(በዳንኤል አማረ እና ዳግማዊ ዳንኤል©ኢትዮጤና)

11008793_493220774165881_274997350542139307_nሁላችንም መቸም ልጅ እያለን ማስቲካ ሳናኝክና እየነፋን ሳንጫወት አላደግንም ይህ ልጅ እያለን እየነፋን ብሎም እያኝክን ስንደሰትበት የነበረው ማስቲካ ለሰውነታችን 10 ጥቅሞችን ይሰጠናል እነዚህን ጥቅሞች ሳናውቅ ማስቲካን ያኝክንበት አያሌ ዘመናትን ትተን አሁን ለእኛ ያለውን ጥቅም አውቀን ማኝክ እንድንጀምር ማለት ነው፡፡ የሚሰጠን ጥቅሞች እነሆ፦

1.ጭንቀትን ማስወገድ
በተለያዩ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ማስቲካ የሚያኝኩ ሰዎች ከማያኝኩት/ከማይጠቀሙት በተሻለ ሁኔታ ከገቡበት ጭንቀት በፍጥነት ይወጣሉ፡፡


2.ክብደትን ለመቀነስ
የተለያዩ ጣዕም ያላቸው ማስቲካዎችን ለማኝክ ከፍተኛ ካሎሪ/ጉልበት እንድናወጣ ስለሚያደርገን ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡


3.የምግብ ስልቀጣን ያፋጥናል
ማስቲካ ማኝክ በአፋችን ውስጥ የምራቅ መጠን እንዲጨምር/እንዲበዛ ያደርጋል ይህ ሁኔታ የምግብ ስልቀጣን/መፈጨትን የማፋጠን ከፍተኛ ሀይል አለው፡፡


4.ሀሳብን ለመሰብሰብ ይረዳል
ማስቲካ ማኝክ ከማንኛውም ጊዜ በላይ እንድንነቃቃ እና ሃሳባችንን እንድንሰበስብ ያደርጋል፡፡ በተለይ በስብሰባ እና በመማሪያ ክፍል ውስጥ(ምንም እንኳን መምህሮች ፈቃደኛ ባይሆኑም) ማስቲካ ማኝክ ነቃ ብለንና ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን እንድንከታተል ይረዳናል፡፡


5.የትውስታ አቅምን ይጨምራል
ማስቲካ በምናኝክበት ጊዜ አማካይ የልብ ምታችን ይጨምራል ይህ ሁኔታ ወደ አእምሮአችን የሚገናውን የኦክስጂን መጠን ይጨምረዋል፡፡ ስለዚህ አእምሮአችን በብቃትና በትኩረት ስራውን እንዲወጣ/እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡


6.መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል
ማስቲካ ማኝክ መጥፎ የአፍ ጠረንን ከመከላከሉም በላይ ጥርሳችን እንዳይበሰብስ ይረዳል፡፡ በምናኝክበት ወቅት ከፍተኛ ምራቅ ስለምናመነጭ በአፋችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ለአፍ ጠረንና ለጥርስ መቦርቦር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡


7.የሲጋራ ሱስን ለማቆም ይረዳል
የተለያዩ የሲጋራን ሱስ ለማቆም የሚረዱ ማስቲካዎች በውስጣቸው ኒኮቲን የያዙ በገበያ ላይ ይገኛሉ እነዚህን ማስቲካዎችን በማኝክ የሲጋራ ሱስን ማቆም ይቻላል፡፡


8.ካሎሪን ለማቃጠል ይረዳል

ማስቲካ በምናኝክበት ወቅት በመንጋጋ አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ይሰራሉ፡፡ እንደሚታወቀው ስራ ለመስራት ሀይል ያስፈልጋል ስለዚህ የመንጋጋ ጡንቻዎች በሠዓት 10 ካሎሪ ያህል ይቀንሳሉ ይህ ደግሞ ክብደትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያበረክታል፡፡


9.የገርድ በሽታን ይከላከላል
ይህ የበሽታ አይነት በጨጓራችን ውስጥ ያለው አሲድ(HCL) በጉሮሮ/የምግብ ቧንቧዎች ወደ ላይ ሲመለስ ልባችን አካባቢ የማቃጠል ስሜት የሚፈጥርብን በሽታ ነው፡፡ ይህን በሽታ በቀላሉ ለመከላከል ማስቲካ በማኝክ በምራቅ አማካኝነት ወደ ላይ የሚመጣውን አሲድ ጨጓራ ውስጥ ማስቀረት ይቻላል፡፡

10.የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን ለማግኝት
ማስቲካ በውስጡ የተለያዩ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ለምሳሌ እንደ ቫይታሚን ሲ በውስጡ ይዟል፡፡ በተጨማሪም የአፍ ውስጥ ባክቴሪያን የሚያጠፉ እንደ ዛይሊቶል() አይነት ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡
መልካም ጤንነት!!
ለበለጠ የጤና መረጃ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉት
www.facebook.com/EthioTena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.