ህፃናትና በቂ እንቅልፍ

babysleepአዲስ አበባ ፣ ህዳር 10 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህፃናት የእንቅልፍ ሰዓታቸው ሲያጥር ሆድ የሚለቅባቸው ሲሆን ፥ ከመደበኛ የእንቅልፍ ሰዓታቸው ሌላ ቀን ላይ በቂ እንቅልፍ ማግኘታቸውም ለአካልና አዕምሯቸው ጤንነት ወሳኝ መሆኑን ነው ኒውዮርክ ታይምስ ያስነበበው።

ብዙ የጥናት ውጤቶች እንደሚጠቁሙትና በተግባርም እንደሚስተዋለው ፥ ለአንድ ህፃን ከእናት ጡት ባልተናነሰ ፤ አንዳንዴም በበለጠ የሚያስፈልገው ነገር በቂ እንቅልፍ ነው።

በእንቅልፍ ወቅት ተሰርተው ያላለቁ የህፃናት የሰውነት ክፍሎች ይሰራሉ ፣ በተጨማሪም በሰውነት ውስጥ የተከማቹ መርዛማ ነገሮች ይወገዳሉ ፥ በተለይም የህፃኑን አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገት የሚወስነው (ግሮውዝ ሆርሞን) የበለጠ እንዲመነጭና ተግባሩን በትክክል እንዲያከናውን እንቅልፍ ወሳኝነቱ ከፍ ያለ ነው።

የህፃናት የእንቅልፍ ሰዓት እንደየሁኔታው ሊለያይ ቢችልም ፥ አንድ ህፃን በአማካኝ 16 ሰዓታትን በእንቅልፍ እንዲያሳልፍ ነው የሚመከረው።

የህፃኑ ዕድሜ ሲጨምር የእንቅልፍ ሰዓቱም እንደዚያው እየቀነሰ ይሄዳል ፤ ይሁንና ህፃኑ የቻለውን ያህል እንቅልፍ ማግኘቱ ግን እጅግ ተመራጭ ነው።

ህፃኑ ወደ መዋዕለ ህፃናት መሄድ ሲጀምርም ቀን ላይ የተወሰኑ ሰዓታትን በእንቅልፍ ማሳለፉ ፥ ቀኑን ሙሉ ንቁና ቀልጣፋ እንዲሆን ይረዳዋል ነው የሚሉት ባለሙያዎቹ።

በተቃራኒው ቀን ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት እንቅልፍ ያላገኙና መሯሯጥን የሚያበዙ  ህፃናት ሌፕቲን የተሰኘውና ቶሎ ቶሎ ምግብ የሚያሰኘው ችግር ይጠናወታቸዋል ሲልም ነው ኒውዮርክ ታይምስ  በጥናቱ የጠቆመው።

በአዳም ታደሰ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.