ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ
አዲስ ጉዳይ

SI_joint_anatomy01የምንመገበው ምግብ የረሃብን ስሜት ከማስታገስ በላይ የሆኑ በርካታ ችግሮች አሉት፡፡ አሁንም ድረስ የማዕድ አይነት የሀብት ደረጃ ማሳያ ነው- በብዙ ሀገራት፡፡ ‹ውድ ምግብ በልቻለሁ› ማለትም የሃብታምነት መለኪያ ነው፡፡ ምግብ ተትረፍርፎ ከሚበላው የሚደፋው የበዛባቸዋል የሚባሉት በምእራቡ አለም ሀገራት ደግሞ ተስፋ የቆረጡ፣ በድብርት የተዋጡ እና ራሳቸውን የሚጠሉ ሰዎች ፊታቸውን ወደ ምግብ በማዞር የሚጠሉትን ስሜት ብዙ በመመገብ ሊርቁት ይሞክራሉ፡፡ ከአለቅጥ ውፍረት መንስኤዎች አንዱ ይሄው አለአግባብ ሲበሉና ሲጠጡ መዋል ነው፡፡

የዘመናችን ሳይንስ ከምግብ ጥቅም እና ጉዳት አልፎ ለእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ለጤንነትና ለፈውስን የሚበጁ ምግቦችን እየዘረዘረ ማስቀመጥ ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የዛሬ ትኩረታችን የበርካታ እናቶች፣ ጎልማሶችና አዛውንቶች ችግር ስለሆነው የመገጣጠሚያ አካላት ጤንነት ነው፡፡ በስነ ምግብ ምሁራንና ተመራማሪዎች ዘንድ መገጣጠሚያዎችን ያበረታሉ፣ ያጠነክራሉ ከዛም አልፈው ተርፈው ለአጥንትም ይበጃሉ ተብለው የተለዩ 7 ምግቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

የሰውነትን መቆጣት ይከላከላሉ ተብለው የሚጠከቀሱትን ምግቦች አዘውትሮ መመገብ ለመገጣጠሚያችን ጤንነት ጠቃሚ እንደሆነ የስፖርት ኒውትሪሽኒስቷ እና የ ‘nancy clark’ sports nutrition guide book’ ደራሲ ናንሲ ክላርክ ይናገራሉ፡፡

“በጣም ወደ ተፈጥሮ የተጠጉ፣ ወደ ምድር የቀረቡና በፋብሪካ የልተዘጋጁ ምግቦችን ብንመገብ ጥሩ ነው፡፡ ጠተጠባበሱ፣ በፋብሪካ የተዘጋጁ፣ በስብ የታጨቁ እና በግሪል የተጠበሱ ስጋወችን መመገብ ችግሩ እንዲፈጠር በሩን ይከፍታሉ” ብለዋል፡፡

የቼሪ ፍሬዎች

እንደ እንጆሪ፣ ብሉ ቤሪ፣ ራሲረፕ ቤሪ ወዘተ… ያሉት ፍሬዎች ቀለማቸውን ያገኙት Anthocyanins ከተኙ ከተፈጥሮአዊ የተክል ኬሚካሎች ነው፡፡ የበርካታ ጥናቶች ውጤት እንዳሳየው ከሆነ ትኩስ የቸሪ ፍሬዎች መመገብ አልያም ጭማቂውን መጠጣት የሰውነት መቆጣት ስሜቶችን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች ደግሞ ትኩስ ቼሪ በመገጣጠሚያወች ላይ የሚከሰትን ድንገተኛ የህመም ስሜት ይቀንሳሉ ብለዋል፡፡

ሚጥሚጣ

በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ነው፡፡ ቫይታመን ሲ ደግሞ ሰውነት collagen የተሰኘውን ጠቃሚ ንጥረ ነገር እንዲያመርት ይረዳዋል፡፡ይህ ንጥረ ነገር ለመገጣጠሚያ አካላት ምቾት እንዲሁም ለጅማቶችና ለደም ስሮች ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡ ከሚጥምጣ በተጨማሪም ብርቱካን፣ ቲማቲምና አናናስም መመገብ ይቻላል፡፡

