የመውለድ አለመቻል/Infertility/ ችግሮች የህክምና መፉትሄዎች – ክፍል 2 (ሰብለ አለሙ)

በምህራቡ ሀገር የምህራቡ ህክምና ( western medicine) ከተራቀቁባቸው የህክምና ዕይነቶች አንዱ የመውለድ ችግር ላጋጠማቸው ጥንዶች መፍትሄ መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ መፉጠራቸው ነው:: በዛው መጠን ይዘቱን ሳይለቅ ለዘመናት የተሸጋገረው የቻይና ባህላዊ ህክምና( traditional Chinese medicine ) በምህራቡ ሀገር ተቀባይነቱ ከጊዜ ወደጊዜ በመጨመር የራሱን ሚና እየተጫወተ ይገኛል::

የምህራቡ የህክምና መፍትሄ ዕይነቶች  /  Assisted Reproductive Technology  or ART/

የህክምናው ጉዞው የሚጀምረው የማህፀን እና ፅንስ እስፔሻሊስት በማየት ሲሆን( ለምሳሌ ችግሩ እንቁላል መተላለፊያ ቱቦ ( Fallopian tube) መጣበቅ ,ተለቅ ያለ እንዲሜትሪዮስስ( endometriosis) , ፋይብሮይድ ቱመር ( fibroid Tumer ) በሰርጀሪ ችግሩ የሚቀርፉ ወይንም ጊዜያዊ መፍትሄ የሚጡ ሲሆን)  ከእዚህ  ህክምና ስፔሻሊቲ አቅም በላይ ከሆነ የማህነት   ህክምና/ fertility  treatment / ብቻ ላይ ስፔሻላይዝድ ያደረጉትን /  fertility experts called Reproductive specialists, Reproductive Endcrologist / እንዲያዪ ይመከራሉ::

 

አይ ቪ ኤፍ ( IVF): In vitro fertilization:

ማለት ከማህፅን ውጪ የሴት እንቁላልና የወንድ የዘር ፍሬ ማራባት ሲሆን በሰፊው እየተሰራበት  ያለ የህክምና ምርጫ ነው ::

ህክምናው የሚውልበት የመውለድ ችግሮቹ :-የሴት ልጅ ማህፀን መደፈን : እንቁላል ማፍራት  አለመቻል: እንቁላል ጥራትመቀነስ ; የወንድ የዘር ፍሬ በቁጥርና በጥራት ማነስ በጥቂቱ ናቸው::

መጀመሪያ ለሴቷ እንቁላል ማፍሪያ መዳኒት በመውጋት የእንቁላል ማፍሪያ አካሏ ( ኦቫሪ) ብዙ እንቁላሎች እንዲያፈራ ይደረጋል :: እንቁላሉ ካደገ( mature) ከሆነ በኃላ , ከእንቁላል ማፍሪያ አካሏ (ኦቫሪ)  ተለቅሞ ወጥቶ በላብራቶሪ ዉስጥ በስሀን ላይ ከወንድ የዘር ፍሬ ጋር እንዲራባ(fertilized) እንዲሆንይደረጋል::

ከ3-5 ቀን በኃላ ጤናማው ኢምብሮይ( embroyos ) ተመልሶ ወደሴቷ ማህፅን ውስጥ ይተከላል::

 

ICSI : Intracytoplasmic Sperm Injection:

ማለት አንድ የወንድ የዘር ፍሬ ቀጥታ የአደገው የሴት እንቁላል (matured egg) ውስጥ ከተወጋ በኃላ ኢምብሮይ ሲሆን ወደ መሃፅን ወይንም  ወደ ማህፅን ቱቦ ይተላለፋል::

ይህ የከፋ የወንድ የዘር ፍሬ ላይ ችግር ሲያጋጥም የሚካሄድና አንዳንዴም እድሜያቸው የ ገፋና እና IVF ሞክረው ያልተሳካላቸው ጥንዶች ላይ የሚካሄድ የህክምና ምርጫ  ነው::

 

IUI: Intrauterine insemination:

ማለት የታጠበና መጠኑ በዛ ያለ የወንድ የዘር ፍሬ ሴቷ እንቁላል ሰርታ በምትለቅበት ጊዜ ተጠብቆ ቀጥታ ወደማህፅኗ ዉስጥ ማስቀመጥ ሲሆን እንደችግሩ አይነት የሴቷን እንቁላል የማፍራት ሂደት በመከተል ወይም መዳኒት በመጠቀም እንቁላል እንድታፈራ በማድረግ ህክምናው ይካሄዳል::

አንዳንዴ ይህ የህክምና ዘዴ ከሌላ ሰው የተገፕ ጤናማ እንቁላል ወይንም የወንድ የዘርፍሬ ወይንም ከዚህ በፊት ከጥንዶቹ ተዎስዶ ፍሮዝን(frozen) የሆነውን እንቁላል/ስፐርም ይጠቀማል::

አነህዚ  ከላይ የተጠቀሱት ካሉት የህክምና ዕይነቶች በጥቂቱ ናቸው:: የህክምና ዕይነቶቹ በአሜሪካ ሀገር ብዙህን ጊዜ በኢንሹራንስ የሚከፈሉ አይደሉም:: ዎጋቸውም በቀላሉ የሚቀመስ ስላልሆኑ አንዳንድ ጥንዶች ወደ ህንድ እና አውሮፓ በመሄድ መፍትሄ ለማግኘት ይሞክራሉ::

 

በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአይ ቪ  ኤፍ ቴክኖሎጂ ልጅ የተወለደው በፈረንጆች አቆጣጠር በ2005-2006 አከባቢ ሲሆን በጊዜው ይሄንን ህክምና የየሚቆጣጠር ህግናደንብ ባለመኖር ሊቋረጥ ችሏል::

በቅርብ ግዜ ውስጥም የኢትዮጵያ ህግ ለዚህ ዓይነት ህክምና በመፍቀዷ Fertility center /የህክምና መሀከል ሊከፈት ችሏል::

በሚቀጥለው ፁሁፌ የምስራቁን ህክምና የአለመውለድ ችግርን እንዴት እንደሚያክም  በአጭሩ እፆፋለው::

 

ጤና ይሁኑ::

ሰብለ አለሙ Acupuncturist and Herbalist .

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.