ባልሽን ወደ ቤት የትመልሺባቸው 4 መንገዶች

አንዳንዴ ለማመን እንቸገራለን፡ ፡ እጅግ እንደሚዋደዱ ተመስክሮላቸው ከዓይን ያውጣችሁ የተባሉ ጥንዶች በትዳር ብዙም ሳይቆዩ በፍቺ ሲለያዩ፤ እንዲሁም ልጆቻቸው ትላልቅ ሆነውና ለቁም ነገር ደርሰው በስተርጅና በሞቀ ትዳራቸው በበለጠ ደስተኝነት ይኖራሉ ተብለው የሚጠበቁ ባለትዳሮች የአልማዝ እዮቤልዩአቸውን ማክበር ባለባቸው ወቅት ትዳራቸው መፍረሱን ስንሰማ እንደነግጣለን፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ አንዳንድ ባለትዳሮች ከተለያዩ ከረጅም ጊዜያት በኋላ መልሰው ጎጇቸውን እንደ አዲስ መቀለሳቸው ነው፡፡ በእርግጥ ይህ አጋጣሚ በዕድለኝነት ብቻ የሚገኝ ሳይሆን በብርቱ ጥረት እና ባላሰለሰ ፅናት ሊፈጠር የሚችል የጥንካሬ ማሳያም ነው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የተጣሉት የትዳር አጋርዎ ተመልሶ ወደ ቤትዎ እንዲመጣ/እንድትመጣ ለማድረግ የሚሹ ከሆነ እርስዎም ተከታዮቹን ተግባራት ለማከናወን ይሞክሩ፡፡

 

1. የጽሑፍ መልዕክት ይላኩ
አንዳንድ ጊዜ መራራቅ ራሱን የቻለ ናፍቆት ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህ የሚልኩት የጽሑፍ መልዕክት ራሱን የቻለ ዋጋ ይኖረው ይሆናል፡፡ በተለይ ባለቤትዎ ሊያስታውሱት የሚችሉ የተለዩ ገጠመኞቻችሁን እያነሡ በትዝታ ባህር ተሳፍረው ወደ ትላንታችሁ እንዲመለሱ የማድረግ ኃይል ያላቸው የፍቅር መልዕክቶች ያድርሷቸው፡፡

2. ነገሮችን በእርጋታ ያከናውኑ
የተለየን አጋር በችኮላ መመለስ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ይልቅ እያንዳንዱ እርምጃዎ የተጠና እና እርጋታ ያልተለየው ይሁን፡፡ ምናልባት አጋርዎ ከእርሶ ከተለዩ በኋላ አዲስ ሕይወት ጀምረው፤ ወይም እርስዎን የሚረሱበት ረጅም የጥሞና ጊዜ ወስደው ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ነገር ማሰብ የሚችሉበት ጊዜ ይስጧቸው፡፡ ከእርስዎ ጋር የመዝለቁን ትርፍ እና ኪሳራ ካሰሉ በኋላ የቀዘቀዘውን ጎጆ ለምድመቅ ተመልሰው ይመጡ ይሆናል፡፡

3. ትናንትን አያስታውሱ
ትናንት ለእርስዎ እና ለባለቤትዎ ጥሩም ሆነ መጥፎ ትዝታዎች ጥሎ አልፏል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው፡፡ በተለይ የትናንቱን የባለቤትዎን ጥፋት ተመልሰው እያስታወሱ መወቃቀስ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ሁሉም ነገር ተመልሶ ይበላሻል፡፡ ይልቁንም ቤት ለቀውየወጡ የትዳር አጋርዎን ወደ ጎጇቸው መመለስ የሚችሉት ምን ያህል መልካም እንደነበሩ በመንገር፣ በአብሮነት ያሳለፋችሁት ጊዜ ትልቅ ደስታ የፈጠረብዎት መሆኑን በማስታወስ እና ያንን ሕይወት ዳግም በመመለስ ከቀደመው ግንኙነት የበለጠ ጣፋጭ የፍቅር ሕይወት ማሳለፍ እንደሚሹ ያረጋግጡላቸው፡፡

4. ይቅርታ ይጠይቁ – ስንት እውነት ይበቃል?

