10 የጉበት በሽታ ምልክቶች

(በዳንኤል አማረ እና ዳግማዊ ዳንኤል ©ኢትዮጤና)

11222462_494858974002061_4867890716416426509_nጤናማ የሆነ ህይወት ለመምራት ጉበት በጣም አስፈላጊ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ የጉበት የመጀመሪያ ተግባሩ የተመገብነውን ምግብ በመሰባበር የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ማውጣት እና የምግብ መፈጨትን ያግዛል፡፡ ለጉበታችን ጤንነት እንድንጨነቅ እና እንድንጠነቀቅለት የሚያደርግ በርካታ የሆኑ ተግባሮችን/ስራዎችን ጉበታችን በመወጣት ይጠቅማል፡፡ የሚከተሉት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፦
1. የቆዳ ቀለም ለውጥ
በአይናችን ልናየው የምንችለው የጉበት ጉዳት/በሽታ ምልክት የቆዳ ቀለም ለውጥ ነው፡፡ የቆዳዎ ቀለም ቢጫ ወይም የገረጣ/የፈዘዘ እየሆነ ከመጣ ጉበትዎ በትክክል ስራውን እየተወጣ አይደለም ማለት ነው ስለዚህ እርዳታ ያስፈልግዎታል ማለት ነው፡፡ ይህ የቆዳችን ቀለም ወደ ቢጫነት መቀየር ዋነኛ ምክንያት ጉበታችን መርዛማ ነገር(ቶክሲን) ስለማይለቅ ሲሆን የዚህ መርዛማ ነገር አለመለቀቅ ቢሊሩቢን በቆዳዎች አካባቢ እንዲጠራቀም ያደርገዋል፡፡

2. የሆድ ህመም
ጉበታችን የሚገኝው በጎድን አጥንታችን አካባቢ ሲሆን የጉበታችን ጤናማ አለመሆን በሆዳችን እና በጎድን አጥንታችን አካባቢ ከፍተኛ የህመም ስሜት ይፈጥራል፡፡

3. በተደጋጋሚ ማግሳት
በሆድ/አንጀት በአየር መነፋት ምክንያት በተደጋጋሚ በግሳት የሚሰቃዩ ከሆነ ጉበታችን ምግብን ለመፍጨት የሚሆን ኢንዛይም ማምረት ተስኖታል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም የምግብ መፍጨት ስርዓታችን በጉበት ችግር ምክንያት ይታወካል፡፡

4. የድካም ስሜት መሰማት
ጉበት ምግብን በሚሰባብርበት/እንዲፈጭ በሚያደርግበት ጊዜ በየቀኑ ስራችንን ለመስራት የሚጠቅም ሃይል/ጉልበት እንድናገኝ ያደርጋል፡፡ በቀላሉ የምንደክም ከሆነ የጉልበት ማጣት ምልክት ነው ይህም ጉበታችን ሥራውን በትክክል አለመወጣቱን ያሳያል፡፡

5. የሽንት ቀለም መለወጥ
ጉበታችን መጎዳት በሚጀምርበት ጊዜ የሽንታችን ቀለም ጠቆር ወዳለ ቢጫ ይቀየራል አንደንዴም ወደ ደም ቀለም ሊወስደው ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህ የቀለም ለውጥ ከፈሳሽ እጥረት እንደመጣ ያስባሉ በቂ ውሃ ጠጥተው ይህ የቀለም ለውጥ ከተከሰተ የኩላሊት ጤና ታውኳል ማለት ነው፡፡

6. ቆዳን ማሳከክ
የጉበት በሽታ ማሳያ ከሆኑት አንዱ የቆዳ ማሳከክ ነው፡፡ በቆዳዎ ላይ የሚያሳክክ ቦታ ካለ እና ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ከመጣ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡

7. ማቅለሽለሽ
የምግብ አለመፈጨት እና የአሲድ አለመመጣጠን የጉበት ጉዳት ምልክቶች ናቸው፡፡ የምግብ አለመፈጨት እና ማቅለሽለሽ የአመጋገብ ሁኔታችንን በመቀየር የማይስተካከል ከሆነ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡ እየተባባሰ ሲሄድ ማስታወክ ደረጋ ላይ ይደርሳል፡፡

8. የክብደት መቀነስ
ድንገተኛ የሆነ የክብደት መቀነስ እንደ ጉበት ችግር ሊታይ ይችላል፡፡ ሳይፈልጉ ክብደት የሚቀንሱ ከሆነ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሊሆን ይችላል ይህም የሚሆነው ጉበታችን ደካማ ስለሚሆን ሲሆን ቀጭን እና የተጎዳ ሰው እንድንሆን ያደርገናል፡፡

9. ፈሳሽን መያዝ
በተላያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ፈሳሾች መቋጠር/መያዝ በተለይ በእግር አካባቢ የደካማ ጉበት ምልክት ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ኢዴማ() ይባላል እብጠት ይመስላል፡፡ ይህ እብጠት በጉልነት፣ እጅ አና እግር ጣቶች አካባቢ ይከሰታል፡፡ ያበጡትን ጣቶች ስንጫናቸው ጊዜ ለጥቂት ሰከንዶች ወደውስጥ ገብተው/ጎድጉደው ይቀራሉ፡፡

10. የአይነ ምድር ቀለም መቀየር
የአይነ ምድር ቀለም መቀየር አንድ የጉበት ችግር ምልክት ነው፡፡ ትንሽ ደም ከአይነ ምድር ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣ ከሆነ በፍትነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ አለብን፡፡ ሌላው ከአይነምድር ጋር የተያያዘ የጉበት ችግር ምልክት የሆድ ድርቀት ነው፡፡

መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ www.facebook.com/EthioTena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.