ሊያገቡት የሚፈልጉትን ሁነኛ ሰው ማግኘትዎን የሚያሳዩ 10 ምልክቶች!

ከፍቅረኛዎ ጋር የፍቅር ግንኙነት ከጀመሩ ዋል አደር ብለዋል እንበል፤ በተደጋጋሚ የሚነሳብዎት ጥያቄም መቼ ነው እናንተ የምትጋቡት? የሚለው ሊሆን ይችላል።

ይሁንና መሰል ጥያቄዎች ሲደጋገሙ ምቾትን ሊነሱ እና ስጋትንም ሊደቅኑብዎት የሚችሉበት ዕድልም ሰፊ ነው።

ታዲያ ጋብቻ ትልቅ ውሳኔን የሚጠይቅ እንደመሆኑ ሊያገቡት የሚፈልጉትን ሰው ማግኘትዎን የሚያረጋግጡልዎን ነጥቦች እንካችሁ የሚለው ደግሞ ሰልፍ ዶት ኮም የተሰኘው ድረ ገፅ ነው።

1.ስለምንም ነገር ሲያወሩ ምቾት ይሰማዎታል፦

ከፍቅር ጓደኛዎ ጋር የትኛውንም አይነት ርዕስ አንስተው ከመወያየት ወደኋላ አይሉም ፣ ሲወያዩ ምቾት ይሰማዎታል።

ስጋትዎን፣ ግምትዎን ውጥንዎንም ሆና ሌላውን ከመግለፅ አያመነቱም፤ ይህን በማለቴ ትዝብት ላይ እወድቅ ይሆን የሚለው ፍራቻም ከአጠገብዎ ዝር አይልም።

2. ስለምንም ጉዳይ በቅድሚያ ለማዋየት ይደፍራሉ፦

ከመስሪያ ቤትዎ ያገኙትን የስራ ዕድገትንም ሆነ ስለፍላጎትዎ፣ ስለገጠመዎ ችግርም ሆነ መልካመ አጋጣሚ ለማውጋት በመጀመሪያ የሚመርጡት ለፍቅረኛዎ ይሆናል።

3.ብዙ ጊዜዎን ከፍቅረኛዎ ጋር ማሳለፍን ይመርጣሉ፦

ከፍቅረኛዎ ጋር ሰፊውን ጊዜዎን እንደማሳለፍ የሚያረካዎት ነገርን ያጣሉ።

አብሮነታችሁንም ሁሌም ቢሆን ይመኙታል።

ቲያትርም ሆነ ሲኒማ ቤት መሄድ ፣ በቤትዎ ቴሌቭዥን መመልከትም ሆነ የእግር ጉዞ ማድረግ ፣ ጨረቃ ማየትም ሆነ ሌላ ሌላ ነገር ለማድረግ ምርጫዎ አሁንም ፍቅረኛዎ ይሆናል።

4.ይከባበራሉ ፣ ይደጋገፋሉ፦

ድካምዎን ለሌላ ሰው አይነግሩም ፍቅረኛዎም ቢሆን ይህንኑ በእርስዎ ላይ ለማድረግ አቅሙ አይኖራቸውም።

ዝንባሌያቸውን፣ ምን እንደሚያስደስታቸው ምን እንደሚያስከፋቸው ያውቃሉ፤ በመሆኑም አንዳያዝኑብዎ ይጠነቀቁላቸዋል።

ያከብሯቸዋል፣ ይታመኑላቸዋል፣ ከአጠገብዎ በስራም ሆና በሌላ ምክንያት ሲርቁም ናፍቆትዎን መቋቋም ሲሳንዎ ራስዎን ያገኙታል።

5.ወደፊት አብረው እንዴት እንደሚዘልቁ ያነሳሉ፦

ወደፊት ግንኙነትዎ በእንዴት ባለ ሁኔታ መቀጠል እንደሚኖርበት ያለ ፍርሃት ይገልፃሉ።

ምናልባትም ለመጋባት እንደሚያስቡ እና ይህም በምን ያህል ጊዜ ቢከናወን ምርጫዎ እንደሆነም ከመናገር ወደኋላ አይሉም ነው የተባለው።

6.የፍቅር ጓደኛዎ ከእነጉድለትዎ ሊቀበሉዎ ዝግጁ ናቸው፦

የፍቅር አጋረዎ በጥንካሬዎ ብቻ ሳይሆን ደካማ ጎንዎን አውቀው ያን በሂደት እንደሚቀርፉት በማመን ጭምር ነው ግንኙነታቸውን ከእርስዎ ጋር የሚወጥኑት።

ፍቅረኛዎ እርስዎን ባለዎት ሃብት እና ንብረት ሳይሆን የሚመዝኑዎት በአመለካከትዎ እና ለሴቶች በሚሰጡት ከበሬታ ይሆናል።

7.ፍቅረኛዎ ከቀድሞ የፍቅር ህይወታቸው መላቀቃቸው ያስታውቃል፦

ፍቅረኛዎ የቀድሞ የፍቅር ህይወታቸውን የረሱ እና ለአዲስ ፍቅር የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡ አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ ዝግጁነቶችን ያነቡባቸዋል።

8.ለፍቅር ግንኙነት መፈላለጋችሁ ያሳብቅባችኋል፦

ምንም እንኳን ለፍቅረኛዎ ካለዎ ከበሬታ የተነሳ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነትን ከጋበቻ በፊት መፈፀሙ ባይዋጥልዎም ለፍቅር ግንኙነት የሚፈልጉት (ጓት) አይነት ሰው መሆናቸውን አይን ለአይን ስትጋጩ አልያም የመደንገጥ ስሜት ድንገት ሲሰማዎት ራስዎን ያገኙታል።

9.ግጭቶችን ጤናማ በሆነ መንገድ ለመፍታት ያለ ዝግጁነት፦

የትኛውም አይነት የሃሳብ ግጭት ሲፈጠር በሰከነ እና በሰለጠነ መንገድ በመወያያት ለመፍታት እርጋታ እና ፍላጎት ይኖርዎታል።

ኩርፊያንም ሆነ ግጭትን በአጭሩ ለመቅጨት ወኔውንም ሆነ ትዕግስተ እንዳለዎት በተለያየ መንገድ ያረጋግጣሉ።

10. ፍቅረኛዎ ይሰሙዎታል፦

ፍቅረኛዎ እርስዎ ሲናገሩ በፍላጎት እና በትዕግስት ማድመጥ ምርጫቸው ነው።

ለፍቅረኛዎ ሊሰጡት የሚችሉት ትልቁ ቦታም ማድመጥ መሆኑን እርስዎም በሚገባ ይገነዘባሉ።

በዚህም ምክንያት ለመስማት ብዙ ጊዜዎን ለመናገር ደግሞ ጥቂቱን ይጠቀማሉ።

በሳሙኤል ዳኛቸው

1 COMMENT

  1. It is really an incredible topic.but not only solution,the negative and positive effects are needed so please explain the negative out comes must be explained in detail.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.