ከአንዳንድ ለጡት ካንሰር መጋለጥ እድልዎን ይቀንሱ


Breast-Cancer-1-400x296ከአንዳንድ ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ነገሮችን ለመቀነስ አይቻልም። ለምሳሌ ከቤተሰብ የበሽታ ታሪክ ወይንም የወር አበባዎ በልጅነትዎ ተከስቶ ከነበረ። አንዳንዶቹን ነገሮች ግን ለምሳሌ የሰውነት ክብደትዎን ወይንም የሚጠጡትንና የሚበሉትን ነገሮች መቀየር ይቻላል። እነዚህን ነገሮች መቀየር ሁልጊዜ ቀላል አይደለም እና እነዚህንም ስላደ
ረጉ ሰውነትዎ የጡት ካንሰር ህመም አይዘውም ማለት አይደለም። ሆኖም እርስዎ በበሽታው የመያዝ እድልዎን ለመቀነስ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ ማለት ነው።

ጤናማ የሰውነት ክብደት መጠንን መጠበቅ Maintain healthy body weight
ከማረጫ እድሜዎ በላይ ከሆኑ ውፍረት በበሽታው የመያዝ እድልዎን የጨምራል። ለአብዛኞቹ ሴቶች የሰውነት ክብደትን መቀነስ ወይንም በጤናማ የሰውነት ክብደት መጠን ላይ መቆየት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። በማረጫ እድሜ ክልል ውስጥ ላሉት ደግሞ ክብደት መጨመርን መቆጣጠር የበለጠ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ለጊዜው ይህ ቢታወቅም ውፍረት በማረጫ እድሜ ውስጥ ላሉ ሴቶች በበሽታው የመያዝ እድላቸውን ለመጨመሩ ተጨማሪ ጥናትና ምርምር ማድረግ ያስፈልገዋል።

የእርስዎን ጤናማ የሰውነት ክብደት መጠንና ክብደትዎን የመጠበቅ ዘዴዎችን ለማወቅ ሀኪምዎን ያነጋግሩ።

ሰውነትዎ እንቅስቃሴ ይኑርዎ Be Physically active አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሰውነት እንቅስቃሴ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል። አሁንም በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ለመቀነስ ምን ያህል የእንቅስቃሴ ጥንካሬ እና መጠን እንደሚያስፈልግ ለማወቅ ተጨማሪ ጥናትና ምርመራ ያስፈልጋል።

ስብ ያልበዛበትን ምግም ይመገቡ Eat food
that are low in fat ስብ ያልበዛበትን ምግብ መመገብ የሰውነት ክብደትዎን ለመጠበቅ ይረዳዎታል። ከምግብ ስለሚገኝ ስብ ከካንሰር በሽታ ያለውን ሚና ለማወቅ ጥናትና ምርምር ማድረግ ያስፈልጋል። ነገር ግን በማረጫ እድሜ ውስጥ መወፈር ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምር ይታወቃል።

አትክልትና ፍራፍሬመመገብ Eat vegitables and fruits
አመጋገብ ከጡት ካንሰር ጋር ያለውን ግንኙነት ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ ያስፈልጋል። ሆኖም በተወሰነ ደረጃ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በብዛት አትክልትንና ፍራፍሬን መመገብ በተለይ በቤተሰባቸው ውስጥ የጡት ካንሰር ህመም ላለባቸው ሰዎች የመጋለጥ እድላቸውን ሊቀንስላቸው ይችላል። ይህ ደግሞ የበለጠ የሆርሞን ሪሴፕተር-ፖሰቲቭ ቱሞርስ ለመከላከል ይረዳል።

ብዙ አኮል መጠጥ አለመጠጣት Don’t drink too much alcohol
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ መጠነኛ አልኮል መጠጥ መጠጣት ለጡት ካንስር የመጋለጥ እድልን በአነስተኛ ደረጃ ይጨምራል። አልኮል መጠጥ ለመጠጣት የሚመርጡ ከሆነ በቀን ከአንድ ብርጭቆ በላይ ላለመጠጣት ይወስኑ። በየቀኑ ከዚህ የበለጠ በጠጡ ቁጥር በበሽታው የመያዝ እድልዎም እየጨመረ ይሄዳል።

