ከማዕዳቸው እርድን ቢያርቁ የሚመከሩ ሰዎች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እርድ ላይነን ከሚሰራበት ተልባ መሰል የቃጫ ተክል (ፈላክስ) ቀጥል በአለማችን በስፋት ገበያ ላይ የሚውል ቅመም ነው፡፡

እርድ በውስጡ የያዘው ኩርኩሚን የተሰኘ ንጥረ ነገር ደስ የሚል ሽታ እና ደማቅ ቢጫ ቀለም አላብሶታል፡፡

እርድ በርካታ የጤና በረከቶች እንዳሉት ሁሉ አንዳንድ ሰዎች ሲጠቀሙት የመደበት፤ የማስመለስ እና የሆድ ህመም እንደሚሰማቸው ይናገራሉ፡፡

እርድን ከበርበሬ ጋር ቀላቅሎ መጠቀምም የኩርኩሚን መጠኑ ከ2 ሺህ እጥፍ በላይ እንዲያድግ እንደሚያደርገው ይታወቃል፡፡

ይህም እንደ ደም ግፊት መዛባት ላሉ የጤና እክሎች ይዳርጋል፡፡

በዚህም የተነሳ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እርድ ባይጠቀሙ ይመከራል፡፡

እነዚህም፦

1.    እርጉዝና የምታጠባ እናት

ነፍሰጡር አልያም ጡት የሚያጠቡ ሴቶች እርድ ባይወስዱ ይመከራል፤ ከወሰዱም በከፍተኛ ጥንቃቄ ሊሆን ይገባል፡፡

እርድ የወር አበባ ኡደትን በማዛባት የእርግዝና ሂደት እንዲሰተጓጎል ያደርጋል፡፡

አባት ለመሆን በተዘጋጁ ወንዶች ላይም የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን እንዲቀንስ እና የስፐርም እንቅስቃሴ እንዲገደብ በማድረግ ህልማቸውን የማጨናገፍ እድል አለው ተብሏል፡፡

2.    የሀሞት ጠጠር ያለባቸው ሰዎች

በሀሞት ጠጠር ህመም የሚሰቃዩ ሰዎችም እርድን ከሚወስዱት ምግብ ባይቀላቅሉት ተገቢ መሆኑ ተነግሯል፡፡

3.    ቀዶ ጥገና ለማድረግ የተዘጋጁ ሰዎች

የቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ የተዘጋጁ ሰዎች ከህክምናው ከሶስት ሳምንት በፊት ጀምሮ እርድን ከምግባቸው ውስጥ መጨመር አይኖርባቸውም፡፡

ምክንያቱም እርድ የደም መርጋትን በመቀነስ በቀዶ ጥገና ወቅት ከፍተኛ የደም መፍሰስ እንዲኖር ስለሚያደርግ ለጤና አስጊ ነው፡፡

4.    የኩላሊት ጠጠር ህመምተኞች

እርድ በየቀኑ በብዛት የሚመገቡ ሰዎች በኩላሊት ጠጠር ህመም የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡

5.    የስኳር ህመምተኞች

እርድ በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠንን ስለሚቀንስ የስኳር በሽተኞች የእርድ ፍጆታቸውን መቆጣጠር ይኖርባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ http://wordoflife.me/

በፋሲካው ታደሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.