‹‹ፌንት (Fainting)›› ማድረግ (ዶ/ር ቁምላቸው አባተ)

ዶ/ር ቁምላቸው አባተ

እንደ  አብዛኛው ተመላላሽ አገላለፅ‹‹ፌንት›› ማድረግ & ራስን ለአፍታ መሳትና ከዛም ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደቀደመው የጤና ሁኔታ መመለስ ነው፡፡ ፌንት ማድረግ ለታማሚው ፤ተመልካቹ፤ለቤተሰብ፤ለ፤ባለሙያ ወዘተ… አሰደንጋጭና አሳሳቢ የሆናል፡፡ ምንም እንኳ የብዙ ሀመሞች አማላካች ጠቋሚ ቢሆንም ፌንት ማድረግ በአብዛኛው ለክፉ የማይሰጥና በራሱ የሚሽር ነው፡፡

fainting‹‹ፌንት›› ማድረግ ከልብ ስራ ማቆም (‹‹ልብ ቀጥ›› ከማለቷ)ጋር ለዩነት አለው፤ ልቡ ቀጥ ያለበት ሰው ራሱን በድንገት ይስታል፤ አብዛኛውን ጊዜን የለምንም ህክምና ርዳታ በሞት ይለያል፡፡ ፌንት ያደረገ ሰው ግን ራሱን ቢስትም ያለምንም ህክምና ያውም በፍጥነት ይሳለዋል፡፡

ራስን ለቅፅበት መሳት ለመውደቅ፤ ለመጋጨት ወዘተ… ስለሚዳርግ ከሶስት ታማሚ አነዱ አካላዊ ጉዳት ይደርስበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የተረጋገጠ የለብ ህመም ባለባቸው ህሙማን ፌንት ማድረጋቸው በልብ ላይ የተጋረጠ አደጋን (ለምሳሌ የልብ ድካም)ጠቋሚ ሊሆን የችላል፡፡

የተለያዩ የጤና ችገሮች ፌንት ለማድርግ መነሻ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የሚጥል በሽታና የስኳር ማነስን መጥቀስ የቻላል፡፡ የሆነው ሆኖ ራስን በቅፅበት የመሳት ህመምን ለመከላከልም ይሁን ለማከም መነሻ ምክንያቱን መለዳት መልካም ነው፡፡

‹‹ፌንት›› ማድረግ በጣም የተለመደ ችገር ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው የማህበረሰብ አባል በህይዎት ዘመኑ ቢያነስ አንድ ጊዜ ፌንት ያደርጋል፡፡ ምንም እመረኳን ለአንዳንድ ሰወች የአሳሳቢ ጊዜ ለህይወት የሚያሰጋ አይደለም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እድሜያቸው ባልገፋ ሰዎች ዘንድ ፌንት ማድረግ ከምንም የህክምና ችግር ጋር የሚገናኝ አሆንም፡፡ ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ አካዊም ሆነ ስነልቦናዊ ህመሞችን በማሰብ እንዲሁም ምንም እንኳን እድሉ አነስተኛ ቢሆንም ከባድ መንስኤ ሊኖር ይችላል በሚል ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸው ተገቢ ነው፡፡

መነሻ ምክንት፡-

አንድ ሰው ንቁ ሆኖ እንዲቆይ በኦክስጅን የበለፀገ ደም ያለምንም ማቋረጥ ወደ አንጎል ሊደርስ ይገባል፡፡ አንጎል ይሄንን ደም ለአፍታም ቢሆን ካጣ ፌንት ማድረግ ይከተላል፡፡ የተለያዩ የጤና ሁናታዎች ችግሩን ሊያስከትሉ የችላሉ፡፡ በጣም የተለመዱ ምክንያቶችን ለመግለፅ ያህል፡

1-ከልብና ከነርቭ ስርአት ጋር የተያያዘ ራስን ለቅፅበት የመሳት ችግር

ይሄ በጣም ከተለመዱት ፌንት የማድረግ መነሻ ምክንያቶች አነዱ ሲሆን፤ የተለያዩ ሁኔታዎች ሊያስነሱት ይችላሉ፡፡ አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ጫና (ውጥረት)፤ የሰውነት የፈሳሽ መጠን እጥረትለ፤ መድማት፤በማናቸውም ምክንያት የተነሳ ስቃይ መከሰት ወዘተ… ከተጠቀሱት አነዱ ወይም በሁሉን የልብ ምት በአስገራሚ ሁኔታ የቀንሳል፤ የደም ስሮች ይሰፋሉ (ይለጠጣሉ)፤ ደም በእግር አካባቢ የቋጥራል፤ የደም ግፊት መጠንም አነስተኛ ይሆናል ወደ አንጎል የሚሄደው የደም መጠን የቀንሣል፡፡

አደጋ የከሰታል ብሎ መፍራት፤ ለከፍተኛ ሙቀት ተጋላጭነት ደም፤ ማየት፤ ከባድ ሰቃይ ወዘተ… ፌንት ማድረግ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ትክክለኛ ያልሆነ የነርቭ ስርአት ምላሽ (ለምሳሌ ለማሳል፤ ለመዋጥ፤ ለመሽናት ወዘተ…)እንዲሁ መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡አነዳንዳም ከነአካቴው ምንም በመነሻ ንክንያት ላይኖር የችላል፡፡

