ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ (ከአዲስ ጉዳይ መፅሄት)

የማሽላ የጤና በረከቶች ዶ ር ብርሃኔ ረዳኢ   እያረረ በመሳቁ የወግ ማሳመሪያ የሆነው ማሽላ ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታ ከሚሰጡ እህል ዘሮች አንዱ ነው፡፡ በዓለም ላይ ከ30 በላይ የማሽላ ዓይነቶች ያሉ ሲሆን በሰው ልጅ ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ግን Sorghum Bicolor የአፍሪካ ማሽላ ብቻ ነው፡፡ ይህ ዝርያ በመላው ዓለም የሚገኝ ሲሆን በበርካታ ሀገራት በሰፋፊ እርሻዎች ከሚመረቱ እህሎች አንዱ ነው፡፡ ማሽላ በዋነኝነት ለሞላሰስ መስሪያነት፣ ለሽሮፕነትና ለምግብነት ይውላል፡፡ ለአልኮል መጠጦች መጥመቂያነትና ለባዮፊውልነት በመዋልም ላይ ይገኛል፡፡ በዓለም ላይ በስፋት በመመረት በአምስተኛ ደረጃ ይዟል፡፡ የሰው ልጅ በጥቅም ላይ ማዋል ከጀመራቸው የመጀመሪያዎቹ እህሎች አንዱ የሆነው ማሽላ በህንድና በአፍሪካ መመረት እንደጀመረ ይነገራል፡፡ ተነግረው ከማያልቁት የጤና ጠቀሜታዎቹ ውስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

         የካንሰር እድገት ይገታል

      3 Deoxyanthoxyanins (3-DXA) የተሰኘው ንጥረ ነገር በቀይ ማሽላ ውስጥ ከሌሎች በተሻለ በርከት ብሎ ይገኛል፡፡ በሚዙሪ ዩኒቨርሲቲ ሳይንቲስቶች የተካሄደ አንድ ጥናት በጥቁር፣ ነጭና ቀይ ማሽላዎች ውስጥ የትልቅ አንጀት ካንሰርን በመፋለም የሚታወቀው Anti proliferative የተሰኘ ጠንካራ ንጥረ ነገር እንደሚገኝባቸው ‹‹Journal Of Agriculture & Food Chemistry›› የ2009 ሜይ ዕትምባስነበቡት ጥናት ላይ አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማሽላ የያዛቸው በርካታ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የተለያዩ የካሰር አይነቶችን የመከላከል ብቃት እንዲጎናፀፍ አድርጎታል፡፡

     ኮሌስትሮልን ለመቆጣጠር ይረዳል

በኔብራስካ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ሳይንቲስቶች ማሽላ በፓይቶኬሚካልስ የበለፀገ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ይህም ኮሌስትሮልን በመቆጣጠር ረገድ ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ‹‹Journal of nutrition›› የ2005 ሴፕቴምበር ወር ዕትም ላይ ለንባብ በበቃው ጥናታቸው ላይ በማሽላ የሚገኙ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የሰው ልጆች ሰውነት የኮሌስትሮል መጠን እንዲቆጣጠር እንደሚረዳ ፅፈዋል፡፡ በአይጦች ላይ ያደረጉት ሙከራ የተሳካ ውጤት በማስመዝገቡም የእህሉን ዘርፈ ብዙ ጠቃሚነት አረጋግጦልናል ሲሉም ማሽላ ከፍተኛ ተቀሜታዎች እንዳሉት መስክረዋል፡፡

የልብ ጤንነት ጠባቂው ማሽላ

ጆሴፍ አዊካና ሎይድ ሩኒ የተባሉ በአሜሪካ የሚገኘው የA&M ዩኒቨርስቲ ባልደረቦች ሜይ 2004 ለንባብ በበቃው ‹‹photochemistry›› ጆርናል ላይ እንደፃፉት ከሆነ ማሽላ ውስጥ የሚገኘው አንቲኦክሲዳንት በሌሎች የእህል ዘሮችና ፍራፍሬዎች ውስጥ ከሚገኘው ይበልጣል፡፡ ይህ ደግሞ ማሽላን ካንሰር ተከላካይ እና የልብ ጤንነት ጠባቂ ያደርገዋል፡፡