በሀኪምየሚታዘዙ የሆርሞን መድሃኒቶችን በተቻለ መጠን ያስወግዱ
Avoid prescription hormones if you can
በሀኪም የሚታዘዙ የሆርሞን መድሃኒቶችን የሚያስከትሉትን የመጋለጥ መጠን፤ ጥቅምና ጊዳቶችን ከሀኪምዎ ጋር ይነጋገሩበት። ይህም በመረጃ የተደገፈ ውሳኔን ለመውሰድ ይረዳዎታል።

ኤች አር ቲ HRT
በሌላ የህክምና ዘዴ ተሞክሮ ያልተሳካ በጣም አስቸጋሪ የማረጥ ህመሞች ካልኖርዎት በቀር ሆርሞንን ለመተካት የሚወሰድን ህክምና ለማስወገድ ይሞክሩ። ሆርሞንን ለመተካት የሚወሰድ ህክምና ያለውን ጠቀሜታ ከጉዳቱ መብለጡን እርስዎና ሀኪምዎ አመዛዝናችሁ ወሰናችሁ ከሆነ በጣም አነስተኛ መጠን ያለውና ለአጭር ጊዜ ብቻ መውሰድ በእርስዎ ላይ ሊታይ የሚቸለውን ምልክት/ጎጂ ተጽዕኖ ለመቀነስ ይቻላል።

የወሊድመቆጣጠሪያ ክኒን The pill
በወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት/ክኒን የሚያመጣው የጡት ካንሰር የመጋለጥ ሁኔታ በጣም አነስተኛ ነው። ሆኖም ከሀኪምዎን ይህንን ክኒን በመውሰድ ለምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለብዎት ያነጋግሩ። እንደ እድሜዎ እና ሌሎች የመጋለጥ ሁኔታዎችዎ ሌላ አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ መንገድ ለእርስዎ የተሻለ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። በ10 አመታት ጊዜ ውስጥ ከክኒኑ ውጪ መሆን ለጡት ካንስር የመጋለጥ እድልዎን ወደ አማካይ ደረጃ ሊመልሰው ይችላል። ዋናው የክኒኑ ጠቀሜታ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል እና በወር አባባ ጊዜ የሚከሰተውን ህመምና ፈሳሽ ለመቀነስ ነው። ሌሎች ጥቅሞቹ ለዩተራይን (ኢንዶሜትሪያል) እና ለማህጸን (ኦቫሪ) ካንስርን የመጋለጥ እድልን መቀነስ ነው።

ሲጋራ አያጭሱ እና ሁለተኛ አጫሽም መሆንን ያስወግዱ
Don’t smoke and avoid second-hand smoke
ባለሙያዎች ሲጋራ ማጨስ ለጡት ካንስር መጋለጥ እድልን ይጨምራል ብለው በእርግጠኝነት አይናገሩም። አንዳንዶች ሁለተኛ አጫሽ መሆን ለበሽታው ያለን የመጋለጥ እድል ይጨምራል ብለው ያስባሉ። የሲጋራ ጭስን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ለጤናዎ ብለው ሊያደርጉት ይቸላሉ እና ይህም ለጡት ካንሰር ያሎትን የመጋለጥ እድል
ይቀንሳል።

ጡት ለማጥባት ያስቡ Consider breast-feeding
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የጡት ወተት ማመንጨት በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል። ጥቅሙም በህይወት ዘመንዎ ውስጥ ጡት በማጥባት ካሳለፉትን ጊዜ ጋር የተያያዘ ይመስላል። ጡት ማጥባትን ለመምረጥ ወይንም ላለመምረጥ ብዙ የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ለሁሉም እናቶችና ህፃናት ተመሳሳይ ሁኔታ
የላቸውም። ለእርስዎ የሚስማማውን ሁኔታ መምረጥ ይችላሉ፤ ረዘም ላለ ጊዜ ማጥባት ይመረጣል።