ከልብና ከነርቭ ስርአት ጋረ የተያያዙ ራስን ለቅፅበት የመሳት ችግር ከመከሰቱ በፊት በአብዛኛው አመላካች ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡ መጫጫን፤ ማቅለሽለሽ፤መገርጣት፤ ማላብ የመሳሰሉት፡፡ የደም ገፊት መጠኑ ዝቅ ባለበት የሚቀጥል እስከሆነ ድረስ ምልክቶቹ ይቀጥላሉ፡፡ በአንዳነድ ሰወች ዘንድ ከመጠን በላይ የድካም ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡

2-የልብ ምት ችግሮች

ጎታታ የልብ ምት (የልብ ምት መጠን ማነስ)በሚኖርበት ጊዜ ወደ አንጎል የሚፈሰው የደም መጠን ይቀነሳል፡፡ የልብ ምትን እና የርምጃ ምጣኔን የሚዎስነው የኤሌክትሪክ ምልክት መዘጋት የሚደረስበት ጊዜ የልብ ምት መስተጓጎሉ ከልክ በላይ ከሆነና መቱ ዘገምተኛ ከሆነ ወደ አንጎል የሚሄደ የደም መጠን የቀንሳል፡፡

የልብ ትርታ መፍጠን በሚከሰትበት ጊዜ ልብ በበቂ ሁኔታ ራሷን በደም የምትሞላበት ጊዜ ሰለምታጣ በቂ ደም ለመርጨት አትችልም፡፡ ልብ በግልቢያ ላይ እንጂ በደንብ እየረቸች ባለመሆኗ ወደ አንጎል የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል፡፡ ከልብ ወደሰውነት የሚኖገው የደም ፍሰት መዘጋት መነሻ ችግሩ መነም ሆነ ምን ፌንት ማድረግን ያስከትላል፡፡

አንድ ሰው ከነበረበት ቦታ ተነስቶ ሲቆም ወይም ሲቀመጥ የደም ግፊት መጠን ዝቅ ማለት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይሄ የሚከሰትበት ጊዜ ወደ አንጎል የሚፈሰው የፈም መጠን አነስተኛ የሆናል ፌነት ማድረግ ይከተላል፡፡ ከመቀመጥና ከመኮም ጋር ተያይዞ የሚከሰት የደም ግፊት መጠን ማነስ በመድማት ወየም ከመጠን በላይ የሰውነት ፈሳሽ በማጣት&የደም መጠን መሰተካከልን ሊያስተጓጉሉ በሚችሉ መድሀኒቶች (ለመጨናነቅና ለደም ግፊት የሚሰጡ መድሀኒቶች)ወዘተ፤ የነረቭ ስርአቶች ሊያዛባ ሚችሉ ህመሞች አልኮል መጠጣት (አልኮል መጠጣት የደም ስሮች እንዲለጠጡ ስለሚያደርግ የደም ግፊትን ዝቅ አድርጎ ፌንት ማድረግን ያስከትላል) የመሳሰሉት ያስከትሉታል፡፡

                            የባለሙያ አስፈላጊነት፡-

ፌንት የማድረግ ችግር የደረሰበት ሰው ባለሙያ ማማከር አለበት፡፡ ራስን ለቅፅበት መሳት ብዙን ጊዜ አሳሳቢ ባይሆንም አካላዊ ጉዳቶች ግን የተለመዱት ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ በተከሰተ ቁጥር ደግሞ ስነልቦናዊ ጉዳቶች እንዲሁን እተባባሰ የመጣል፡፡ እርስዎ ፌንት የሚደርግዎት ከሆነ መነሻ ንክንያቱን ማዎቅ ተገቢ ነው፡፡ ባለሙያ የልብ ትርታ መጠን፤ የደም ግፊት ልክ፤ ልብዎን የማዳመጥ ስራ ወዘተ…ያድርጉ፡፡

ባለሙያ ጋር የሄደ አንድ ሰው ፌነረት ከማድረጉ በፊት፤ ባደረገበት ሰአተና ቡሀላ የነበረው ስሜት በግልፅ፤ እወሰደ ያለውንመድሀኒት ማበራራት የጠበቅበታል፡፡ የልብን ኤሌክትሪክ ንቅስቃሴ በመለካት የልብን ትርታ ምጣኔ ትክክለኛ መሆንና አለመሆን የሚያረጋግጠው ኢሲጂ(Electro cardio graphy ) ሊታዘዝ ይችላል፡፡ የልብ ትርታ በቤት ውስጥ መቆጣጠሪያ መሳሪያ “የለበሠ” ወይም የተደረገለት ሰው የእለት ከእለት ስራዎቹን ይቀጥላል፡፡የልብ ትርታውም ለአንድ ወይም ለሁለት ቀናት የመዘግባሉ፤ አለበለዘያም ሌሎች መሳሪያዎች ደግሞስሜቶች (ምልክቶቹ) ሲኖሩት ጠቋሚ ቁልፎች በመንካት የልብ ትርታን ይመዘግባል፡፡ በመሮጫ ማሽን እንቅስቃሴ እያደረጉም የልብን የኤሌክትሪክ እነቅሰቃሲ በኤሴግ ምምዝገብና በመሳሰሉት ምርመራዎች በባለሙያ ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡

