ለጥንቃቄ ኩላሊት መጎዳቱን ማሳያ ምልክቶች

ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ ግን ሰውነት ላይ የሚታዩ አንዳንድ ምልክቶች ሳይታወቅ ለበሽታ ተጋልጠው መሆንዎን አመላካች ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ማድረጉም መልካም ነው።

ነገን ለማየት እና ያሰቡትን ለማሳካት በጤና መሰንበቱ የመጀመሪያውና ዋናው ነገር ነው። እርሰዎ ከሌሉ እቅድዎም ሆነ የተለሙት ጉዳይ ዋጋ አይኖረውምና ቅድሚያ ለጤና መስጠቱ ይመረጣል።

ከጎጅ ልማዶች ጀምሮ ሰውነትን ከሚጎዱ እና ለጤና ጠንቅ ከሆኑ ጉዳዮች መራቅ በጤና ለመሰንበት ቀዳሚው መሆኑም ይነገራል።
ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ ግን ሰውነት ላይ የሚታዩ አንዳንድ ምልክቶች ሳይታወቅ ለበሽታ ተጋልጠው መሆንዎን አመላካች ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ማድረጉም መልካም ነው።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ፈሳሽ ነገሮችን እያጣራ ከሰውነት የሚያስወግደው ኩላሊት ላይ ችግር መከሰቱን አመላካች መንገዶች ተብለው የተዘረዘሩትን ይመልከቱ፤
የሰውነት መልፈስፈስና መዛል፦ ኩላሊት ሲጎዳ በሰውነት ውስጥ የሚገኘው ቀይ የደም ሴል መጠን ይቀንሳል፤ ይህ ደግሞ ከአዕምሮ ድካም ጀምሮ የጡንቻ አካባቢ መስነፍና የሰውነት መዛልን ያስከትላል።

የቆዳ ላይ አለርጅ፦ በተጎዳ ጊዜ ኩላሊት ስራውን ስለሚያቆም እና ፈሳሽ ነገሮች ቶሎ ከሰውነት ስለማይወገዱ በሰውነት ውስጥ መርዛማ ነገሮች ይበዙና በቆዳ ላይ ለሚፈጠር አለርጅ ምክንያት ይሆናሉ።

የትንፋሽ ማጠር፦ ከቀይ የደም ሴል ቁጥር መቀነስ ጋር ተያይዞ የትንፋሽ ማጠር ይከሰታል።

የጣዕም መቀየር፦ ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ የምግቡ ጣዕም የብረት አይነት እና ሌላም የተለየ አይነት ቃና ካለው ኩላሊትዎ ተጎድቷልና መፍትሄ ይውሰዱ። ይህ የጣዕም መቀየር መንስኤው ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች ስለሚቀያየሩ ነውና ምልክቱን ሲያስተውሉ ወደ ሃኪም ቢያመሩ መልካም ነው።

የሽንት ቀለም መቀየር፦ በተለይም የሽንት ቀለም በተደጋጋሚ ወደ ቢጫነት ካደላ ችግር አለና ጊዜ ሳያጠፉ ይታዩት።

የሰውነት ክፍል እብጠት፦ ኩላሊት ሲጎዳ በሰውነት ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽን የማጣራት አቅም ስለሚያጣ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ እብጠት ይከሰታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.