በአሁኑ ወቅት ሴቶችም ሆነ ወንዶች በተለያዩ ምክንያቶች ፀጉራቸውን ቀለም ይቀባሉ።

ይህ ቀለም እንደ አሞኒ (ammonia) ፣ ፕሮፕይለን (propylene)፣ ግላይኮል (glycol) እና ፒፒዲ የመሳሰሉ አለርጂ የሚፈጥሩ ኬሚካሎችን ይዟል።

እነዚህ ኬሚካሎችም በፀጉር አልያም በጭንቅላት ላይ በሁሉም ሰው ላይ ነው ባይባልም አንዳንድ ችግር ይፈጥራሉ።

በጆሯችን፣ የእጅ መዳፎቻችን፣በፊት እና በጭንቅላታችን ላይም የመንደብደብና የሽፍታ ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።

ችግሩ ከበድ ሲልም እስከ መተንፈስ ማቃት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊፈጥር ስለሚችልም ወደ ሀኪም ዘንድ መሄድ ይገባል።

ፀጉራችንን ለማሳመር የምንጠቀምባቸው ቀለሞች አለርጂ በማስከሰት ሰቀቀን ከሆኑብንም ስታይል ክሬዝ የተሰኘው ድረገፅ ያወጣውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ የፀጉር አለርጂን መከላከያ መንገዶች ብንጠቀም የተሻለ ለውጥ እናያለን።

1. የሎሚ ጭማቂ

የሎሚ ጭማቂ የበሰበሰና በጉድፍ የተበከለ የሰውነት ክፍልን ማድረቅ ስለሚያስችል በአለርጂ ለተጎዳ የጭንቅላት ክፍል ወሳኝ ነው።

የሎሚ ጭማቂን ከውሃ ጋር በመቀላቀልና አልያም ከእርጎ ጋር አዋህዶ ጭንቅላታችንን በመቀባት በፀጉር ቀለም የሚመጣ የጭንቅላት አለርጂን መከላከል ይቻላል።

2. ቤኪንግ ሶዳ

የተቦካ ቤኪንግ ሶዳም በፀጉር ቀለም ምክንያት የሚከሰት አለርጂን ለማከም ያግዛል።

ቤኪንግ ሶዳውን በጭንቅላታችን ላይ በማድረግና በውሃ በማራስ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ከቆየን በኋላ በውሃ በደንብ መታጠብ አለርጂን ለማጥፋት እንደሚረዳ ይነገራል።

3. የሻይ ዛፍ ዘይት

የሻይ ዛፍ ዘይት ጸረ ባክቴሪያና ፀረ ፈንገስ የሆኑ ውህዶችን የያዘ በመሆኑ አለርጂን ለመከላከል ይረዳል።

አለርጂው የሚያስከትለውን ማሳከክና የሰውነት መጉረብረብን ለመቀነስም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

4. የዘንባባ ዘይት

የዘንባባ ዘይት የቆዳ እርጥበትን በመጠበቅ አለርጂው የሚያስከትላቸውን የቆዳ መድረቅና ሽፈታዎችን ለማጥፋት እንደሚያግዝ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

ዘይቱን ጭንቅላታችንን በመቀባት ለ15 ደቂቃ ያህል ከቆየን በኋላ በሻምፖ መታጠብ የፀጉር ቀለም አለርጂን ለመከላከል ከፍተኛ ድርሻ አለው።

5. የአፕል ጭማቂ

የአፕል ጭማቂ ሰውነታችንን ከሚያስቆጡ ነገሮች የሚታደግ ንጥረ ነገር በመያዙ የፀጉር አለርጂን በቤት ውስጥ ለማከም ይረዳል።

የጭንቅላት ድርቀትንና ሽፍታዎችን ለማጥፋትም ያግዛል።

እነዚህንና ሌሎች በቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ነገሮችን ተጠቅመን አለርጂው ሊቀንስ ካልቻለ ወደ ህክምና ተቋማት ማምራቱ ተገቢ ነው።

ምንጭ፦ http://www.stylecraze.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.