ቁምላቸው አባተ (ሜዲካል ዶክተር-ዕንቁ)

blood_pressure_2ከፍተኛ ‹‹ደም ግፊት›› ልብን፣ ጭንቅላትንና ኩላሊትን አደጋ ውስጥ የሚከት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ምልክቶችን አያስከትልም፡፡ ነገር ግን አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሌም የደም ግፊት መጠንዎን ማወቁ በእጅጉ መልካም ነው፡፡ የጤና ባለሙያው የደም ግፊት መጠኑን ለክቶ ሁለት ቁጥሮችን ይነግሮታል፡፡ ለምሳሌ 140 በ90፡፡ የመጀመሪያው ቁጥር (140) ልብ ደም በምትረጭበት ጊዜ ደም ቅዳዎች ውስጥ የሚኖረው ግፊት ሲሆን የታችኛው ቁጥር (90) ደግሞ ልብ ደም ለመቀበል ጡንቻዎቹ ዘና በሚሉበት ጊዜ በደም ቅዳዎቹ ውስጥ ሚኖረው የደም ግፊት መጠን ነው፡፡ ደም በሰውነት ሁሉ መዘዋወሩ በልብ ግፊት ሀይል እንደሆነ አይዘነጋም፡፡ ‹‹ደም ግፊት›› አለብኝ ሣይሆን ከፍተኛ ‹‹ደም ግፊት›› አለብኝ ሲባል ትክክል ይሆናል፡፡

ከፍ ያለ ደም ግፊትን እንዴት ማውረድ ይቻላል? ባለሞያው መድሀኒቱን በሚዎስዱበት ጊዜ ተጓዳኝ ችግሮች ቢመጡ እነኳን መድሀኒቶን ከማቋረትጥዎ በፊት ባለሙያ ያማክሩ፤ መጠኑን ሊቀንሱት ወይም ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡ የመድሀኒቱ ዋጋ ካሳሰብዎትም ከመጠየቅ ወደኋላ አይበሉ፡፡ ተመሳሳይ ጥቅም ባለው ረከስ ባለ መድሀኒት ሊተካ ይችላል፡፡ መድሀኒት በአግባቡ መውሰድ ህመሙን ተከትለው ከሚከሰቱ የልብም ይሁን የጭንቅላት ህመሞች ራስን መጠበቅ ነዉ፡፡

በሽታውን ለመቆጣጠር በራስዎ ምን ማድረግ ይችላሉ?

ደም ግፊትን ለመቆጣጠር ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ዝቅ ለማድረግ፡-

 • ክብደትዎ ከፍ ያለ (ወፍራም)ከሆነ ይቀንሱ@
 • ምግብዎ በአትክልትና ፍራፍሬ የበለጸገ ይሁን& ቅባት ይቀንሱ@
 • የሚመገቡትን የጨው መጠን በእጅጉ ይቀንሱ@
 • በሳምንቱ ቀናት በአብዛኛዎቹ ቢያነስ በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እነቅስቃሴ ያድርጉ@
 • አልኮል የሚጠጡ ከሆነ ይቀነሱ@

ከቤትዎ የደም መለኪያ ካለ የሚወስዱት መድሀኒትና ማደረገ በሚገባዎት ያአኗኗር ዘይቤ ለወጥ ከሀኪምዎ ጋር እየተማከሩ ሊቀጥሉ ይቺላሉ፡፡ እንደ ደም ግፊትዎ ለውጥም የመድሀኒትዎን መጠን የማስተካከል አጋጣሚ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

የአኗኗር ዘይቤ ከደም ግፊት ከፍታ ጋር ምን ያያይዘዋል?

የሚያደርጉትና የሚመገቡት በደም ግፊት መጠንና በጠቅላላ ጤናዎ ላይ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡ እናም ትክክለኛውን አኗኗር ዘይቤ መከተል ይጠበቅብዎታል፤ መጀመሪያ ጨርሶውኑ ደም ግፊትዎ ከፍ እንዳይል፣ ከጨመረም ዝቅ እንዲል ማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

 • ለደም ግፊት ማስተካከያ ሚያስፈልጉ መዳኒቶችን አስፈላጊነት መቀነስ፤
 • መድሀኒት የሚወስዱ ከሆነ መዳኒቶቹ በተሻለ ደረጃ እንዲሰሩ ማድረግ፤
 • በልብና በሌሎች አካላት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የጤና አደጋዎችን ማስቀረት፤