ስለጡትካንሰርየመጋለጥ እድልዎከሀኪምዎ ይነጋገሩበት
Talk to your doctor about your risk
ሁሉም ሴቶች በጡት ካንሰር ስለመጋለጥ እድላቸው ከሀኪሞቻቸው ጋር መነጋር አለባቸው። ለበሽታው ለመጋለጥ በቤተሰብዎ ውስጥ የበሽታው ታሪክ መኖር አያስፈልገውም – በቀላሉ ሴት መሆንና በእድሜ መግፋት ማለት የጡት ካንሰር የመያዝ እድልዎ ይጨምራል ማለት ነው። የበለጠ ለመረዳት ሀኪምዎ ለዚህና ለሌሎች በሽታዎች ያሎትን የመጋለጥ እድል ሊያስረዱዎት ይችላሉ። በተጨማሪም የጡት ካንሰርን ስር ሳይሰድ እንዲታወቅ የሚረዱ የምርመራ አይነቶችን ሀኪምዎ ሊነግሩዎት ይችላሉ።፡

በቤተሰብ የህክምና ታሪክ ወይንም ስለበሽታው በቤተሰብ ውስጥ ያለ ጠንካራ ታሪክ ምክንያት በጡት ካንሰር የመያዝ እድል ያላቸው ሴቶች በቁጥር በጣም አነስተኛ ናቸው። ከእነዚህ ሴቶች መካከል አንዷ ከሆኑ የሚከተሉት አማራጮች ሊኖርዎት ይችላሉ

· በሽታው ከመከሰቱ በፊት የጡት ካንሰር ምርመራ ማድረግ ወይንም በአማካይ ከሚደረግበት ድግግሞሽ በተጨማሪ ምርመራውን ማድረግ
· በጄኔቲክ የመጋለጥ እድልን ማስጠናት
· አንዳንድ የመከላከያ (prophylactic) ህክምና ለምሳሌ ኤስትሮጅን ሆርሞንን የሚከላከል መድሃኒት ወይንም የመከላከያ የቀዶ ጥገና ህክምና ማድረግ ሃኪሞን

ስለጡት ካንሰር መጠየቅ የሚገባዎ ጥያቄዎች
Questions to ask your doctor about breast cancer
· ለበሽታው የሚያጋልጡኝ ነገሮች ምንድናቸው?
· በቤተሰቤ ውስጥ ያለው የበሽታ ታሪክ ከአማካይ በላይ ሊያጋልጠኝ ይችላል?
· ለበሽታው ያለኝን መጋለጥ ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብኝ?
· ምን አይነት ምርመራዎችን ማድረግ እችላሉ?
· ምን አይነት ጉዳቶች አሉት?
· የምርመራ ውጤቴ ያልተለመደ ሁኔታን ቢያመለክት ምንድነው የሚሆነው?
· ለምርመራው የሚየስፈልገው ወጪ አለ? ወጪ ካለ ምን ያህል ነው?
· በየምን ያህል ጊዜ ነው ምርመራ ማድረግ ያለብኝ?

የጡት ካንሰር መንስኤዎች Causes of breast cancer
አንድ ተለይቶ የታወቀ የጡት ካንስር መንስኤ ነው የሚባል ነገር የለም። ሆኖም የጡት ካንሰርን ያመጣሉ ተብለው የሚገመቱ ነገሮች አሉ። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው:፡

