ሰውነትን መታሸት (ማሳጅ) ለሰውነታችንም ሆነ ለአዕምሯችን በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ይናገራል።

የማሳጅ ህክምና የሚሰጡ ባለሙያዎች በእጃቸው፣ በክርናቸውና በክንዳቸው አልያም ሁሉንም በአንድ ጊዜ በመጠቀም አገልግሎቱን ይሰጣሉ።

እነዚሁ ባለሙያዎች የምንሰጠው አገልግሎት በርካታ ጥቅሞች ቢኖሩትም አስሩን እንገራችሁ ብለዋል። እነዚህም

1. የህመም ስሜትን ይቀንሳል

ሰውነታችን በሚታሽበት ወቅት በአጥንቶቻችን፣ ጅማቶቻችን እና በሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ላይ የሚከሰቱ የህመም ስሜቶችን የሚቀንሱ ኬሚካሎች ይመረታሉ።

ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ሰውነትን በተደጋጋሚ መታሸት የአጥንት በሽታዎችን ለማጥፋት ይረዳል።

2. የደም ግፊትን ይቆጣጠራል

ከፍተኛ የደም ግፊት ለሚሊዮኖች ዋነኛ የጤና ጉዳይ ነው።

በርካታ ጥናቶችም ሰውነትን መታሸት (ማሳጅ) ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመከላከል እንደሚያግዝ አመላክተዋል።

3. ጭንቀትና ፍርሃትን ያስወግዳል

መጥፎ ስሜት አልያም ድብርት ሲሰማን ወደ ማሳጅ ቤት ማምራት ከዚያ ስሜት ለመውጣት እንደሚረዳ ይነገራል።

ሰውነትን መታሸት የጭንቀት ሆርሞን የሆነውን ኮርቲሶል(Cortisol) መጠን ይቀንሳል።

ማሳጅ በተጨማሪም ጭንቀትን ለማስወገድ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን ዶፓሚን እና ሴሮቶኒን የተሰኙ ሆርሞኖች መመረት ያሳድጋል።

4. ለአስደሳች እንቅልፍ

የእንቅልፍ እጦትና ተያያዥ ችግሮች በአንዳንድ ሴቶችም ሆነ ወንዶች በየትኛውም የእድሜ ክልልና ቦታ የሚከሰት በሽታ ነው።

በስራ ጫናም ይሁን የተለያዩ አነቃቂ ነገሮችን በማዘውተራቸው በእንቅልፍ እጦት ለሚሰቃዩ ሰዎች ሰውነትን መታሸት መፍትሄ መሆኑ ይነገራል።

5. ለጤናማ የአተነፋፈስ ስርአት

ሰውነትን መታሸት እንደ ሳይነስ፣ የጉሮሮ ቁስልና አለርጂ ካሉ ህመሞች ለመገላገልና ጤናማ የአተነፋፈስ ስርአት እንዲኖር ያደርጋል።

የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸውን የመተንፈሻ መሳሪያዎችን ሳንጠቀም በቀላሉ እንድንተነፍስም እገዛ ያደርጋል።

6. በሽታ የመከላከል አቀምን ያዳብራል

በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ሰውነትን መታሸት ነጭ የደም ህዋሳቶችን ቁጥር እንደሚያሳድግ አረጋግጠዋል፤ ይህም በሽታ የመከላከል አቅማችን ያሳድጋል።

7. ካንሰርን ያስታግሳል

የማሳጅ ህክምና ከተለመደው ባህላዊ ህክምና ይልቅ የካንሰር ህመምን ለማስታገስ ትልቅ አቅም እንዳለው ይታመናል።

የካንሰር በሽተኞች ከህመም ሰሜት ወጥተው ዘና እንዲሉ ማሳጅ ቤቶችን እንዲያዘወትሩ ይመከራል።

8. ማራኪ የሰውነት ቅርጽ ያላብሳል

በአሁኑ ወቅት ለኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ቅርብ የሆኑና መቀመጥ የሚያዘወትሩ ሰዎች የሰውነት ቅርፃቸው ሲበላሽ ይሰተዋላል።

በተለይም ኮምፒዩተር ላይ ለብዙ ስአት መቀመጥና ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርአት ለሰውነት ቅርጽ መበላሸት ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ይነገራል።

ስለሆነም የተበላሸ የሰውነት ቅርጽን ለማስተካከል ሰውነትን መታሸት ጠቃሚ ነው።

9. የራስ ምታትን ይቀንሳል

በከባድ የራስ ምታት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች ብዙ ጊዜ እንደ አስፕሪን እና ፓራሲንታሞል ያሉ ማስታገሻዎችን ሲያዘወትሩ ነው የሚስተዋለው።

ይሁን እንጂ መድሃኒቶቹ የህመሙን ስሜት የሚያስታግሱት ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው።

ለረዥም ጊዜ የቆየ የራስ ምታት ወይም ማይግሬን ካለብዎ የጭንቅላት ማሳጅ ቢያደርጉ ከህመም ለመገላገል ያግዝዎታል ተብሏል።

10. ከጉዳት በፍጥነት ለማገገም ያግዛል

ማሳጅ በሰውነታችን ላይ ከደረሰ አደጋ በኋላ እና ከቀዶ ጥገና ማግስት በፍጥነት ለማገገም ዋነኛው መንገድ መሆኑ ይነገራል።

የደም ዝውውርን በማፋጠን የተዳከሙ ጡንቻዎች እንዲፍታቱም ያደርጋል።

በአደጋዎች የተጎዱ የሰውነታችን ክፍሎች በሚታሹበት ወቅት በቂ ኦክስጂን ስለሚያገኙ ከህመሙ ቶሎ ለመዳን ማሳጅ ማድረግ ከፍተኛ ጥቅም አለው።

ምንጭ፦ www.stylecraze.com

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በፋሲካው ታደሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.