መከላከል፡-

ችግሩ የገጠመው ሰው ዳግመኛ ፌንት ላለማድረግ የመሚከተሉትን መተግበር ይገባዋል፡፡

–      በባለሙያ በመታገዝ መነሻ ምክንያቱን ማወቅ፤ ማስተካከል ርምጃዎችን መውሰድ ከተቻለን ሁኔታዎቹን ጨሩሶ ማስወገድ፤

–      ፌንት ሊያደርጉ ከመሰልዎት በጀርባዎ ተኝተዉ አግረዎን ከፍ ማድረግ ይገባዎታል፤ ሲቀመጡሙ ሆነ ሲቆሙ የደም ገፊት መጠንዎ ዝቅ እንዳይል የሚከተለ፤ትን ማድረግ ተገቢ ነው፤ እስከ ጉልበት የሚደርሱ ተለጣጭ ስቶኪንጎች (ካለሲዎችን) ማድረግ ደም እግርዎ ላእ እንዳይጠራቀን ይረዳሉ፡፡ ከመቆምው በፊትና ተነስተው በቆሙበት ሰአት የእግርዎን ጡንቻወች ማጠንከር፤ ከተኙበት ወይም ከተቀመጡበት ሲነሱ ቀስ ብሎ መነሳትም የመረጣል፤

ህክምና፡-

ህክምናው በመነሻ ምክንያቱ የሚዎሰን የሆናል፡፡ ጨርሶውኑ ህክምና ማድረግ ላስፈልግም የችልል፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ግን የሚከተሉትን ህክምናዎች ሊያካትት ይችላል፡፡

–      በሀኪም ትእዛዝ የልብ ምት ፍጥነት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች መጠቀም፤ እርምጃ መጣኝ መሳሪየ(pace maker) ከቆዳስር ውለው በቀጫጭን ሽቦዎች ከልብ ጋር ይያያዙና የልብን ምት የማሰተካከል ወይም አስተካከለ ሀረግ እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡

ማስታወሻ፡-

ራስን ለቅፅበት መሳት በሀፃናትም ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ እንደአዋቂወች ሁሉ ለህፃናትም አብዛኛዉን ጊዜ አሳሳቢ አይደለም፡፡ ፌንት ያደረገው በልብ ህመም አልያም በሌላ የጤና ችግር ሊሆን ስለሚችል ህፃኑን ባለሙያ ጋር ዎስዶ ማሰመርመር የግድ የላል፡፡

በልጆች ላይ ፌንት ማድረግን የሚያስከትሉት ሌሎች ምክንቶች ትንፋሽ መያዝ፤ በከሰል ጪስ (ሙሉን ባልተቃጠለ ካረቦን ወይም አየር)መታፈን፤ መድሀኒት ወይም አልኮል መውሰድ ወየም በደም ውስጥ የስኳር ማነስ ሊሆን የችላሉ፡፡

ኃላፊነት፡-

መኪና እያሽከረከረ ፌንት ያደረገ ሰው ለራሱ በዙሪያዉም ካሉ ሁሉ ከባድ አደጋ የሆናል፡፡ ሌሎች ለአደአደጋ የሚያጋለጡ ማሽኖች ቢሆኑ ሙሉ ነቃትን የኒጠይቁ ናቸው፡፡ በተለይ ደሞ እንዲህ አይነት ችግር ያለበት ሠው በህክምና አገለገሎት ማግኘት፤ አደጋ ሊያደርሱበት ከሚችሉ ማሽኖች የሁን መኪና ከማሽከርከር መቆጠብ ይኖርበታል፡፡ የፌንት ማድረጉ መነሻ ካልታወቀ ወይም ያለምንም ማስጠንቀቂያ ምልክት ፌንት የሚያደርግ ሰው ጨርሶውኑ ማሽከርከር የለበትም፡፡

መደምደሚያ፡-

ራስን ለቀፅበት የመሳት መነሻምክንያት በዙን ጊዜ በግለፅ እንደማይታወቅ ቀደም ሲል ተብራርቷል፡፡ ራስን የመሳቱ ነገር እውነት ነው ወየስ አይደለም ብለ፤ መሎ መለየቱ መልካም ነው፡፡ ከአንድ አንድ አይነቱ የሚጠል በሽታ መለየትም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ የህክምና ባለሙያ ርዳታን የማግኘት መሰረታዊ ጥቅሙ ምልክቱ ፌንት ማድረግ ነው ወይስ አይደለም?መነሻ ምክንያቱ ይታወቃል?…እና የልብ ህመም ወይም ለህይወት ሊያሰጋ የሚችል ሌላ የጤና ችግር አለ?የሚሉ ጥያቄዎች የሚመልስ በመሆኑ ነው፡፡

በቸር እንሰንብት፡፡፡፡፡

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.