· እድሜ (የጡት ካንሰር በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ
ሊታይ ይችላል፡፡ ነገር ግን በእድሜ በገፋ ቁጥር በበሽታው የመያዝ እድል ይጨምራል።)
· በራስ ላይተከስቶ የነበረ የጡት ካንሰር ካለ (በአንደኛው ጡትዋ ላይ የጡት ካንሰር ታይቶ ከበነረ በሌላኛው ጡትዋ ላይ ካንሰሩ ደግሞ የመውጣት እድሉ ከፍተኛ ነው።)
· ቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር ታሪክ ካለ (በተለይ እናት፤ አህት፤ ወይንም ልጅ ከማረጫ እድሜያቸው በፊት የጡት ካንሰር የተያዙ ከነበረ ወይንም ቢ አር ሲ 1 ወይንም ቢ አር ሲ 2 (BRCA1 BRCA2) ተብሎ የሚጠራው ካንሰር አይነት ተከስቶ ከነበረ።)
· በቤተሰብ ውስጥ የማህፀን ካንሰር ከነበረ
· ልጅ ያለመውለድ ወይንም የመጀመሪያ ልጅ የተወለደው ከ30 አመት በሗላ ከነበረ
· የወር አባባ በልጅነት ጀምሮ ከነበረ
· የማረጫ ጊዜ ከተለመደው አማካይ ጊዜ በላይ ከተራዘመ
· የሆርሞን (hormone)መተኪያ ህክምና/ቴራፒ (ኤስትሮ ጂን ወይንም ፕሮጀስትሮን) ከ5 አመታት በላይ ወስደው ከነበረ
· ጠንካራ የጡት ይዘት (dense breast tissue)- በማሞግራም
ከተረጋገጠ
· ቀደም ብሎ በተደረገ የጡት ህመም የናሙና/ባዮፕሲ (biopsy) ምርመራ ለውጥ ታይቶ ከነበረ ለምሳሌ ምንም እንኳን ካንሰር ያለባቸው ሴሎች ባይሆኑም ጤናማ ያልሆኑ ሴሎች ቁጥር መጨመር (atypical hyperplasia)

አልኮል መጠጣት ወይንም የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን መውሰድ በትንሹ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ይጨምራሉ። ሌሎች መንስኤ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመቱት ገና መጠናት ላይ ያሉ ናቸው። እነዚህም ሲጋራ ማጨስ፤ አመጋገብ፤ የሰውነት እንቅስቃሴ (exercise) እና ውፍረት ናቸው።

አንዳንድ ሴቶች ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ሳይመለከታቸው/ሳይታይባቸው የጡት ካንሰር ሊኖራቸው ይችላል። አብዛኞቹ የጡት ካንሰር የተገኘባቸው ሴቶች በቤተሰብ ታሪካቸው ውስጥ ያልነበረ ነው። በተጨማሪ ብዙ ከላይ የተጠቀሱት መንስኤ ሊሆኑ ይቸላሉ ተብለው የሚገመቱት ነገሮች ቢኖሩባቸውም ብዙ ሴቶች በጡት ካንሰር አልተያዙም።
የጡት ካንሰር ምልክቶች Symptoms of breast cancer
አብዛኛውን ጊዜ የጡት ካንሰር መኖሩ የሚታወቀው ምንም የህመም ምልክት በሌለው ጡት ወይንም በብብት ውስጥ በሚገኝ እብጠት ነው። ይህንንም እብጠት እርስዎ ወይንም ያእርስዎ ባለቤት/ጓደኛ ልታገኙት ወይንም ሀኪምዎ የተለመደውን የጡት የአካል ወይንም የማሞግራም ምርመራ ሲያደርጉ ሊያገኙት ይችላሉ።

ሌላ የጡት ካንሰር ምልክት ሊሆን የሚችሉት ደግሞ በጡት ላይ የሚታይ የመጠንና የቅርጽ ለውጥ፤ የመሰርጎድ ወይንም የጡት ቆዳ መወፈር (አንዳንዴ ኦሬንጅ ፒል ስኪን/ እንደብርትኳን ልጣጭ ቆዳ የወፈረ እየተባለ የሚጠራው) ናቸው። በጡት ጫፍ ላይ ለውጥ ሊያስተውሉ ይችላሉ ለምሳሌ የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት (inversted nipple)፤ በጡት ጫፍ ዙሪያ የሚታይ ሽፍታ ወይንም ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ሊታይ ይችላል።

አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ምልክቶች በካንስር ምክንያት ብቻ የሚታዩ አይደሉም። ሌሎች የጤና እክሎችም እነዚህን ምልክቶች ሊያመጡ ይችላሉ። በጡት ውስጥ የሚታይ እብጠት በጣም የተለመደ መሆኑን ያስታውሱ። በተለይ ደግሞ ከወር አበባ በፊት። አብዛኞቹ እብጠቶች የጡት ካንሰር አይደሉም። ሆኖም ለይቶ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
Create a free website with Photo used under Creative Commons from U.S. Embassy Tel Aviv
ኮፒ ራይት Disclaimer and Copyright Disclaimer:- ብሬስት ካንስርአምሃሪክ የተባለው ድህረ ገጽ የተሰራበት ዋና ዓላማ የጡት ካንሰር ምንነትን ለመረዳት ለሚፈልጉ፤ በዚህ ህመም ራሳቸው የተያዙ እና ስለበሽታው ያላቸውን ግንዛቤ ማዳበር ለሚፈልጉ፤ ላስታማሚዎችና በዚህ የህመምና ድህነት ጫና ላለባቸው ሰዎች ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ መረጃን ለመስጠት ነው። ድህረ ገጹ ትምህርታዊ ይዘት ያለው ሲሆን ምንም አይነት የህክምና አገልግሎት ወይም የባለሙያ ምክር ለመስጠት የተዘጋጀ አይደለም። ማንኛውም የህክምና ውሳኔ ከሀኪምዎ ጋር ወይንም በራስዎ የሚያደርጉት ነገር ነው። በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የቀረበውን መረጃ በመጠቀም ለሚደርሰው ማንኛውም አይነት የህመም መባባስ፤ ጉዳት ወይንም እክሎች እና ከህክምና ጋር የተያያዙ ጉዳቶች የድህረ ገጹ አዘጋጅ ወይንም መረጃውን በጽሁፍ በመስጠት ትብብር ያደረጉትን ቶም ቤከር ካንሰር ማዕከልን (Tom Beker Cancer Center) ወይንም www.cancer.ca በሀላፊነት የሚያስጠይቅ አይሆንም። ኮፒ ራይት Copyright:- በዚህ ድህረ ገጽ ላይ የቀረቡት መረጃዎች ከቶም ቤከር ካንሰር ማዕከልን (Tom Beker Cancer Center) ወይንም www.cancer.ca የተወሰዱ ሲሆን ለጽሁፎቹ ጥራት በቂ ጥናት የተደረገበትና የተመረጡ ናቸው። ከሌሎች ምንጮች ተገኝተው የተተረጎሙ መረጃዎች በሙሉ በባለቤትነት ያበረከቱት ድርጀርጅቶች/ሰዎች ስም ይጠቀሳሉ። ስለዚህ ከዚህ በሚከተሉት መሰረት ከድህረ ገጹ የሚያገኙትን መረጃዎች በማተም ወይንም በመገልበጥ (copy) መጠቀም ይችላሉ። 1. የትርጉም ስራውን ያገኙበትን www.weebly.breast cancer- Amharic.com በመጥቀስ። 2. ከዚህ በተጨማሪ መረጃዎቹ የተገኙበት www.cancer.ca መሆኑን በማሳወቅ። 3. ማንኛውንም በዚህ ላይ የቀረቡትን ጽሁፎች ከንግድ ጋር ላልተያያዘ ስራ በመጠቀም። 4. በቀረቡት ጽሁፎች ላይ የማሻሻል፤ የማዳበር ወይንም የመለወጥ ስራ ባለማከሄድ። የቀረቡትን መረጃዎች በድጋሚ ለመጠቀምም ሆነ ለማሰራጨት የዚህ ጽሁፍን ምንጭ በመጥቀስ ለሌሎች ግልጽ ማድረግ ይኖርብዎታል። አግባብ ያለው አጠቃቀምዎና ሌሎች መብቶችዎን ሁሉ ከዚህ በላይ በቀረበው ሁኔታ ምክንያት የሚነፈግዎት አይደለም።   Source; Ethiopia Cancer Association

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.