ነፍሰጡር እና እርግዝና

የእርግዝና ወቅት በሳምንታት ነው የሚቆጠረው

thirst/thirstyለማርገዝ ከፍተኛ እድል ያለበት ወቅት በወርአበባ ዑድት ግማሽ ላይ ነው። እርግዝና ወቅት ማለት የጸነሰው እንቁላል መህጸን ውስጥ ማደግ ከጀመረችበት ቀን ጀምሮ፥ ልጅ እስኪወለድበት ቀን ድረስ ያለው ጊዜ ነው። እርግዝና ለ 9 ወራት ወይም ለ40 ሳምንታት ድረስ ይቆያል። አንድ እርግዝና መቆጠር የሚጀምረው የወር አበባ ከቆመበት ቀን ጀምሮ ወይም ዋናው ጽንስ ከማጋጠሙ በፊት ያሉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ነው። መወረድ የወርአበባው መጨረሻ ከታየ ከአርባ ሳምንታት በኋላ ልጅ ይወለዳል።

ብዙ ሴቶች በወሊድ ጊዜ ከባድ ችግሮች ሳያጋጥማቸው ጤነኛ ልጅ ይገላገላሉ። ኖርዌይ ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሴት በአማካኝ ሁለት ልጆች ትወልዳለች። በየአመቱ እስከ 55,000 ልጆች ይወለዳሉ።

ምልክቶች

የሴት ልጅ እርግዝና የመጀመሪያው ምልክት የወር አበባ መቋረጥ ነው። ቤት ውስጥ ሆነሽ የምትጠቀሚበት የእርግዝና መመርመሪያ ከፋርማሲ መግዛት ትችያለሽ። እንዲሁም ትንሽ ሽንት ወደ ዶክተር መውሰድ ትችያለሽ።

እርጉዝ የሴት ልጅ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ውስጥ የማቅለሽለሽ እና የመታመም ስሜቶች ይሰሟታል። ሊደክማትና ሃይል ሊያንሳትም ይችላል። ሌሎች ምልክቶችም ጡት መወጠርና በጡት ጫፍ ላይ ከመጠን በላይ የሆነ የመጥቆር ሁኔታ ሊኖር ይችላል። ለአብዛኛዎቹ እርጉዝ ሴቶች ከ4ተኛ እስከ 7ተኛው ወር ያለው ጊዜ በጣም አመቺ ጊዜ ነው። በእዚህ ጊዜ ብዞዎቹ ሴቶች ሙሉ ኃይል ይሰማቸዋል።

Scale (5)

ሽል (ማህጸን ውስጥ ያለ ልጅ)

አንዲት እርጉዝ ሴት ከአረገዘችበት አራተኛ ወይም አምስተኛ ወር ጀምሮ ማህጸኗ ውስጥ ያለው ልጅ ሲንቀሳቀስ ሊሰማት ይችላል። በፊት ወልደው ለሚያውቁ ሴቶች ይህ ስሜት ቀደም ብሎ ሊመጣ ይችላል። መጀመሪያ ላይ የማህፀን እንቅስቃሴ በሳምንት አንድ ሁለት ጊዜ ብቻ ይሰማና ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንቅስቃሴው በየቀኑ ይሰማል።

በሰባተኛው ወር ማህጸን ውስጥ ያለው ልጅ በክብደት 1 ኪ.ግ. እና በርዝመት 35 ሳ.ሜ. አካባቢ ይሆናል። ሽሉ በእዚህ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለአደገ ከዚህ በኋላ የሚወለዱት ልጆች አብዝኛውን ጊዜ በህይወት ይወለዳሉ። ነገር ግን ይህ ወቅት ለወላድ በጣም የፈጠነ ነው። ያረገዘች ሴት ለራስዋ እንክብካቤ ማድረግ ይኖርባታል። ከባድ ነገሮችን ከማንሳትና ተገቢ በላይ ከሆነ የሰውነት እንቅስቃሴ መቆጠብ ይኖርባታል። በእርግዝናው መጨረሻ ወራት ሆድዋ እየገፋ ይመጣል። የሴትዋ ክብደትም በየጊዜው እየጨመረ ይመጣል። ትንፋሽዋም ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ይህም ልጁ ሆድዋን ስለሚገፋው ነው።

ልጁ በመጨረሻ በእርግዝና ወራት አካባቢ በጣም ትልቅ ይሆናል። በስምንተኛው ወር መጨረሻም ወደ ሶስት ኪ.ግ. አካባቢ ይመዝናል። ልጁ ከመወለዱ በፊት በአሉት የመጨረሻ ወራት ውስጥ ልጁ የቦታ ለውጥ አድርጎ ወደ እናቱ የዳሌ አጥንት ቦታ ጭንቅላቱን ያስገባል። ሁሉ ነገርም ለወሊድ ዝግጁ ይሆናል። ከ40 ሳምነታት በኋላ ልጁ ይወለዳል። ኖርዌይ ውስጥ በወሊድ ጊዜ የአንድ ልጅ ክብደት 3.6 ኪ.ግ. ይደርሳል።

Source: introamharisk.cappelendamm

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.