አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2011 (ኤፍቢሲ) የዩናይትድ ስቴትስ ተመራማሪዎች የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታን እንደሚያዳብር በጥናታቸው ይፋ አደረጉ፡፡

ተመራማሪዎቹ ይህንን ያረጋገጡት በእድሜ የገፋና አዕምሮው የተዳከመ አይጥ እንዴት የማስታወስ ችሎታውን የመለሰበትን ሂደት ከተከታተሉ በኋላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ በምርምራቸው ሰዎች ከዕድሜ ጋር በተገናኘ የማስታወስ ችሎታቸው ሊቀንስ የሚችለው RbAp48 በተሰኘ የፕሮቲን እጥረት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ይህ ፕሮቲን ከዕድሜ መግፋት ጋር የሚከሰት ሲሆን ሆኖም የፕሮቲን እጥረቱ ለመርሳት በሽታ እንደማይዳርግ አረጋግጠዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ አይጦቹ ላይ RbAp48 የተሰኘውን ፕሮቲን ሰውነታቸው ላይ በሚጨምሩበት ሰዓት የማስታወስ ችሎታቸው መሻሻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ይህ ፕሮቲን አጥንት ውስጥ ከሚገኝ ኦስትዮካልሰን ከተሰኘ ፕሮቲን ጋር ግንኙነት እንዳለው የተረጋገጠ ሲሆን፥ ለማስታወስ ችሎታ መሻሻልም ጉልህ አስተዋፅዖ ያደርጋል ተብሏል፡፡

በዚህም ሰዎች የተስተካከለ የሰውነት እንቅስቃሴ በሚያደርጉበት ወቅት ፕሮቲኑን እንደሚያገኙ ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ሽንዋ
በአብርሃም ፈቀደ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.