ዶ/ር አብርሃም ክብረት

Sleepwalkerጥያቄ፡-  ለሜዲካል ጋዜጣ የሀኪምዎን ያማክሩ አዘጋጅ ለአንተ ያለኝን ክብርና አድናቆት እየገለፅኩ ሠላምና ጤናን እመኝልሀለሁ፡፡ እኔ መፈጠርን የሚያስጠላ አንድ መፍትሄ ላገኝበት ባልቻልኩት ችግር የተነሳ ህይወቴ ተመሰቃቅሎብኛል፡፡ በተጨማሪም ተስፋ እንድቆርጥና እንዳዝን ያደረገኝ ደግሞ በእኔ ላይ እየተከሰተ ያለውን ችግር በሌላ ሰውም ላይ ደርሶ አለማየቴ ነው፤ ችግሩ በእኔ ብቻ ላይ የደረሰብኝ እኔ ልዩ ፍጡር ስለሆንኩ ይሆን እንዴ? እላለሁ፡፡

አሁን እድሜየ 20 ሲሆን በአንድ የግል ኮሌጅ እማራለሁ፡፡ ችግሬን ከሌላው ሰው የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ሰው ሁሉ እንቅልፉን የሚተኛውም ሆነ የሚጨርሰው አልጋው ላይ ሆኖ እያለ እኔ ግን አልጋየ ላይ ተኝቼ እያለ ከእንቅልፌ የምነቃው ግን ከመኖሪያ ቤቴ ብዙ ርቄ መንገድ ላይ እየተጓዝኩ ነው፡፡ ይገርምሀል መኖሪያ ቤታችን ያለው ወደ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቢሆንም እኔ ግን ቦሌ መድሀኒያለም አካባቢ፣ ኦሎምፒያ አካባቢ፣ ቀለበት መንገድ ውስጥ፣ ካሳንችስ ቶታል አካባቢ፣ ፍልውሀ ድረስ ሳይቀር መንገድ ላይ እየተጓዝክ ከእንቅልፌ የነቃሁበት ጊዜ አለ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ በጣም እርቄ በምጓዝበት ወቅት ፖሊሶች ስለማይዙኝ ነው ከእንቅልፌ የምነቃው፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ በማጅራት መችዎች አማካኝነት ተመትቼ ሞባይሌን እና ከኪሴ ውስጥ ያለውን ገንዘብ የተዘረፍኩ ሲሆን፣ አራት ጊዜ ያህል የጎርፍ መውረጃ ትቦ ውስጥ ገብቼ አንድ ጊዜ እግሬ ተሰብሮ ነበር፡፡ ውድ የሀኪሞን ያማክሩ አዘጋጅ ይህ በእኔ ላይ ተከስቶ እያሰቃየኝ ያለው ችግር እርግማን ነው ወይስ በሽታ? በሽታው በሃኪም ይታወቃል ወይ? የሚታወቅ ከሆነስ ምን የሚሉት በሽታ ይሆን? በምን ምክንያት የሚመጣ ችግር ይሆን? መፍትሄ ካለውስ ምን ይሆን? ህክምናውን ለማግኘት የምችለው የትና በማን ነው? ቦታውን ብትጠቁሙኝ በኔ በኩል ላደርጋቸው የምችላቸው የመፍትሄ አማራጮች ይኖሩ ይሆን? ካለስ ብትጠቁኝ? መልስ፡- ውድኤፍ.ዲ ይህ ባአንተ ላይ የተከሰተው ችግር (sleep walking) እየተባለ ይጠራል፡፡ ትርጓሜውም በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ከአልጋ ተነስቶ መጓዝ ማለት ነው፡፡ ሀኪሞች ሁኔታውን የበሽታው ምልክቶች ምንድ ናቸው?

  1. በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ መራመድ ወይም ሌሎች ተግባራትን ማከናወን ለምሳሌ የቁም ሳጥንዎን በር መክፈት፣ የቤት በር መክፈት፣ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ወይም ደግሞ መኪና ማሽከርከርም ሊሆን ይችላል፡፡ በርግጥ ይህ ህመም ያለባቸው ሰዎች መኪና ካላቸው በእንቅልፍ ልባቸው ከመኝታቸው ተነስተው የቆመች መኪናቸው ውስጥ በመግባት እና ሞተሯን በማስነሳት ከአካባቢያቸው ወጥተው ከተማ ውስጥ ባሉ መንገዶች ውስጥ መኪናችውን ሊያሽከረክሩ ይችላሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች በዚህ ወቅት በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ ሊያስከትሉት የሚችሉት አደጋ ለመገመት አይከብድም፡፡
  1. በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ተነስቶ የመንቀሳቀሱ ድርጊት አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ነው፡፡ በጊዜ ማለት ነው፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ ቤተሰቡ ወይም አካባቢው ሰዎች ገና ሳይተኙ ስለሚሆን የሰውየውን የልተለመደ ሁኔታ በመመልከት ብዙ ርቆ ሳይሄድ ሊደርሱበት ይችላልሉ ማለት ነው፡፡ ግለሰቡ ከቤቱ ወጥቶ በጣም ርቆ ሊሄድ የሚችለውም በተለይም ክስተቱ የተከሰተው ከለሊቱ ስድስት ሰአት በኋላ ከሆነ ነው፡፡ በዚህ ወቅት የቤተሰቡ አባላት በሙሉ እንቅልፍ ላይ ናቸው፡፡ የአካባቢው ነዋሪም ሰለሚያንቀላፋ እና አካባቢው ጭር ስለሚል በሽተኛው ከቤት ወጥቶ ማንም ሳያየው ሰፈሩን አቆራርጦ ርቆ ሊሄድ ይችላል፣ የመኪና አደጋ፣ ጉድጓድ ውስጥ የመገኘት ክስተት፣ በዘራፊዎች የመደብደብ አደጋ ወይም በፀጥታ ፖሊሶች የመያዝ እድል ካላጋጠመው ወይም በራሱ ጊዜ ከንቅልፉ የመንቃት እድል ካላጋጠመው በስተቀር ማለት ነው፡፡
  1. በእንቅልፍ ልቡ መንቀሳቀሱ ክስተት የሚቆይበት ጊዜ አብዛኛውን ጊዜ ከጥቂት ደቂቃቆች አንስቶ እስከ ግማሽ ሰአት ያህል ነው፡፡
  1. ከእንቅልፉ ሲነቃ በሽተኛው ግራ ይገባዋል ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ራሱንና አካባቢውን ሊስት ይችላል፡፡