ከላይ ከተጠቀሱት አኗኗር ዘይቤ ለውጦች ባሻገር ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ያቁሙ፡፡ ማቆም የደም ግፊት መጠንን ዝቅ ላያደርገው ይችላል፡፡ ነገር ግን የጭንቅላትም ይሁን የልብ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን እድል ይቀንሳል፡፡

ሲጋራ ማቆም የተሻለ ስሜት እንዲሰማዎትና እድሜና ማራዘም ዕድል ይፈጥራል፡፡ በትንሹ ይጀምሩ፣ ቀስበቀስ ይራመዱ፡፡ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን በአንድ ጊዜ ማሰብና መከወን ሊከብድ ይችላልለ፡፡ መጨነቅ አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም በአንድ ጊዜ መለወጥ አያሻዎትም፡፡ ቀስበቀስ ግን ማሳካት ይቻላል፡፡ አንድን ነገር ልምድ እስከሚያደርጉት ይከውኑት፡፡ ባይሳካ እንኩዋን ተስፋ አይቁረጡ፡፡ ደግሞ ሌላኛውን መርጠው ይሞክሩት፤ ለውጡንም ያስተውሉት (ጊዜ ይስጡ-ይታገሱ)፡፡

ምሳሌ፡- እርስዎ አመጋገብዎትን መለወጥ ፈለጉ፡፡ ስጋ አዘወታሪ ነዎት እንበል፤ ባንድ ጊዜ ወደ ሰላጣ፣ ጎመን ወዘተ ላይ ሊያተኩሩ እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡ ባንድ ጊዜ ለውጥ ማድረግ ከስኬት ያርቃል፡፡ ተስፋ ስለሚያስቆርጥ መልሶ ለመሞከር እክል ሊሆን ይችላል፡፡ ውጤታማ ለመሆን በአንድ ቀን መለወጥ ሳይሆን ከተለመደ ምግብዎ ላይ አንድ ሁለት ነገሮችን በመጨመር ለራስዎ ጊዜ ይስጡ፡፡ መለወጥ የሚችሉትን የአኗኗር ዘይቤ ሲያገኙ ያዳብሩትና አዲስ ለውጥ ይጨምሩ፡፡ በጊዜ ብዛት ብዙ ነገሮችን መለወጥ እንደሚችሉ ያስተውሉ፡፡

ክብደት መቀነስ፡-

ክብደት ለመቀነስ ቀላሉ መንገድ ትንሽ መብላት ወይም ብዙ መጓዝ ነው@ ሁለቱንም ማድረግ ከቻሉ ደግሞ የበለጠ ውጤታማ ይሆናሉ፡፡ ይሄኛዉ አመጋገብ ከዚህኛዉ እንቅስቃሴ የተሻለ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል የሚል መንገድ የለም፡፡ ዋናው ነገር ያዘወተሩት መንገድ ውጤታማ እንደሚሆን ያስተውሉ፡፡

አመጋገብዎትን ያሻሽሉ፤ ለሁሉም ሰው ተስማሚ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ የለም፡፡ ባጠቃላይ ጤናማ አመጋገብ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡

 • food-to-help-high-blood-pressureብዙ ፍራፍሬ፣ አትክልትና ጥራጥሬ፣
 • መጠነኛ ባቄላ አተር፣ ምስር፣ ሽምብራና ተመሳሳ ምግቦች፣
 • መጠነኛ ለውዝና ተመሳሳይ ምግቦች፣
 • ቅባት ያልበዛበት ወተትና የወተት ውጤቶች፤
 • መጠነኛ አሳ፤

ስኳር መተው ወይም መቀነስ እንዲሁም ሌሎች ጣፋጮችን፣ ሥጋን እንዲሁም የተጣራ የጥራጥሬ ውጤቶችን መቀነስ ወይም መተው ጤናማ አመጋገብ ማለት ነው፡፡ (በነገራችን ላይ የተጣራ ጥራጥሬ ውጤቶች የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል፡፡ ነጭ ዳቦ& ነጭ ሩዝ&ፓስታ ወዘተ…)

ጨው መቀነስ፡-

ጨው የተለያዩ ምግቦች ውስጥ ሊኖር ስለሚችል ማባያዎች ላይ ብቻ አናተኩር፡፡ ማባያዎች ላይ ቀጥታ ጨው አለመጨመራችን ምግባችን ላይ ጨው የለም ማለት አይደለም፡፡ ገዝተን የምንጠቀማቸው ምግቦችና መጠቶች ካሉ (ለምሳሌ ቆሎ& የመአድን ዉኃ ወዘተ…) ጨው ይኖራቸዋል፡፡ የታሸጉ ምግቦችን አለማዘውተር መልካም ነው፡፡ ከተቻለ በቤት የተዘጋጁ መግቦች ላይ ማዘውተር ይመረጣል፡፡ ትኩስ አትክልት& ፍራፍሬ እና ስጋ መጠቀም የምንወስደውን የጨው መጠን ለመቀነስ አይነተኛ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ጨውም ለመቀነስም ሆነ ለማቆም ውጤታማ ለመሆን ደረጃ በደረጃ ቢሆን ይመረጣል፡፡

