በአፍንጫችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ምልክቶችን ለማስወገድ የሚረዱ 8 ዘዴዎች

afenchaበፋሲካው ታደሰ

በቆዳችን ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ምልክቶች በቀላሉ ልናስወግዳቸው እየቻልን ለእይታ የማይስብ ቆዳ ያላብሱናል።

በቆዳ ላይ የሚወጡትን ምልክቶች በቀላሉ ማጥፋት ይቻላል ማለት ግን አንድ የተሳሳተ አካሄድ በቆዳችን ላይ ጠባሳ ጥሎ ሊያልፍ አይችልም ማለት አይደለም።

ስለሆነም የቆዳችንን ጤና መጠበቅ የዘወትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል።

በአፍንጫችን አካባቢ ጥቋቁር ምልክቶች ከታዩ ብዙ መጨነቅ አይገባም የሚለው የስታይል ክሬዝ ድረ ገጽ ዘገባ የሚከተሉትን ቢተገብሯቸው ጥሩ ውጤት ያገኛሉ በማለት አስቀምጧቸዋል።

1. የፊት ንጽህናን መጠበቅ

በየቀኑ ከ2 እስከ 3 ጊዜ ፊታችንን መታጠብ የፊት ቆዳን ጤንነት ለመጠበቅና በአፍንጫ ላይ የሚወጡ ጥቋቁር ምልክቶችን ለማጥፋት አይነተኛ ሚና አለው።

ጥቋቁር ምልክቶች የወጡበትን የአፍንጫችን ክፍል የሎሚ ጭማቂ መቀባትም ይመከራል።

2. የትራስ ልብሶችን መቀያየር

3. የጥርስ ሳሙና

የጥርስ ሳሙናን መቀባት ጥቋቁር ምልክቶችን ለማጥፋት እንደሚያግዝ ይነገራል።

የጥርስ ሳሙናውን በተጎዳው ወይም ጥቁር ምልክቶች በወጡበት ክፍል ላይ በመቀባት ለ10 ደቂቃ መቆየትና በቀዝቀዛ ውሃ መታጠብ ከችግሩ ለመገላገል ከፍተኛ እገዛ እንዳለው መረጃው አመላክቷል።

4. ስቲም

በሞቀ ውሃ መታጠብ አልያም ስቲም ውስጥ መግባትም ለችግቱ መፍትሄ ነው ተብሏል።

ከእንፋሎቱ የሚወጣው ሙቀት የቆዳችን ቀዳዳዎች እንዲከፈቱ ስለሚያደርግ በአፍንጫችን ላይ የሚከሰቱ ጥቋቁር ምልክቶችን ለማጥፋት ይረዳል።

5. የውበት መጠበቂያዎችን ከመኝታ በፊት ማስወገድ

አንዳንድ ሴቶች ቀን ላይ ውበታቸውን ለመጠበቅ የተጠቀሟቸውን ሜካፖች ሳያስወግዱ ወይንም ሳይታጠቡ ይተኛሉ።

ይህም ለቆዳ ጤና አደገኛ መሆኑ የሚነገር ሲሆን በአፍንጫ ላይም ጥቁር ምልክቶች እንዲወጡ ያደርጋል።

ማንኛውም የውበት መጠበቂያ ለቆዳችን ተስማሚ መሆኑን ማረጋገጥና ከተጠቀምነው በኋላም ከመኝታ በፊት መታጠብ ለቆዳችን ጤንነት መዘየድ ነው።

6. ማር

ፊታችንን አልያም አፍንጫችን ማር መቀባት ጥቁር ምልክቶችን በማጥፋት ንጹህ ቆዳን ያጎናጽፋል።

በቀን ለሁለት ጊዜ አፍንጫችን አንድ ማንኪያ ማር በስሱ በመቀባት ከአምስት ደቂቃ በኋላ በቀዘቃዛ ውሃ መታጠብ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ከችግሩ ለመውጣት ያግዛል።

7. የእንቁላል ነጩ ክፍል

በርካታ ሰዎች የእንቁላል ነጩን ክፍል በመቀባት የቆዳቸውን ውበት ሲጠብቁ ይስተዋላል።

ጥቁር ምልክቶች የወጡበትን የፊታችንን ክፍል የእንቁላል ነጩን ክፍል በእጣታችን በመቀባት ለ10 ደቂቃ ያህል እንዲደርቅ መጠበቅ፤ ከዚያም በእርጥብ ጨርቅ ማጽዳት።

8. አረንጓዴ ሻይ

አንድ ማንኪያ የአርንጓዴ ሻይ ቅጠል ከውሃ ጋር በመበጥበጥ ፊታችንን መቀባትም ቆሻሻዎችን በማስወገድ የጠራ ቆዳን ያላብሰናል።

ከላይ የጠቀስናቸው ነጥቦች በአፍንጫ ብሎም በፊታችን ላይ የሚታዩ ጥቋቁር ምልክቶች በቀላሉ ለማጥፋት የሚረዱ ሲሆን ችግሩ ባስ ሲልም በህክምና ተቋማት የሚታዘዙ ቅባቶችና መድሃኒቶች ይኖራሉ።

ምንጭ:- http://www.stylecraze.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.