ቫይታሚን እና ሚኒራሎች

    ማሽላ የቫይታሚን ቢ6፣ ራይቦቭላቢን፣ ታያሚን፣ ፖታሲም፣ ማግኒዚም፣ አይረን፣ ማንጋኒዝ ምርጥ መገኛ ነው፡፡ በዳቦ፣ ኬክ፣ እንጀራና ገንፎ ተዘጋጅቶ ለምግብነት መቅረብ የሚችለው ማሽላ በጥቂት መጠን በርካታ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ ከማሽላ በተዘጋጀ 28 ግራም ምግብ ውስጥ 81 ካሎሪ እና በርካታ ሚኒራል እና ቫይታሚኖችን ማግኘት ይቻላል፡፡ በዚህ መጠን ከፍተኛ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የሚይዙ ምግቦች እጅግ ጥቂት እንደሆኑም አጥኝዎች ይስማማሉ፡፡

የሆድ ድርቀትን ይከላከላል በፕሮቲን የበለፀገ ነው

በርካታ ጥናቶች ከፋይበር ነፃ የሆኑ ምግቦች የስልቀጣ ስርዓቱን በማዛባት ለሆድ ድርቀት እንደሚያጋልጡ ይገልፃሉ፡፡ እንደማሽላ ያሉ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦች ደግሞ ምግብ በአንጀት ውስጥ ያለ ችግር እንዲንሸራሸር እና የስልቀጣ ሥርዓቱም በአግባቡ እንዲካሄድ በማድረግ የሆድ ድርቀትን ጨምሮ ሌሎች ችግሮችን ይከላከላሉ፡፡

በፕሮቲን የበለፀገ ነው

የምንመገበው ምግብ 43 ከመቶ የሚሆነው ይዘቱ ፕሮቲን እንዲሆን ይመከራል፡፡ ፕሮቲን ቆዳንና ጡንቻዎችን ጨምሮ የእያንዳንዷን የሰውነት ክፍል ለመገንባት አስፈላጊ በመሆኑ በተፈለገው መጠን መገኘቱ ግድ ነው፡፡ ማሽላ ደግሞ በከፍተኛ የፖሮቲን መጠን የበለፀገ ነው፡፡ እርስዎ በተመቸዎ የአመጋገብ ዘዴ እያዘጋጁ አዘወትረው ሊመገቧቸው ከሚገባ ምግቦች አንዱ መሆን እንደሚገባው በባለሙያዎች ይመከራል፡

ከግሉቲን ነፃ ነው

ማሽላ ከግሉቲን ነፃ በመሆኑ ስንዴ ሲመገቡ አለርጂ ለሚፈጥርባቸው ሰዎች ጥሩ አማራጭም ነው፡፡ በተጨማሪም ተፈላጊውን ኃይል በመስጠት ለአጥንትና ጥርስ ጤንነት አስተዋፀኦ ያበረክታል፡፡

ስኳር በሽታን ይከላከላል

በጆርጂያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተደረገ አንድ ጥናት የማሽላ ገለባ (Bran) የስኳር በሽታ እንዳይከሰት በሚያደርግ ንጥረ ነገር የበለፀገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ተመራማሪዎች የተለያዩ የማሽላ አይነቶች የኢንሱሊን አለመቀበል ችግርንና ስኳር በሽታን እንዳይከሰት ማድረግ የሚያስችሉ አንቲ ኦክሲደንቶች የበለፀጉ ናቸው ብለዋል፡፡

ለአጥንት ጤንነት-ማሽላ

ማግኒዚየም በማሽላ ውስጥ በከፍተኛ መጠን ይገኛል፡፡ ይህም ለአጥንት ጥንካሬ የሚያስፈልገው ካሲየም በአስተማማኝ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል ይረዳል፡፡ ማግኒዚየም ሰውነት ካልሲየምን በአግባቡ እንዲያዋህድ ያስችላል፡፡ የእነዚህ ሁለት ሚኒራሎች ጥምረት የተጎዱ አጥንቶች በቶሎ እንዲያገግሙ፣ የደከሙት እንዲበረቱ ከማድረጉም በላይ የአጥንት ቲሹዎች እድገት እንዲፋጠን ያደርጋሉ፡፡

የደም ዑደትና ቀይ የደም ሴል ዕድገት

ማሽላ ውስጥ ኮፐርና አይረን ይገኛሉ፡፡ ኮፐር ሰውነት የአይረን አጠቃቀሙ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ የደም ማነስ የመከሰት እድልን ይቀንሳል፡፡ በሰውነት ውስጥ በቂ ኮፐርና አይረን ከተገኘ የቀይ ደም ሴሎች የመመረት ሂደትን ያፋጥናል፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል፣ የሴል እድገት እና ጥገናን ያሳድጋል፣ የፀጉር እድገትን ይጨምራል እንዲሁም የሰውነትን የኃይል መጠን ያሳድጋል፡፡ አንዴ የምንመገበው ከማሽላ የተሰራ ማዕድ ከቀን የአይረን ፍላጎታችን ውስት 58 ከመቶ የሚሆነውን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.