የጤና ነገር

ጃፓናውያን ማለዳ እንደተነሱ ለብ ያለ ውሃን የመጠጣት ልምድ እንዳላቸው የሚነገር ሲሆን፥ ይህም እጅግ በርካታ ህመሞችን ለማዳን እና ለመከላከል እንደሚያስችልም ነው በተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ማረጋገጥ የተቻለው።
ለብ ያለ ውሃን መጠጣት ለረዥም ጊዜ ታዋቂ የሆኑ በሽታዎችንና ዘመን አመጣሽ በሽታዎችን ሳይቀር ለማዳንም ሆነ ለመከላከል ያስችላል ተብሏል በጥናቱ።

ለአብነትም ፣ ለጨጓራ ህመም፣ ለብሮንካይትስ፣ ለኩላሊት
ለስኳር ህመም ፣ ለአስም፣ ለሳምባ ነቀርሳ፣ ለወር አበባ መዛባት፣
ለምግብ አለመስማማት፣ ለደም ግፊት፣ ለቁርጠት፣ ለካንሰር፣ ለራስ ምታት፣ ፈጣን የልብ ምትን ለማስተካከል፣ ለድርቀት ፣ ማጅራት ገትር በሽታን ለመከላከል፣ ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ ለጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ህመሞች እና ለሌሎችም ፍቱን ነው።

አወሳሰድ፦

ግማሸ ሊትር ለብ ያለ ውሃን ከመኝታችን ከተነሳነ በኋላ መውሰድ ፤ ከዚያም ለ45 ደቂቃ ምንም አይነት ምግብ አለመመገብ።
ቁርስ ከተመገብን በኋላም ለቀጣይ ሁለት ሰዓታት ሌላ ተጨማሪ ምግብ አለመውሰድ ።
በዕድሜ የገፉ ሰዎች የቻሉትን ያህል ውሃ እንዲጠጡ ሲመከር፥ ሌሎች ግን እስከ አራት ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃን እንዲጠጡ ነው የሚመከረው።
የተሻለ ውጤት ለማግኘትም ይህንኑ በየቀኑ ከ20 ቀናት እስከ አንድ ወር ድረስ ማድረግ ይገባል።
በተመሳሳይ ቀዝቃዛ ውሃን ከምግብ በኋላ ከመውሰድ ይልቅ ለብ ያለ ውሃን መጠቀሙ ተመራጭ ነው።
ቀዝቃዛ ውሃ ከምግብ በኋላ በሚወሰደበት ወቅት ቅዝቃዜው የወሰድነው ምግብ ቅባት ያለው ከሆነ እንዲረጋ ያደርጋል።
ይህ የረጋ ምግብ በሰውነት ከሚመነጩ አሲዶች እና ኢንዛይሞች ጋር ሲገናኝም ካንሰርን ሊያስከትል ሁሉ ይችላል።
በመሆኑም ከምግብ በኋላ ለብ ያለ ውሃ ፣እንደ ሻይ ያሉ ትኩስ መጠጦች አልያም ሾርባ መውሰድ ይመረጣል።

ለብ ያለ ውሃ መጠጣት ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደሌለውም ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል። ሊሰመርበት የሚገባው ግን ለብ ያለውሃ /የጋለ /ውሃ አይደለም ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ
ምንጭ፦ Healthy Life Land

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.