያለቅሱ ያደርጋቸዋል ስለዚህ የህፃናት ማቆያ እና መማሪያ ቦታዎች በዚህ ቀለም ማስዋብን ማቆም አለብን፡፡

5. ብርቱካናማ(Orange)
ሀወይወትን የሚዘራ ቀለም ሲሆን አእምሮን የሚቀሰቅስ እና የሰዎችን ትጋት፣ ጉጉት እና ስሜት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ደማቅ ሲሆን ሞቅታን የሚያሳይ ሲሆን ነጣ ያለ/የፈዘዘ ሲሆን ደግሞ ማስጠንቀቅን እና ሰውየው ሁልጊዜ ንቁ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

6. ሮዝ/ፒንክ(Pink)
የመረጋጋትና የሞቅታ ቀለም ነው፡፡ የፍቅር፣ የቆንጆ ሴታሴትነትና የእናትነት መገለጫ ቀለም ነው፡፡ አእምሮን የመያዝ አቅም ስላለው የማረሚያ ቤቶችየማደሪያ ግድግጋዎች ሮዝ ቀለም እንዲቀቡ ይደረጋል፡፡ ይህም በጣም አደገኛ የህግ ታራሚዎች እንዲረጋጉና እንዳይረብሹ ያደርጋል፡፡

7. ወይነጠጅ(Purple)
የንጉስነት፣ የባለጠግነት እና የስኬት ቀለም ነው፡፡ አእምሮን በቅንጦት ካባ የሚያጎናጽፍ ሲሆን ብዙ ንጉሶች ወይነጠጅ ቀለም ያለው ልብስ ይጠቀማሉ፡፡ ፈዛዛ የሆነ ወይነጠጅ ቀለም የተበሳጩ/የተናደድ ሰዎችን በማረጋጋት ዘና እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡

8. ጥቁር(Black)
በጣም የሚያስጨንቅ/የሚረብሽ ቀለም ብዙ ጊዜ ሞት እና ሃዘንን ይወክላል፡፡ ጥንታዊ ግብፃዊያን ጥቁር ቀለምን የህይወት እና እንደገና መወለድ ተማሳሌት ያደርጉት ነበር፡፡

9. ነጭ(White)
የንጹህነት፣ የታማኝነትና የባዶነት ቀለም ነው በተጨማሪም የሠላም ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በሰዎች ህሊና ውስጥ ፍጹም ንጹህ ከምንም ነገር የፀዳ ህሊናን ለመፍጠር ይረዳል ለዚህም ነው አብዛኛዎቹ ሆስፒታሎችና የሆስፒታል ሠራተኞች ነጭ ቀለምን የሚጠቀሙት፡፡

10. ወርቃማ(Golden)
የብረቶች ቀለም ሲሆን ከፍቅር፣ ጥበብ፣ ጥራት፣ ሳቢነት እና ሃብት ጋር ጥብቅ የሆነ ቁርኝት አለው፡፡

መልካም ጤንነት!!
Source- www.facebook.com/EthioTena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.