እናንተ ባለትዳሮች ሆይ ልጆቻችሁን ስታሣድጉ በስንት ፈታኝ አጋጣሚዎች አልፋችሁ ይሆን? በእርግጥ ፈታኝ ከሆኑት አጋጣሚዎች አንዱ ለልጆቻችሁ ምን ያህል እውነት መንገር በቂ እንደሆነ ማረጋገጥ መቻላችሁ ነው! ልጆቻችሁን በግልፅነት የማሣደግ አርአያነቱ የሚጀምረው ከእናንተ ነውና እናንተም ግልፅ ሆናችሁ መገኘት አለባችሁ፡፡ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ልጆቻችሁ ክፉና ደጉን የሚለዩበትና ከበድ ያለውን የሕይወት ሸክም የሚያስተናግዱበት ማንነት ላይ የደረሡ ባለመሆኑ ብዙም ልትፈተኑ አትችሉም፡፡ የልጆቻችሁ ዕድሜ በጨመረ ቁጥር ግን ልጆቻችሁ ሙሉ በሙሉ እምነት ጥለውባችሁ በእውነት እና በግልፅነት እንድትመሯቸው ይፈልጋሉ፡፡ ዶ/ር አኒታ ጋዲያ ስሚዝ የተባሉት የስነ-አእምሮ ባለሙያ እና የወላጆች አማካሪ “ልጆችን መዋሸት ጥሩ አይደለም” ይላሉ፡፡ “ይህ ማለት ግን ሁሉንም ነገር ለልጆች መንገር ተገቢ ነው ማለት አይደለም” በማለትም በሁለቱም በኩል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ይመክራሉ፡፡

ለምሳሌ አባት ወይም እናት ከትዳር አጋራቸው ጋር መለያየታቸውን ወይም ትዳራቸው መፍረሡን ጨምሮ ሌሎችም የትዳራቸውን ምስጢሮች ለልጃቸው ሲነግሩት፤ ልጃቸው የእነርሱን “ጣጣ” የመሸከም አቅም ያለው መሆኑን በቅድሚያ ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ “በእርግጥ በእኔ እና በባለቤቴ ጉዳይ ልጄን ማስጨነቅ አለብኝ?” ብለው ራሳቸውን ሊጠይቁም ይገባል፡፡ አንዳንድ ወላጆች ከትዳር አጋራቸው የደበቁትን ምስጢር ከመናገር በላይ ልጆቻቸውን እንደ ሽማግሌ አስቀምጠው በአጋራቸው የደረሠባቸውን በደል እስከ መንገር ይደርሳሉ፡፡ ይህ ድርጊት ልጃችሁ መጨነቅ በሌለበት ጉዳይ እንዲጨነቅና ዕድሜው ሳይደርስ ከባዱን የቤተሰብ ኃላፊነት እንዲሸከም የሚያስገድድ በመሆኑ ፤ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

በርካታ ወላጆች በማደጎ ከሚያሳድጓቸው ልጆች ጋር ከፍተኛ ፀብ ውስጥ የሚገቡበት ዋነኛው ምክንያት የኋላ ታሪካቸውንና ማንነታቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡ ይህንንም በተመለከተ የልጆች ዕድሜ እውነታውን ለመቀበል በቂ መሆኑን ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ እውነታው ሊነገራቸው ይገባል፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን አስተሣሠብ እና ስነ-ልቦና የማይጎዱ እውነቶችን ሁሉ ለልጆቻቸው ከመንገር መቆጠብ የለባቸውም፡፡ ልጆቻችሁ ከውሸት የሚርቁትና በመልካም ጠባይ ተኮትኩተው የሚያድጉት እናንተን ሲመለከቱ በመሆኑ ፈፅሞ ባለመዋሸት ጥሩ አርአያ ሁኗቸው፡፡

ምንጭ፡- Psychentral.com | ትርጉምና በቅድሚያ የታተመው በቁምነገር መጽሔት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.