ሜዲካል ጋዜጣ

  • በአለም ላይ 50 በመቶ የሚሆኑት ወፍራም ሰዎች በ10 ሀገሮች ብቻ ይገኛሉ!

ባለፉት ሥስት አስርት አመታት ከመጠን በላይ የወፈሩ ሰዎች ቁጥር ከ857 ሚሊዮን ወደ 2.1 ቢሊዮን ማሻቀቡን ጥናቶች አመላከቱ፡፡

ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው ከሆነም አሜሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወፍራም ሰወች ያሉባት አደር ሆናለች፡፡ ይህም በአሀዝ ሲገለፅ 13 በመቶ ሚሆኑ ወፍራም ሰዎች ባሜሪካ ይገኛሉ፡፡

ከመጠን በላይ የሚከሰት ውፍረት በአደጉት ሀተራትም ሆነ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ዋነኛ የማህበረሰብ ጤና ጠንቅ መሆኑን በዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ የሄልዝ ሜትሪክስ ኤንድ ኢቫሉዌሽን (Health metrics and Evaluation) የተሰኘዉ ተቋም የሚገኙ አጥኚዎች አሰስታውቀዋል፡፡

ከመጠን ያለፈ ውፍረት በወንዶች ላይ ከ29 ወደ 37 በመቶ የጨመረ ሲሆን በሴቶች ላይ ደግሞ ከ30 ወደ 38 በመቶ መጨመሩ ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በወንዶች ላይ የሚታየው ከመጠን ያለፈ ውፍረት በታዳጊ ሀገራት ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በህፃናት ላይ የሚታይ ከልክ ያለፈ ውፍረት ከ1980 እሰከ 2013 በ50 በመቶ የጨመረ ሲሆን በ2013 በአደጉት ሀገራት 22 በመቶ የሚሆኑ ህፃናት ወንዶች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ግን በህፃናት ሴቶችም ላይ 13 በመቶ የሆነ ጭማሪ ማሳየቱ ታውቋል፡፡

በህፃናት ላይ የሚታየው ከፍተኛ የሆነ ውፍረት በተለይ ዝቅተኛ እና መካክለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ በስፋት እነደሚታይ የጥናት አቅራቢዎቹ አስታውቀዋል፡፡

ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሀፃናትን ለመተንፈሻ አካላት በሽታ& ለስኳር ህመም እንዲሁም ለካንሰር በሽታ  ስለሚያጋልጣቸዉ ሊታሰብበት እንደሚገባ ተመራማሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ጥናቱ አክሎም 50% ወይም 671 ሚሊዮን የሚሆኑት የአለማችን ወፍራሞች የሚገኙት በ10 ሀገራት ብቻ መሆኑን ጠቅሶ ሀገራቱም አሜሪካ& ቻይና& ህንድ& ሩሲያ& ብራዚል& ሜክሲኮ& ግብፅ& ጀርመን& ፓኪስታን& እና ኢንዶኔዥያ መሆናቸዉ ተጠቁሟል፡፡

ውፍረት በሁሉም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችልና ከፍተኛም ሆነ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎችን ሊያጠቃ እንደሚችል  የገለፁት የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ክርስቶፎር መሬይ ሲሆኑ ባለፉት ሶስት አስርት አመታትም አንድም ሀገር ውፍረትን በመቀነስ ረገድ ስኬት አለማስመዝገቡን ጠቁመው አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ የማህበረሰቡነን ቴና በእጅጉ እንደሚጎዳ አሰታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.