የበለጠ ንቁ መሆን፡-

ጥሩ እንቅሰቃሴ አድርገዋል ለማለት የግድ ስፖርት ቤት መሄድ ወይም ላብ በላብ እስኪሆኑ ስፖርት ሠርተዉ መገኘት የለብዎትም፡፡ ደስ የሚልዎትን የተለመዱ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ በእግርዎ የሚያደርጉትን ጉዞ ረዘም ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማያደርጉ ከሆነ አንድ ቀን አልፎ አንድ ቀን ለጥቂት ደቂቃዎች እንቅስቃሴ ያድርጉ፡፡ ለጥቂት ሳምንታት በዚሁ ቀጥለው እየጨመሩ መሄድም ተመራጭ ነው፡፡ በቀን ከ20 እስከ 30 ደቂቃ መንቀሳቀስ የደም ግፊት መጠንን ዝቅ ያደርገዋል፡፡ እንቅስቃሴው በሚቋረጥበት ጊዜ ተመልሶ ከፍ ሊል ስለሚችል አለማቋረጡ ተገቢ ነው፡፡

     ብዙ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ፡-

እነዚህ ምግቦች ላይ ቢያተኩሩ የደም ግፊት መጠን ይቀንሳል፡፡ ነገር ግን የግድ የቬጂተርያን አመጋገብ መሆን ላይኖርበት ይችላል፡፡ ብዙ አትክልትና ፍራፍሬ አነስተኛ ቅባት ካላቸው ምግቦች ጋር ተዋህዶ ቢወሰድ የደም ግፊት መጠንን ሊቀንስ ይችላል፡፡

ብዙ ዓሣ መብላት፡-

ክብደት ለመቀነስ ይረዳል በተለይ ከሌሎች ክብደትን ለመቀነስ ከምናደርጋቸው እርምጃዎች ጋር ከተጣመረ የበለጠ ውጤታማ መሆን ይችላል፡፡

        ቡና መጠጣት፡-

የደም ግፊት መጠንን በተወሰነ መልኩ ከፍ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይሄ ግን ብዙውን ጊዜ ጊዜያዊ ነው፡፡ ለአባዛኛው ሰው በቀን ሁለት ሲኒ ቡና ደም ግፊት መጠንን አይጨምርም፡፡

እንግዲህ ቀለል ከሚልዎት ለውጥ መጀመር መልካም ነው፡፡ ለምሳሌ እንቅስቃሴ ያደርጉ ከነበረና አቋርጠውት ከሆነ እንቅስቃሴውን መጀመር ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ሲጀምሩ ብዙ እንቅስቃሴ አደርጉለሁ ማለት ጥሩ አይሆንም፡፡ በሳምንት ሦስት ቀናት በቀን ለአስር ደቂቃዎች ለሁለት ሳምንታት በእግሬ ጉዞ አደርጋለሁ ብለው ቢያስቡ ለራስዎ ግልፅ ግብ አስቀምጠዋል ማለት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይም  የአኗኗር ዘይቤን ማሻሻል  የደም ግፊቱ ከፍ ላለበትም ይሁን ለሌላው መሰረታዊ ጥቅም ይቸራል፡፡ ደም ግፊት መጠንን መቀነስ፣ ደም ግፊት ከፍ እንዳይል መከላከል፣ የደም ግፊት መድኃኒትን ውጤታማነት ማሻሻልና በልብ እና በደም ስር ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ ያስችላል፡፡ ትኩረታችን በመጠንና በጊዜ ሰፋ ባለ ቁጥር ደም ግፊትን በለወትነው አኗኗር ዘይቤ ማለትም ክብደትን ማስተካከል፣ ብዙ አትክልትና ፍራፍሬ መብላት፣ቀባት መቀነስ፣ ጨው መቀነስ፣ ተከታታይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አልኮል መቀነስ፣ሲጋራ ማቆም ወዘተ በማድረግ በቀላሉ መከላከል ወይም መቆጣጠር ይቻላል፡፡ ደም ግፊትን በመከላከል ወይም በመቆጣጠር ከልብና ከኩላሊት ህመም ራሳችንን እንጠብቅ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.