ስሊፕ ዎኪንግ መጓዝ ብቻ ሳይሆን በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም ማድረግ ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የቤት እቃ አቀማመጥን መቀየር፣ ልብስ መልበስ ወይም ማውለቅ፣ ወይም ደግሞ መኪና ውስጥ ገብቶ ማሽከርከር ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውየው በጉዞ ላይ ሆኖ አይኖቹን የማይጨፍን ሲሆን በፊቱ ላይም ምንም የተለየ ስሜት አይነበብበትም፡፡ እንዲነቃ ከተደረገ ግን ይምታታበታል ወይም ግራ ይጋባል፡፡ ብዙ ሰዎች በእንቅልፍ ልባቸው የሚጓዙ ሰወች ጉዳት አይደርስባቸውም ብለው የሚያስቡ ቢሆንም ይህ ግን የተሳሳተ ነው፡፡ ሚዛናቸውን መጠበቅ ባለመቻላቸውና አንሸራቷዋቸው በመውደቅም ሁልጊዜም ማለት ይቻላል ጉዳት ይደረስባቸዋል፡፡ ህመሙ በተለያዩ የእድሜ ክልሎች ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ በአብዛኛው ሊከሰት የሚችለው ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ካሉት ላይ ነው፡፡ መነስኤው ንምድነው? በህፃናት ላይ መንስኤው ኢ ልቦናዊ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ እነዚህም ድካም፣ በፈተና የእነቅልፍ ጊዜ ወቅት እንቅልፍ ሳይተኛ ማደራቸው ሊሆን ይችላል፡፡ አዋቂዎች በተመለከተ ደግሞ ያልተለመደ የባህሪ ለውጥ መከሰት፣ ጭንቀት ወይም መፍትሄን ያልተገኘላቸው ማህበራዊ ጉዳቶች ተፈጥረው ሊሆን ይችላል፡፡ ህመሙ ያለባቸው ወላጆች ችግሩን ወደ ልጆቻቸው ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ህክምናው ምንድን ነው? ህመሙ የተዋጣለት ህክምና አለው፡፡ በበሽተኛው ላይ ጉዳት እንዳይደርስበት ግን ክፍሉንና ቤቱን አደጋ ሊያስከት ከሚችሉ ነገሮች ነፃ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በሽተኛው በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ ሲጓዝ ጠልፈው ሊጥሉት የሚችሉ ነገሮችን ለምሳሌ የኤሌክትሪክ ገመዶችን፣ ትናንሽ እቃዎችን ማራቅ ያስፈልጋል፡፡ በሽታው ወደ ውጪ እንዳይወጣ ዋናውን የቤት በር ቆልፎ ቁልፉን እሱ ከማይደርስበት ስፍራ መደበቅ ያስፈልጋል፡፡ የአልኮል መጠጦችንና አእምሮን ሊያደነዝዙ የሚችሉ ሌሎች ነገሮችን ከመውሰደ መቆጠበ አለበት፡፡ በመድሀኒት የታገዘ ህክምና! መድሀኒቶችን የምትጠቀመው ሀኪምህ ካመነበት ብቻ ነው፡፡ መድሀኒቶቹ የሚያስገኙት ውጤት የተወሰነና አጭር ቆይታ ያለው ሲሆን አእምሮን የማረጋጋት ብቃት አላቸው፡፡ ሌላው የህክምና አማራጭ ደግሞ ሳይኮቴራፒ የሚባለው ነው፡፡ ይህም በአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞቹ አማካኝነት የሚሰጥ ነው፡፡ አእምሮን ዘና ለማድረግ የሚረዳው እና “ሪላክሴሽን ትሬዲንግ” የሚባለው የስነ-ልቦና ህክምናም በሽተኛውን ሊረዳው ይችላል፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አድርግ፡-

  1. ቤት ውስጥ በተቻለ መጠን ብቻህን አትተኛ
  2. የመኖሪያ ቤትህን የውጪ በር ይቆለፍና አንተ የማታውቀው ቦታ ይቀመጥ
  3. መኪና ለማሽከርከር አትሞክር
  4. ችግሩ እንዳለብህ በምትኖርበት አካባቢ ላለው ህዝብ አሳውቅ፡፡ ችግሩ ሲከሰትብህ ፈጥነው ሊተባበሩህ ይችላሉና፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.