ሳልመን (አሳ)

ስለ አጥንት ጥንካሬ ሲነሳ ሳልመን በመጀመሪያ ደረጃ ከምናስብቸው ምግቦች አንዱ ላይሆን ይችላል፡፡ የስፖርት ኒውትሪሽኒስቷ ክላርክ ግን በተለይ በጣሳ የታሸገ ሳልመን በዋነኛነት ለአጥንት ጠቃሚ ነው ይላሉ፡፡ አጥነት እንዲጠነክር በሚያደርጉት በካልሲየም እና ቫይታሚን ዲ የበለፀገ ነው፡፡ ሳልመንድ የኦሜጋ -3 የተሞላ በመሆኑ የመቆጣት ስሜትን ይቀንሳል፡፡

በተጨማሪም ከፍተኛ የካልሲየም እና የቫይታሚን ዲ ይዘት ያላቸውን እርጎና ወተት ይውሰዱ፡፡ እንደ ሰርዲን ያሉ ዘይታም አሳዎችንም መመገብዎ ተጨማሪ ኦሜጋ-3 ያስገኝልወታል፡፡

አጃ

እንደ አጃ ያሉ ያልተፈለጉ እህሎች የሰውነት መቆጣትን ይቀንሳሉ፡፡ በፋብሪካ ተመርተው የሚወጡ እንደ ነጭ ስንዴ ዱቄት ያሉት ደግሞ ተቃራኒው እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ስፖርታዊ እንቅስቃሴወች አጥንትና ጡንቻን ለማጠንከር የሚረዱ ቢሆንም የመገጣጠሚያ አካላት ላይ ግን ጫና ያሳርፋሉ፡፡ ለእንቅስካሴወቹ ሲባል ሀይልን እንዲሰጥ ብቻ ታስቦ መመገብ ተገቢ አይደለም የሚሉት ክላርክ ለማገገምና ለመዳን ተብሎ መመገብ እንደሚገባ ያሰምሩበታል፡፡

እርድ

Cur cumin በተሰኘ ተፈጥሮአዊ ኬሚካል የበለፀገ ነው፡፡ አንድ ጥናት አንዳመለከተው ከሆነ ከዚህ ንጥረ ነገር የተዘጋጀ እርድ ውጤት Ibuprofen የተሰኘው የጉልበት ህመምን የሚያስታግስ መድሀኒት ከሚሰጠው ጥቅም ዝንጅብል ሌሎች የመቆጣት ስሜቶችን የሚቀንሱ የቅመማ ቅመም ዝርያወች ናቸው፡፡ እርድ፣ ቀረፋ እና ዝንጅብል በአብዛኛው የሀገራችን ምግብ ላይ መገኘታቸውና ሰውነታችንም እነሱን በመላመዱ ተጠቃሚዎች ያደርገናል፡፡

 

አብዛኛው በሱፐት ማርኬቶች ይገኛሉ፡፡ የሰውነት መቆጣት አዝምሚያን በሚዋጉ በርካታ ንጥረ ነገቶችም የተሞላ ነው፡፡ ሌሎች የለውዝ ዝርያወችንም ጠቃሚ ናቸው፡፡ ሁሉም በሚባል መልኩ ከፍተኛ ካሎሪ ስለሚይዙ ስለ ክብደትዎ የሚጨነቁ ከሆነ ብዙ አችንዲመገቧቸው አይመከርም፡፡

 የፈረንጅ ጎመን

ይህ ተክልና ሌሎችም ጠቆር ያለ አረንጓዴ ቀለም ያላቸው ባለ ቅጠል ተክሎች ለመገጣጠሚያ አካላት በሚበጁ ንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ናቸው፡፡ አንቲ-ኦክሲደንቶች፣ ቤታ ካሮቲን እና ቫይታሚን ሲን በብዛት ያገኙበታል፡፡ እንደ ፈረንጅ ጎመን ያሉት ደግሞ የካልሲየም ምርጥ መገኛዎች ናቸው፡፡ ካልሲየም ምርጥ ጠንካራ አጥንቶች እንዲኖሩ ያግዛል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.